Skip to content
← 2 Chronicles

Chapter 17 · Amharic

2 Chronicles

1በርሱም፡ፋንታ፡ልጁ፡ኢዮሳፍጥ፡ነገሠ፥በእስራኤልም፡ላይ፡ጠነከረ።

2በተመሸጉትም፡በይሁዳ፡ከተማዎች፡ዅሉ፡ወታደሮችን፡አኖረ፥በይሁዳም፡አገር፡አባቱም፡አሣ፡ በወሰዳቸው፡በኤፍሬም፡ከተማዎች፡ዘበኛዎችን፡አስቀመጠ።

3እግዚአብሔርም፡ከኢዮሳፍጥ፡ጋራ፡ነበረ፥በፊተኛዪቱ፡በአባቱ፡በዳዊት፡መንገድ፡ኼዷልና፥በዓሊምንም፡ አልፈለገምና፤

4ነገር፡ግን፥የአባቱን፡አምላክ፡ፈለገ፥በትእዛዙም፡ኼደ፥የእስራኤልንም፡ሥራ፡አልሠራም።

5እግዚአብሔርም፡መንግሥቱን፡በእጁ፡አጸና፤ይሁዳም፡ዅሉ፡እጅ፡መንሻ፡ለኢዮሳፍጥ፡አመጣ፤እጅግም፡ ብዙ፡ብልጥግናና፡ክብር፡ኾነለት። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

6ልቡም፡በእግዚአብሔር፡መንገድ፡ከፍ፡ከፍ፡አለ፤የኰረብታውን፡መስገጃዎችና፡የማምለኪያ፡ዐጸዱንም፡ ከይሁዳ፡አስወገደ።

7በነገሠም፡በሦስተኛው፡ዓመት፡በይሁዳ፡ከተማዎች፡ያስተምሩ፡ዘንድ፡ መሳፍንቱን፥ቤንኀይልን፥ዐብድያስን፥ዘካርያስን፥ናትናኤልን፥ሚክያስን፥ሰደደ።

8ከነርሱም፡ጋራ፡ሌዋውያንን፡ ሸማያን፥ነታንያን፥ዝባድያን፥ዐሳሄልን፥ሰሚራሞትን፥ዮናታንን፥አዶንያስን፥ጦብያን፥ጦባዶንያን፡ሰደደ፡ ከነርሱም፡ጋራ፡ካህናቱን፡ኤሊሳማንና፡ኢዮራምን፡ሰደደ።

9እነርሱም፡የእግዚአብሔርን፡የሕጉን፡መጽሐፍ፡ይዘው፡በይሁዳ፡ያስተምሩ፡ነበር፤ወደይሁዳም፡ከተማዎች፡ ዅሉ፡ኼደው፡ሕዝቡን፡ያስተምሩ፡ነበር።

10በይሁዳም፡ዙሪያ፡በነበሩ፡መንግሥታት፡ዅሉ፡ላይ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ድንጋጤ፡ኾነ፥ከኢዮሳፍጥም፡ ጋራ፡አልተዋጉም።

11ከፍልስጥኤማውያን፡ለኢዮሳፍጥ፡እጅ፡መንሻና፡የብር፡ግብር፡ያመጡ፡ነበር፤ዐረባውያንም፡ደግሞ፡ ከመንጋዎቻቸው፡ሰባት፡ሺሕ፡ሰባት፡መቶ፡አውራ፡በጎችና፡ሰባት፡ሺሕ፡ሰባት፡ሺሕ፡ሰባት፡መቶ፡አውራ፡ ፍየሎች፡ያመጡለት፡ነበር።

12ኢዮሳፍጥም፡እየበረታና፡እጅግም፡እየከበረ፡ኼደ፤በይሁዳም፡ግንቦችንና፡የጐተራ፡ከተማዎችን፡ሠራ።

13በይሁዳም፡ከተማዎች፡ብዙ፡ሥራ፡ሠራ፥በኢየሩሳሌምም፡ጽኑዓን፡ኀያላን፡ሰልፈኛዎች፡ነበሩት።

14ቍጥራቸውም፡እንደ፡አባቶቻቸው፡ቤት፡ይህ፡ነበረ፤ከይሁዳ፡ሻለቃዎች፡አለቃው፡ዓድና፥ከርሱም፡ጋራ፡ ሦስት፡መቶ፡ሺሕ፡ጽኑዓን፡ኀያላን፡ሰዎች፡ነበሩ፤

15ከርሱም፡በዃላ፡አለቃው፡ይሆሐናን፥ከርሱም፡ጋራ፡ኹለት፡መቶ፡ሰማንያ፡ሺሕ፡ሰዎች፡ነበሩ፤

16ከርሱም፡በዃላ፡በፈቃዱ፡ራሱን፡ለእግዚአብሔር፡የቀደሰ፡የዝክሪ፡ልጅ፡ዓማስያ፥ከርሱም፡ጋራ፡ኹለት፡ መቶ፡ሺሕ፡ጽኑዓን፡ኀያላን፡ሰዎች፡ነበሩ።

17ከብንያምም፡ጽኑዕ፡ኀያል፡የነበረው፡ኤሊዳሄ፥ከርሱም፡ጋራ፡ቀስትና፡ጋሻ፡የሚይዙ፡ኹለት፡መቶ፡ሺሕ፡ ሰዎች፡ነበሩ፤

18ከርሱም፡በዃላ፡ዮዛባት፥ከርሱም፡ጋራ፡ለሰልፍ፡የተዘጋጁ፡መቶ፡ሰማንያ፡ሺሕ፡ሰዎች፡ነበሩ።

19ንጉሡ፡በተመሸጉ፡በይሁዳ፡ከተማዎች፡ዅሉ፡ካኖራቸውም፡ሌላ፡እነዚህ፡ንጉሡን፡ያገለግሉ፡ነበር።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source