1የይሁዳም፡ንጉሥ፡ኢዮሳፍጥ፡ወደ፡ቤቱ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡በደኅና፡ተመለሰ።
2ባለራእዩ፡የዐናኒ፡ልጅ፡ኢዩ፡ሊገናኘው፡ወጣ፥ንጉሡንም፡ኢዮሳፍጥን፦ከሓዲውን፡ታግዛለኽን፧ወይስ፡ እግዚአብሔርን፡የሚጠሉትን፡ትወዳ፟ለኽን፧ስለዚህም፡ነገር፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ቍጣ፡ኾኖብኻል።
3ነገር፡ግን፥የማምለኪያ፡ዐጸዶቹን፡ከምድር፡አስወግደኻልና፥እግዚአብሔርንም፡ትፈልግ፡ዘንድ፡ልብኽን፡ አዘጋጅተኻልና፥መልካም፡ነገር፡ተገኝቶብኻል፡አለው።
4ኢዮሳፍጥም፡በኢየሩሳሌም፡ተቀመጠ፤ደግሞም፡ከቤርሳቤሕ፡ዠምሮ፡እስከ፡ተራራማው፡እስከኤፍሬም፡ አገር፡ድረስ፡ወደ፡ሕዝቡ፡ወጥቶ፡ወዳባቶቻቸው፡አምላክ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡መለሳቸው።
5በምድር፡ላይ፡በተመሸጉት፡በይሁዳ፡ከተማዎች፡ዅሉ፡በያንዳንዱ፡ከተማ፡ውስጥ፡ፈራጆች፡አኖረ።
6ፈራጆቹንም፦ለእግዚአብሔር፡እንጂ፡ለሰው፡አትፈርዱምና፥ርሱም፡በፍርድ፡ነገር፡ከእናንተ፡ጋራ፡ ነውና፥የምታደርጉትን፡ተመልከቱ።
7አኹንም፡እግዚአብሔርን፡መፍራት፡በእናንተ፡ላይ፡ይኹን፤በአምላካችንም፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡በደልና፡ ለሰው፡ፊት፡ማድላት፡መማለጃም፡መውሰድ፡የለምና፡ዅሉን፡ተጠንቅቃችኹ፡አድርጉ፡አላቸው።
8ኢዮሳፍጥም፡ከሌዋውያንና፡ከካህናት፡ከእስራኤልም፡የአባቶች፡ቤቶች፡አለቃዎች፥በእግዚአብሔር፡ስም፡ ፍርድን፡እንዲፈርዱ፡ክርክርንም፡እንዲቈርጡ፡በኢየሩሳሌም፡ሾመ።እነርሱም፡በኢየሩሳሌም፡ተቀመጡ።
9እንዲህም፡ብሎ፡አዘዛቸው፦እንዲሁ፡እግዚአብሔርን፡በመፍራት፡በቅንነትም፡በፍጹምም፡ልብ፡አድርጉ።
10በከተማዎቻቸውም፡ከተቀመጡት፡ከወንድሞቻችኹ፡በደምና፡በደም፡መካከል፡በሕግና፡በትእዛዝ፡ በሥርዐትና፡በፍርድም፡መካከል፡ያለ፡ማናቸውም፡ነገር፡ወደ፡እናንተ፡ቢመጣ፡እግዚአብሔርን፡ እንዳይበድሉ፥ቍጣም፡በእናንተና፡በወንድሞቻችኹ፡ላይ፡እንዳይመጣ፡አስጠንቅቋቸው፤እንዲህም፡ብታደርጉ፡ በደለኛዎች፡አትኾኑም። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
11እንሆም፥ለእግዚአብሔር፡በሚኾነው፡ነገር፡ዅሉ፡የካህናቱ፡አለቃ፡አማርያ፥በንጉሡም፡ነገር፡ዅሉ፡ የይሁዳ፡ቤት፡አለቃ፡የይስማኤል፡ልጅ፡ዝባድያ፡በላያችኹ፡ተሾመዋል፤ሌዋውያኑም፡ደግሞ፡በፊታችኹ፡ አለቃዎች፡ይኾናሉ፤በርትታችኹም፡አድርጉ፥እግዚአብሔርም፡መልካም፡ከሚያደርግ፡ጋራ፡ይኹን።