Skip to content
← 2 Chronicles

Chapter 20 · Amharic

2 Chronicles

1እንዲህም፡ኾነ፤ከዚህ፡በዃላ፡የሞዐብና፡የዐሞን፡ልጆች፡ከነርሱም፡ጋራ፡ምዑናውያን፡ኢዮሳፍጥን፡ሊወጉ፡ መጡ።

2ወሬኛዎችም፡መጥተው፦ከባሕሩ፡ማዶ፡ከሶርያ፡ታላቅ፡ሰራዊት፡መጥቶብኻል፤እንሆም፥ዐይንጋዲ፡ በተባለች፡በሐሴሶን፡ታማር፡ናቸው፡ብለው፡ለኢዮሳፍጥ፡ነገሩት።

3ኢዮሳፍጥም፡ፈራ፥እግዚአብሔርንም፡ሊፈልግ፡ፊቱን፡አቀና፤በይሁዳም፡ዅሉ፡ጾም፡ዐወጀ።

4ይሁዳም፡እግዚአብሔርን፡ይፈልግ፡ዘንድ፡ተከማቸ፤ከይሁዳ፡ከተማዎችም፡ዅሉ፡እግዚአብሔርን፡ይፈልጉ፡ ዘንድ፡መጡ።

5ኢዮሳፍጥም፡በይሁዳና፡በኢየሩሳሌም፡ጉባኤ፡መካከል፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ውስጥ፡በዐዲሱ፡አደባባይ፡ ፊት፡ቆመ፤

6እንዲህም፡አለ፦አቤቱ፡የአባቶቻችን፡አምላክ፡ሆይ፥በሰማይ፡ያለኽ፡አምላክ፡አንተ፡ አይደለኽምን፧የአሕዛብንስ፡መንግሥታት፡ዅሉ፡የምትገዛ፡አንተ፡አይደለኽምን፧ኀይልና፡ችሎታ፡በእጅኽ፡ ነው፥ሊቋቋምኽም፡የሚችል፡የለም።

7አምላካችን፡ሆይ፥በዚህ፡ምድር፡የነበሩትን፡አሕዛብ፡ከሕዝብኽ፡ከእስራኤል፡ፊት፡ያሳደድኽ፥ለወዳጅኽም፡ ለአብርሃም፡ዘር፡ለዘለዓለም፡የሰጠኻት፡አንተ፡አይደለኽምን፧

8እነርሱም፡የተቀመጡባት፥ለስምኽም፡መቅደስን፡ሠርተውባት።

9ክፉ፡ነገር፥የፍርድ፡ሰይፍ፡ወይም፡ቸነፈር፡ወይም፡ራብ፥ቢመጣብን፡ስምኽ፡ባለበት፡በዚህ፡ቤት፡ፊትና፡ በፊትኽ፡ቆመን፡በመከራችን፡ወዳንተ፡እንጮኻለን፥አንተም፡ሰምተኽ፡ታድነናለኽ፡አሉ።

10አኹንም፥እንሆ፥እስራኤል፡ከግብጽ፡ምድር፡በወጡ፡ጊዜ፡ያልፉባቸው፡ዘንድ፡ያልፈቀድኽላቸው፥ነገር፡ ግን፥ፈቀቅ፡ብለው፡ያላጠፏቸው፥የዐሞንና፡የሞዐብ፡ልጆች፡የሴይርም፡ተራራ፡ሰዎች፥

11እንሆ፥ለወሮታችን፡ክፋት፡ይመልሱልናል፤ከሰጠኸንም፡ርስት፡ያወጡን፡ዘንድ፡መጥተዋል።

12አምላካችን፡ሆይ፥አንተ፡አትፈርድባቸውምን፧ይህን፡የመጣብንን፡ታላቅ፡ወገን፡እንቃወም፡ዘንድ፡ አንችልም፤የምናደርገውንም፡አናውቅም፤ነገር፡ግን፥ዐይኖቻችን፡ወዳንተ፡ናቸው።

13የይሁዳም፡ሰዎች፡ዅሉ፡ከሕፃናታቸውና፡ከሚስቶቻቸው፡ከልጆቻቸውም፡ጋራ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ ቆመው፡ነበር።

14የእግዚአብሔርም፡መንፈስ፡ከአሣፍ፡ወገን፡በነበረው፡በሌዋዊው፡በማታንያ፡ልጅ፡በይዒኤል፡ልጅ፡ በበናያስ፡ልጅ፡በዘካርያስ፡ልጅ፡በየሕዚኤል፡ላይ፡በጉባኤው፡መካከል፡መጣ፤

15እንዲህም፡አለ፦ይሁዳ፡ዅሉ፥በኢየሩሳሌምም፡የምትኖሩ፥አንተም፡ንጉሡ፡ ኢዮሳፍጥ፥ስሙ፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላችዃል።ሰልፉ፡የእግዚአብሔር፡ነው፡እንጂ፡የእናንተ፡ አይደለምና፡ከዚህ፡ታላቅ፡ወገን፡የተነሣ፡አትፍሩ፥አትደንግጡም።

16ነገ፡በእነርሱ፡ላይ፡ውረዱ፤እንሆ፥በጺጽ፡ዐቀበት፡ይወጣሉ፤በሸለቆውም፡መጨረሻ፡በይሩኤል፡ምድረ፡ በዳ፡ፊት፡ለፊት፡ታገኟቸዋላችኹ።

17እናንተ፡በዚህ፡ሰልፍ፡የምትዋጉ፡አይደላችኹም፤ይሁዳና፡ኢየሩሳሌም፡ሆይ፥ተሰለፉ፥ዝም፡ብላችኹ፡ ቁሙ፥የሚኾነውንም፡የእግዚአብሔርን፡መድኀኒት፡እዩ፤እግዚአብሔርም፡ከእናንተ፡ጋራ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ነውና፥አትፍሩ፥አትደንግጡም፥ነገም፡ውጡባቸው።

18ኢዮሳፍጥም፡በምድር፡ላይ፡ተደፋ፡ይሁዳም፡ዅሉ፡በኢየሩሳሌምም፡የሚኖሩ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ ወደቁ፥ለእግዚአብሔርም፡ሰገዱ።

19ሌዋውያንም፥የቀአት፡ልጆችና፡የቆሬ፡ልጆች፥የእስራኤልን፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡በእጅግ፡ታላቅ፡ ድምፅ፡ያመሰገኑት፡ዘንድ፡ቆሙ።

20ማልደውም፡ተነሡ፥ወደቴቁሔም፡ምድረ፡በዳ፡ወጡ፤ሲወጡም፡ኢዮሳፍጥ፡ቆመና፦ይሁዳና፡ በኢየሩሳሌም፡የምትኖሩ፡ሆይ፥ስሙኝ፤በአምላካችኹ፡በእግዚአብሔር፡እመኑ፥ትጸኑማላችኹ፤በነቢያቱም፡ እመኑ፥ነገሩም፡ይሰላላችዃል፡አለ።

21ከሕዝቡም፡ጋራ፡ተማክሮ፡በሰራዊቱ፡ፊት፡የሚኼዱትን፦ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፥እግዚአብሔርን፡ አመስግኑ፡የሚሉትንም፥ጌጠኛ፡ልብስም፡ለብሰው፡የሚያመሰግኑትን፥ለእግዚአብሔርም፡የሚዘምሩትን፡ መዘምራን፡አቆመ።

22ዝማሬውንና፡ምስጋናውንም፡በዠመሩ፡ጊዜ፡ይሁዳን፡ሊወጉ፡በመጡት፡በዐሞንና፡በሞዐብ፡ልጆች፡ በሴይርም፡ተራራ፡ሰዎች፡ላይ፡እግዚአብሔር፡ድብቅ፡ጦርን፡አመጣባቸው፤እነርሱም፡ተመቱ።

23የዐሞንና፡የሞዐብ፡ልጆችም፡በሴይር፡ተራራ፡በሚኖሩት፡ላይ፡ፈጽመው፡ይገድሏቸው፡ዘንድ፡ ያጠፏቸውም፡ዘንድ፡ተነሥተውባቸው፡ነበር፤በሴይርም፡የሚኖሩትን፡ካጠፉ፡በዃላ፡እያንዳንዱ፡ባልንጀራውን፡ ለማጥፋት፡ተረዳዳ።

24የይሁዳም፡ሰዎች፡ወደምድረ፡በዳ፡ግንብ፡በመጡ፡ጊዜ፡ሕዝቡን፡አዩ፤እንሆም፥በምድሩ፡ዅሉ፡ሬሳ፡ ሞልቶ፡ነበር፥ያመለጠም፡ሰው፡አልነበረም።

25ኢዮሳፍጥና፡ሕዝቡም፡ምርኮ፡ይወስዱ፡ዘንድ፡መጡ፡ብዙ፡ከብትና፡ልዩ፡ልዩ፡ ዕቃም፥ልብስም፥እጅግም፡ያማረ፡ዕቃ፡አገኙ፥በዘበዙትም፥ዅሉንም፡ይሸከሙ፡ዘንድ፡ አልቻሉም፤ከምርኮውም፡ብዛት፡የተነሣ፡እስከ፡ሦስት፡ቀን፡ድረስ፡ይበዘብዙ፡ነበር።

26በአራተኛውም፡ቀን፡በበረከት፡ሸለቆ፡ውስጥ፡ተሰበሰቡ፥በዚያም፡እግዚአብሔርን፡ባረኩ፤ስለዚህም፡ያ፡ ስፍራ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡የበረከት፡ሸለቆ፡ተባለ።

27የይሁዳና፡የኢየሩሳሌም፡ሰዎች፥በፊታቸውም፡ኢዮሳፍጥ፥እግዚአብሔር፡በጠላቶቻቸው፡ላይ፡ደስ፡ አሠኝቷቸዋልና፥በደስታ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ይኼዱ፡ዘንድ፡ተመለሱ።

28በበገናም፡በመሰንቆም፡በመለከትም፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ወደእግዚአብሔርም፡ቤት፡ገቡ።

29እግዚአብሔር፡የእስራኤልን፡ጠላቶች፡እንደ፡ወጋ፡በሰሙ፡ጊዜ፡በምድር፡መንግሥታት፡ዅሉ፡ላይ፡ የእግዚአብሔር፡ፍርሀት፡ኾነ።

30የኢዮሳፍጥም፡መንግሥት፡ጸጥ፡አለች፥አምላኩም፡በዙሪያው፡ካሉ፡አሳረፈው።

31ኢዮሳፍጥ፡በይሁዳ፡ላይ፡ነገሠ፤መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜም፡የሠላሳ፡ዐምስት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ ነበረ፥በኢየሩሳሌምም፡ኻያ፡ዐምስት፡ዓመት፡ነገሠ፤እናቱም፡የሺልሒ፡ልጅ፡ዓዙባ፡ነበረች።

32በአባቱም፡በአሣ፡መንገድ፡ኼደ፥ከርሱም፡ፈቀቅ፡አላለም፤በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቅን፡አደረገ።

33ነገር፡ግን፥የኰረብታው፡መስገጃዎች፡አልተወገዱም፤ሕዝቡም፡ገና፡ልባቸውን፡ወዳባቶቻቸው፡አምላክ፡ አላዘጋጁም፡ነበር።

34የቀረውም፡የፊተኛውና፡የዃለኛው፡የኢዮሳፍጥ፡ነገር፥እንሆ፥በእስራኤል፡ነገሥታት፡መጽሐፍ፡ውስጥ፡ በሚገኘው፡በዐናኒ፡ልጅ፡በኢዩ፡ታሪክ፡ተጽፏል።

35ከዚህም፡በዃላ፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡ኢዮሳፍጥ፡ሥራው፡እጅግ፡ክፉ፡ከኾነ፡ከእስራኤል፡ንጉሥ፡ከአካዝያስ፡ ጋራ፡ተባበረ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

36ወደ፡ተርሴስም፡የሚኼዱትን፡መርከቦች፡ያሠሩ፡ዘንድ፡አንድ፡ኾኑ፤መርከቦቹንም፡በዔጽዮንጋብር፡ አሠሩ።

37የመሪሳም፡ሰው፡የዶዳያ፡ልጅ፡አልዓዛር፦ከአካዝያስ፡ጋራ፡ተባብረኻልና፥እግዚአብሔር፡ሥራኽን፡ አፍርሶታል፡ብሎ፡በኢዮሳፍጥ፡ላይ፡ትንቢት፡ተናገረ።መርከቦቹም፡ተሰበሩ፥ወደ፡ተርሴስም፡ይኼዱ፡ዘንድ፡ አልቻሉም።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source