Skip to content
← 2 Chronicles

Chapter 21 · Amharic

2 Chronicles

1ኢዮሳፍጥም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በዳዊትም፡ከተማ፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡ተቀበረ፤ልጁም፡ኢዮራም፡ በርሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።

2ለርሱም፡የኢዮሳፍጥ፡ልጆች፡ዐዛርያስ፥ይሒኤል፥ዘካርያስ፥ዔዛርያስ፥ሚካኤል፥ሰፋጥያስ፡የሚባሉ፡ ወንድሞች፡ነበሩት፤እነዚህ፡ዅሉ፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡የኢዮሳፍጥ፡ልጆች፡ነበሩ።

3አባታቸውም፡ብዙ፡ስጦታ፥ብርና፡ወርቅ፥የከበረም፡ዕቃ፥በይሁዳም፡የተመሸጉትን፡ከተማዎች፡ ሰጣቸው፤መንግሥቱን፡ግን፡በኵር፡ልጁ፡ስለ፡ኾነ፡ለኢዮራም፡ሰጠ።

4ኢዮራምም፡በአባቱ፡መንግሥት፡ላይ፡ተነሥቶ፡በጸና፡ጊዜ፡ወንድሞቹን፡ዅሉ፡ሌላዎችንም፡የእስራኤልን፡ መሳፍንት፡በሰይፍ፡ገደለ።

5ኢዮራምም፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የሠላሳ፡ኹለት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፥በኢየሩሳሌምም፡ስምንት፡ ዓመት፡ነገሠ።

6የአክአብንም፡ልጅ፡አግብቶ፡ነበርና፥የአክአብ፡ቤት፡እንዳደረገ፡በእስራኤል፡ነገሥታት፡መንገድ፡ ኼደ፤በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ክፉ፡አደረገ።

7ነገር፡ግን፥ከዳዊት፡ጋራ፡ስላደረገው፡ቃል፡ኪዳን፥ለርሱና፡ለልጆቹም፡በዘመናት፡ዅሉ፡መብራት፡ ይሰጠው፡ዘንድ፡ስለሰጠው፡ተስፋ፥እግዚአብሔር፡የዳዊትን፡ቤት፡ያጠፋ፡ዘንድ፡አልወደደም።

8በርሱም፡ዘመን፡ኤዶምያስ፡በይሁዳ፡ላይ፡ዐመፀ፥ለራሱም፡ንጉሥ፡አነገሠ።

9ኢዮራምም፡ከአለቃዎቹና፡ከሠረገላዎቹ፡ዅሉ፡ጋራ፡ተሻገረ፤በሌሊትም፡ተነሥቶ፡ርሱንና፡የሠረገላዎቹን፡ አለቃዎች፡ከበ፟ው፡የነበሩትን፡የኤዶምያስን፡ሰዎች፡መታ።

10ኤዶምያስ፡ግን፡በይሁዳ፡ላይ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ዐመፀ፥በዚያንም፡ዘመን፡ልብና፡ደግሞ፡በርሱ፡ላይ፡ ዐመፀ፥የአባቶቹን፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡ትቶ፡ነበርና።

11ዳግምም፡በይሁዳ፡ተራራዎች፡ላይ፡መስገጃዎችን፡ሠራ፥በኢየሩሳሌምም፡የተቀመጡትን፡እንዲያመነዝሩ፡ አደረጋቸው፥ይሁዳንም፡አሳ፟ተው።

12ከነቢዩም፡ከኤልያስ፡እንዲህ፡የሚል፡ጽሕፈት፡መጣባት፦የአባትኽ፡የዳዊት፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ እንዲህ፡ይላል፦በአባትኽ፡በኢዮሳፍጥ፡መንገድ፡በይሁዳም፡ንጉሥ፡በአሣ፡መንገድ፡አልኼድኽምና፥

13በእስራኤል፡ነገሥታት፡መንገድ፡ግን፡ኼደኻልና፥የአክአብም፡ቤት፡እንዳደረገ፡ይሁዳንና፡በኢየሩሳሌም፡ የሚኖሩትን፡እንዲያመነዝሩ፡አድርገኻልና፥ከአንተም፡የሚሻሉትን፡የአባትኽን፡ቤት፡ወንድሞችኽን፡ገድለኻልና፥

14እንሆ፥እግዚአብሔር፡ሕዝብኽንና፡ልጆችኽን፡ሚስቶችኽንም፡ያለኽንም፡ዅሉ፡በታላቅ፡መቅሠፍት፡ ይቀሥፋል።

15አንተም፡ከደዌው፡ጽናት፡የተነሣ፡አንዠትኽ፡በየዕለቱ፡እስኪወጣ፡ድረስ፡በክፉ፡የአንዠት፡ደዌ፡ ትታመማለኽ።

16እግዚአብሔርን፡የፍልስጥኤማውያንና፡በኢትዮጵያውያን፡አጠገብ፡የሚኖሩትን፡የዐረባውያንን፡መንፈስ፡ በኢዮራም፡ላይ፡አስነሣ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

17ወደ፡ይሁዳም፡ወጡ፥አፈረሷትም፥የንጉሡንም፡ቤት፡ዕቃ፡ዅሉ፥ወንዶች፡ልጆቹንም፡ሴቶች፡ልጆቹንም፡ ማረኩ፤ከታናሹም፡ልጅ፡ከአካዝያስ፡በቀር፡ልጅ፡አልቀረለትም።

18ከዚህም፡ዅሉ፡በዃላ፡እግዚአብሔር፡በማይፈወስ፡ደዌ፡አንዠቱን፡ቀሠፈው።

19ከቀንም፡ወደ፡ቀን፡እንዲህ፡ኾነ፤ከኹለት፡ዓመት፡በዃላ፡ከደዌው፡ጽናት፡የተነሣ፡አንዠቱ፡ ወጣ፥በክፉም፡ደዌ፡ሞተ።ሕዝቡም፡ለአባቶቹ፡ያደርገው፡እንደ፡ነበር፡ለርሱ፡የመቃብር፡ወግ፡አላደረገም።

20መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የሠላሳ፡ኹለት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፥በኢየሩሳሌምም፡ስምንት፡ዓመት፡ ነገሠ፤ማንም፡ሳያዝንለት፡ኼደ፤በዳዊትም፡ከተማ፡እንጂ፡በነገሥታት፡መቃብር፡አልቀበሩትም።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source