Skip to content
← 2 Chronicles

Chapter 23 · Amharic

2 Chronicles

1በሰባተኛውም፡ዓመት፡ዮዳዔ፡በረታ፥የመቶ፡አለቃዎቹንም፥የይሮሐምን፡ልጅ፡ዐዛርያስን፥የይሆሐናንንም፡ ልጅ፡ይስማኤልን፥የዖቤድንም፡ልጅ፡ዐዛርያስን፥የዓዳያንም፡ልጅ፡መዕሴያን፥የዝክሪንም፡ልጅ፡ኤሊሳፋጥን፡ ወስዶ፡ከነርሱ፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡አደረገ።

2ይሁዳንም፡ዞሩ፥በይሁዳም፡ከተማዎች፡ዅሉ፡ሌዋውያንንና፡የእስራኤልን፡አባቶች፡ቤቶች፡አለቃዎች፡ ሰብስበው፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡መጡ።

3ጉባኤውም፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ውስጥ፡ከንጉሥ፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡አደረገ።ዮዳዔም፡ አላቸው፦እንሆ፥እግዚአብሔር፡ስለዳዊት፡ልጆች፡አንደ፡ተናገረ፡የንጉሡ፡ልጅ፡ይነግሣል።

4የምታደርጉት፡ይህ፡ነው፤በሰንበት፡ቀን፡ከምትገቡት፡ከእናንተ፡ከካህናትና፡ከሌዋዊውያን፡ከሦስት፡አንድ፡ እጅ፡በመግቢያ፡በሮች፡በረኛዎች፡ኹኑ፤

5ከሦስት፡አንድ፡እጅም፡በንጉሥ፡ቤት፡ኹኑ፤አንድ፡እጅም፡በመካከለኛው፡በር፡ኹኑ፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡ በእግዚአብሔር፡ቤት፡አደባባይ፡ይኹኑ።

6ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ግን፡ከካህናትና፡ከአገልጋዮቹ፡ሌዋውያን፡በቀር፡ማንም፡አይግባ፤እነርሱ፡ቅዱሳን፡ ናቸውና፥ይግቡ፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡የእግዚአብሔርን፡ሕግ፡ይጠብቅ።

7ሌዋውያንም፡የጦር፡መሣሪያቸውን፡በእጃቸው፡ይዘው፡ንጉሡን፡በዙሪያው፡ይክበቡት፤ወደ፡ቤቱም፡ የሚገባ፡ይገደል፡ንጉሡም፡ሲገባና፡ሲወጣ፡ከርሱ፡ጋራ፡ኹኑ።

8ሌዋውያንና፡ይሁዳም፡ዅሉ፡ካህኑ፡ዮዳዔ፡ያዘዘውን፡ዅሉ፡አደረጉ፤ካህኑም፡ዮዳዔ፡ሰሞነኛዎቹን፡ አላሰናበተም፡ነበርና፥እያንዳንዱ፡በሰንበት፡ቀን፡ይገቡ፡የነበሩትን፡በሰንበትም፡ቀን፡ይወጡ፡የነበሩትን፡ሰዎች፡ ወሰደ።

9ካህኑም፡ዮዳዔ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡የነበረውን፡የንጉሡን፡የዳዊትን፡ጋሻና፡ጦር፡አላባሽ፡አግሬውንም፡ ጋሻ፡ለመቶ፡አለቃዎች፡ሰጣቸው።

10ሕዝቡም፡ዅሉ፡እያንዳንዱ፡የጦር፡መሣሪያውን፡በእጁ፡እየያዘ፡በንጉሡ፡ዙሪያ፡ከቤቱ፡ቀኝ፡እስከቤቱ፡ ግራ፡ድረስ፡በመሠዊያውና፡በቤቱ፡አጠገብ፡እንዲቆም፡አደረገ።

11የንጉሡንም፡ልጅ፡አውጥተው፡ዘውዱን፡ጫኑበት፥ምስክሩንም፡ሰጡት፥አነገሡትም፤ዮዳዔና፡ ልጆቹም፦ንጉሡ፡ሺሕ፡ዓመት፡ይንገሥ፡እያሉ፡ቀቡት።

12ጎቶሊያም፡የሚሮጡትንና፡ንጉሡን፡የሚያመሰግኑትን፡የሕዝቡን፡ድምፅ፡በሰማች፡ጊዜ፡ወደ፡ሕዝቡ፡ ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡መጣች።

13እንሆም፥ንጉሡ፡በመግቢያው፡በዐምዱ፡አጠገብ፡ኾኖ፡ከንጉሡ፡ጋራ፡አለቃዎችና፡መለከተኛዎች፡ ቆመው፡አየች።የአገሩም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ደስ፡ብሏቸው፡መለከቱን፡ይነፉ፡ነበር፤መዘምራንም፡በዜማ፡ዕቃ፡ እያዜሙ፡የምስጋና፡መዝሙር፡ይዘምሩ፡ነበር።ጎቶሊያም፡ልብሷን፡ቀዳ፟፦ዐመፅ፡ነው፥ዐመፅ፡ነው፡ብላ፡ ጮኸች።

14ካህኑም፡ዮዳዔ፡በጭፍራው፡ላይ፡የተሾሙትን፡የመቶ፡አለቃዎች፦ወደ፡ሰልፉ፡መካከል፡ አውጧት፤የሚከተላትም፡በሰይፍ፡ይገደል፡ብሎ፡አዘዛቸው።ካህኑም፦በእግዚአብሔር፡ቤት፡ውስጥ፡ አትግደሏት፡አለ።

15ገለልም፡ብለው፡አሳለፏት፤ርሷም፡ወደፈረሱ፡በር፡መግቢያ፡ወደንጉሡ፡ቤት፡ኼደች፥በዚያም፡ገደሏት።

16ዮዳዔም፡በርሱና፡በሕዝቡ፡ዅሉ፡በንጉሡም፡መካከል፡የእግዚአብሔር፡ሕዝብ፡ይኾኑ፡ዘንድ፡ቃል፡ ኪዳን፡አደረገ።

17ሕዝቡም፡ዅሉ፡ወደበዓል፡ቤት፡ኼደው፡አፈረሱት፥መሠዊያዎቹንና፡ምስሎቹንም፡አደቀቁ፥የበዓልንም፡ ካህን፡ማታንን፡በመሠዊያው፡ፊት፡ገደሉት። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

18ዮዳዔም፡በሙሴ፡ሕግ፡እንደተጻፈው፥እንደ፡ዳዊትም፡ትእዛዝ፥በደስታና፡በመዝሙር፡ለእግዚአብሔር፡ የሚቃጠለውን፡መሥዋዕት፡ያቀርቡ፡ዘንድ፡ዳዊት፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡የከፈላቸውን፡ካህናትና፡ሌዋውያን፡ በእግዚአብሔር፡ቤት፡አገልግሎት፡ላይ፡ሾመ።

19በማናቸውም፡ነገር፡ዅሉ፡ርኩስ፡የኾነ፡ሰው፡እንዳይገባ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡በር፡በረኛዎችን፡አኖረ።

20የመቶ፡አለቃዎችንም፥ከበርቴዎቹንም፥የሕዝቡንም፡አለቃዎች፥የአገሩንም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ ወሰደ፥ንጉሡንም፡ከእግዚአብሔር፡ቤት፡አወረደ፤በላይኛውም፡በር፡በኩል፡ወደንጉሡ፡ቤት፡ መጡ፥ንጉሡንም፡በመንግሥቱ፡ዙፋን፡ላይ፡አኖሩት።

21የአገሩም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ደስ፡አላቸው፥ከተማዪቱም፡ጸጥ፡አለች፤ጎቶሊያንም፡በሰይፍ፡ገደሏት።ች፡

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source