1ኢዮአስም፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የሰባት፡ዓመት፡ልጅ፡ነበረ፥በኢየሩሳሌምም፡አርባ፡ዓመት፡ ነገሠ፤እናቱም፡ሳብያ፡የተባለች፡የቤርሳቤሕ፡ሴት፡ነበረች።
2በካህኑም፡በዮዳዔ፡ዘመን፡ዅሉ፡ኢዮአስ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቅን፡ነገር፡አደረገ።
3ዮዳዔም፡ኹለት፡ሚስቶች፡አጋባው፤ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆችንም፡ወለደ።
4ከዚህም፡በዃላ፡ኢዮአስ፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ይጠግን፡ዘንድ፡ዐሰበ።
5ካህናትንና፡ሌዋውያንንም፡ሰብስቦ፦ወደይሁዳ፡ከተማዎች፡ውጡ፥የአምላካችኹንም፡ቤት፡በየዓመቱ፡ ለማደስ፡ከእስራኤል፡ዅሉ፡ገንዘብን፡ሰብስቡ፤ነገሩንም፡ፈጥናችኹ፡አድርጉ፡አላቸው።ሌዋውያን፡ግን፡ቸል፡ አሉ።
6ንጉሡም፡አለቃውን፡ዮዳዔን፡ጠርቶ፦የእግዚአብሔር፡ባሪያ፡ሙሴ፡ስለምስክሩ፡ድንኳን፡የእስራኤል፡ ጉባኤ፡እንዲያዋጣ፡ያዘዘውን፡ግብር፡ከይሁዳና፡ከኢየሩሳሌም፡ያመጡ፡ዘንድ፡ስለ፡ምን፡ሌዋውያንን፡ አላተጋኻቸውም፧አለው።
7ጎቶሊያ፡ከሓዲት፡ነበረችና፡ልጆቿም፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡አፍርሰዋልና፤በእግዚአብሔርም፡ቤት፡ ተቀድሶ፡የነበረውን፡ዅሉ፡ለበዓሊም፡ሰጥተዋልና።
8ንጉሡም፡አዘዘ፥ሣጥንም፡ሠርተው፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡በር፡አጠገብ፡በስተውጭ፡አኖሩት።
9የእግዚአብሔርም፡ባሪያ፡ሙሴ፡በምድረ፡በዳ፡በእስራኤል፡ላይ፡ያዘዘውን፡ግብር፡ለእግዚአብሔር፡ያመጡ፡ ዘንድ፡በይሁዳና፡በኢየሩሳሌም፡ዐዋጅ፡ነገሩ።
10አለቃዎቹና፡ሕዝቡም፡ዅሉ፡ደስ፡ብሏቸው፡አቀረቡት፥እስኪሞላም፡ድረስ፡በሣጥኑ፡ውስጥ፡ጣሉት።
11ሣጥኑም፡በሌዋውያን፡እጅ፡ወደንጉሡ፡ሹማምት፡በደረሰ፡ጊዜ፥ብዙ፡ገንዘብም፡እንዳለበት፡ባየ፡ ጊዜ፥የንጉሡ፡ጸሓፊና፡የዋነኛው፡ካህን፡ሹም፡እየመጡ፡ብሩን፡ከሣጥን፡ያወጡ፡ነበር፥ሣጥኑንም፡ደግሞ፡ ወደ፡ስፍራው፡ይመልሱት፡ነበር።እንዲሁም፡በየቀኑ፡ያደርጉ፡ነበር፥ብዙም፡ገንዘብ፡አከማቹ።
12ንጉሡና፡ዮዳዔም፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ሥራ፡ላይ፡ለተሾሙት፡ሰጧቸው፤እነርሱም፡የእግዚአብሔርን፡ ቤት፡የሚጠግኑትን፡ጠራቢዎችንና፡ዐናጢዎችን፥የእግዚአብሔርንም፡ቤት፡የሚያድሱትን፡የብረትና፡የናስ፡ ሠራተኛዎችን፡ይገዙበት፡ነበር።
13ሠራተኛዎችም፡ሠሩ፥የፈረሰውም፡በእጃቸው፡ተጠገነ፤የእግዚአብሔርንም፡ቤት፡እንደ፡ቀድሞው፡ሥራ፡ መለሱ፥አጽንተውም፡አቆሙት።
14በጨረሱም፡ጊዜ፡የተረፈውን፡ገንዘብ፡በንጉሡና፡በዮዳዔ፡ፊት፡አመጡ፤እነርሱም፡ለእግዚአብሔር፡ቤት፡ ዕቃ፥ለአገልግሎትና፡ለቍርባን፡ዕቃ፥ለጭልፋዎችም፥ለወርቅና፡ለብርም፡ዕቃ፡አደረጉት።በዮዳዔም፡ዘመን፡ ዅሉ፡ለእግዚአብሔር፡ቤት፡የሚቃጠል፡መሥዋዕት፡ዅልጊዜ፡ያቀርቡ፡ነበር። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
15ዮዳዔም፡ሸመገለ፥ዕድሜም፡ጠግቦ፡ሞተ፤በሞተ፡ጊዜ፡ዕድሜው፡መቶ፡ሠላሳ፡ዓመት፡ነበረ።
16ከእስራኤልም፡ጋራ፥ከእግዚአብሔርና፡ከቤቱም፡ጋራ፡ቸርነትን፡ሠርቷልና፥በዳዊት፡ከተማ፡ከነገሥታቱ፡ ጋራ፡ቀበሩት።
17ዮዳዔም፡ከሞተ፡በዃላ፡የይሁዳ፡አለቃዎች፡ገብተው፡ለንጉሡ፡እጅ፡ነሡ፤ንጉሡም፡ዕሺ፡አላቸው።
18የአባቶቻቸውንም፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡ትተው፡የማምለኪያ፡ዐጸዶችንና፡ጣዖታትን፡አመለኩ፤በዚህ፡ በደላቸውም፡ምክንያት፡በይሁዳና፡በኢየሩሳሌም፡ላይ፡ቍጣ፡ወረደ።
19ወደ፡እግዚአብሔርም፡ይመልሷቸው፡ዘንድ፡ነቢያትን፡ይሰድ፟ላቸው፡ነበር፤መሰከሩባቸውም፥እነርሱ፡ግን፡ አላደመጡም።
20የእግዚአብሔርም፡መንፈስ፡በካህኑ፡በዮዳዔ፡ልጅ፡በዘካርያስ፡ላይ፡መጣ፤ርሱም፡በሕዝቡ፡ፊት፡ ቆመና፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የእግዚአብሔርን፡ትእዛዝ፡ለምን፡ትተላለፋላችኹ፧መልካምም፡ አይኾንላችኹም፤እግዚአብሔርን፡ስለ፡ተዋችኹ፡ርሱ፡ትቷችዃል፡አላቸው።
21ተማማሉበትም፡በንጉሡም፡ትእዛዝ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡አደባባይ፡ውስጥ፡በድንጋይ፡ወገሩት።
22እንዲሁም፡ንጉሡ፡ኢዮአስ፡ዮዳዔ፡ያደረገለትን፡ቸርነት፡አላሰበም፥ልጁንም፡ዘካርያስን፡ አስገደለው፤ርሱም፡ሲሞት።እግዚአብሔር፡ይየው፥ይፈልገውም፡አለ።
23ዓመቱም፡ካለፈ፡በዃላ፡የሶርያውያን፡ሰራዊት፡መጡበት፤ወደ፡ይሁዳና፡ወደ፡ኢየሩሳሌምም፡መጥተው፡ ከሕዝቡ፡መካከል፡የሕዝቡን፡አለቃዎች፡ዅሉ፡አጠፉ፥ምርኳቸውንም፡ዅሉ፡ወደ፡ንጉሡ፡ወደ፡ደማስቆ፡ ላኩ።
24የሶርያውያንም፡ሰራዊት፡ቍጥር፡ጥቂት፡ኾኖ፡ሳለ፡እግዚአብሔር፡ታላቅን፡ሰራዊት፡አሳልፎ፡በእጃቸው፡ ሰጣቸው፤ይህም፡የኾነው፡የአባቶቻቸውን፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡ትተው፡ስለ፡ነበረ፡ነው።እነርሱም፡ በኢዮአስ፡ላይ፡ፍርድ፡ፈረዱበት።
25ከርሱም፡ዘንድ፡ዐልፈው፡ከኼዱ፡በዃላ፡እጅግ፡ታሞ፟፡ነበር፤የገዛ፡ባሪያዎቹም፡ስለ፡ካህኑ፡ስለዮዳዔ፡ ልጅ፡ተበቅለው፡ተማማሉበት፥በዐልጋውም፡ላይ፡ገደሉት፥ሞተም፤በዳዊት፡ከተማ፡እንጂ፡በነገሥታት፡ መቃብር፡አልቀበሩትም።
26የተማማሉበትም፡የአሞናዊቱ፡የሰምዓት፡ልጅ፡ዛባድ፥የሞዐባዊቱም፡የሰማሪት፡ልጅ፡ዮዛባት፡ነበሩ።
27የልጆቹና፡በርሱ፡ላይ፡የተደረገው፡ነገር፡የእግዚአብሔርንም፡ቤት፡ማደሱ፥እንሆ፥በነገሥታቱ፡መጽሐፍ፡ ተጽፏል።ልጁም፡አሜስያስ፡በርሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።