Skip to content
← 2 Chronicles

Chapter 26 · Amharic

2 Chronicles

1የይሁዳም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡የዐሥራ፡ስድስት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡የነበረውን፡ዖዝያንን፡ወስደው፡በአባቱ፡ በአሜስያስ፡ፋንታ፡አነገሡት።

2ንጉሡም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡ካንቀላፋ፡በዃላ፡ዖዝያን፡ኤላትን፡ሠራ፥ወደ፡ይሁዳም፡መለሳት።

3ዖዝያንም፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የዐሥራ፡ስድስት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፥በኢየሩሳሌምም፡ዐምሳ፡ ኹለት፡ዓመት፡ነገሠ፤እናቱም፡ይኮልያ፡የተባለች፡የኢየሩሳሌም፡ሴት፡ነበረች።

4አባቱም፡አሜስያስ፡እንዳደረገው፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቅን፡ነገር፡አደረገ።

5እግዚአብሔርንም፡መፍራት፡ባስተማረ፡በዘካርያስ፡ዘመን፡እግዚአብሔርን፡ይፈልግ፡ዘንድ፡ልብ፡ አደረገ፤እግዚአብሔርንም፡በፈለገ፡ጊዜ፡እግዚአብሔር፡ነገሩን፡አከናወነለት።

6ወጥቶም፡ከፍልስጥኤማውያን፡ጋራ፡ተዋጋ፥የጌትንና፡የየብናን፡የአዞጦንንም፡ቅጥር፡አፈረሰ፤በአዛጦንና፡ በፍልስጥኤማውያንም፡አገር፡ከተማዎችን፡ሠራ።

7እግዚአብሔርም፡በፍልስጥኤማውያንና፡በጉርበዓል፡በሚኖሩ፡ዐረባውያን፡በምዑናውያንም፡ላይ፡ረዳው።

8አሞናውያንም፡ለዖዝያን፡ገበሩ፤እጅግም፡በርትቶ፡ነበርና፥ዝናው፡እስከግብጽ፡መግቢያ፡ድረስ፡ተሰማ።

9ዖዝያንም፡በኢየሩሳሌም፡በማእዘኑ፡በርና፡በሸለቆው፡በር፡ቅጥሩም፡በዞረበት፡ማእዘን፡አጠገብ፡ግንቦችን፡ ሠርቶ፡መሸጋቸው።

10ብዙም፡እንስሳዎች፡ነበሩበትና፡በምድረ፡በዳና፡በቈላው፡በደጋውም፡ግንብ፡ሠራ፥ብዙ፡ጕድጓድም፡ ማሰ፤ደግሞም፡ዕርሻ፡ይወድ፟፡ነበርና፥በተራራማውና፡በፍሬያማው፡ስፍራ፡ዐራሾችና፡አትክልተኛዎች፡ነበሩት።

11ደግሞም፡ለዖዝያን፡በሰራዊት፡ውስጥ፡ሰልፈኛዎች፡ነበሩት፤በንጉሡ፡አለቃ፡በሐናንያ፡ትእዛዝ፡በአለቃው፡ በመዕሴያና፡በጸሓፊው፡በይዒኤል፡እጅ፡እንደ፡ተቈጠሩ፡ወደ፡ሰልፍ፡በየቍጥራቸው፡ይወጡ፡ነበር።

12የአባቶቻቸውም፡ቤቶች፡አለቃዎች፡የጽኑዓን፡ኀያላኑ፡ቍጥር፡ዅሉ፡ኹለት፡ሺሕ፡ስድስት፡መቶ፡ነበረ።

13ንጉሡንም፡በጠላቱ፡ላይ፡ያግዝ፡ዘንድ፥በታላቅ፡ኀይል፡ወደ፡ሰልፍ፡የሚወጣ፥ከእጃቸው፡በታች፡ የነበረ፡ሰራዊት፡ሦስት፡መቶ፡ሰባት፡ሺሕ፡ዐምስት፡መቶ፡ነበረ።

14ዖዝያንም፡ለጭፍራው፡ዅሉ፡ጋሻና፡ጦር፥ራስ፡ቍርና፡ጥሩር፥ቀስትና፡የሚወነጭፉትን፡ድንጋይ፡ አዘጋጀላቸው።

15በኢየሩሳሌምም፡በብልኀተኛዎች፡እጅ፡የተሠሩትን፥በግንብና፡በቅጥር፡ላይ፡የሚኖሩትን፥ፍላጻና፡መርግ፡ የሚወረወርባቸውን፡መሣሪያዎች፡አደረገ፤እስኪበረታም፡ድረስ፡እግዚአብሔር፡በድንቅ፡ረድቶታልና፥ዝናው፡ እስከ፡ሩቅ፡ድረስ፡ተሰማ።

16ነገር፡ግን፥በበረታ፡ጊዜ፡ለጥፋት፡ልቡ፡ታበየ፥አምላኩንም፡እግዚአብሔርን፡በደለ፤ወደ፡መቅደስ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ገብቶ፡በዕጣን፡መሠዊያ፡ላይ፡ዐጠነ።

17ካህኑም፡ዐዛርያስ፡ከርሱም፡ጋራ፡ጽኑዓን፡የነበሩ፡ሰማንያ፡የእግዚአብሔር፡ካህናት፡ተከትለው፡ገቡ።

18ንጉሡንም፡ዖዝያንን፡እየተቃወሙ፦ዖዝያን፡ሆይ፥ዕጣን፡ማጠን፡የተቀደሱት፡የአሮን፡ልጆች፡የካህናቱ፡ ሹመት፡ነው፡እንጂ፡ለእግዚአብሔር፡ታጥን፡ዘንድ፡ለአንተ፡አይገ፟ባ፟ኽም፤በድለኻልና፥ከመቅደሱ፡ ውጣ፤ከአምላክኽም፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ክብር፡አይኾንልኽም፡አሉት።

19ዖዝያንም፡ተቈጣ፤የሚያጥንበትም፡ጥና፡በእጁ፡ነበረ፤ካህናቱንም፡በተቈጣ፡ጊዜ፡በካህናቱ፡ፊት፡ በእግዚአብሔር፡ቤት፡ውስጥ፡በዕጣኑ፡መሠዊያ፡አጠገብ፡ሳለ፡በግንባሩ፡ላይ፡ለምጽ፡ታየ።

20ታላቁም፡ካህን፡ዐዛርያስ፡ካህናቱም፡ዅሉ፡ተመለከቱት፥እንሆም፥በግንባሩ፡ላይ፡ለምጽ፡ ነበረ፤ፈጥነውም፡አባረ፟ሩት፥ርሱም፡ደግሞ፡እግዚአብሔር፡ቀሥፎት፡ነበርና፥ይወጣ፡ዘንድ፡ቸኰለ።

21ንጉሡም፡ዖዝያን፡እስኪሞት፡ድረስ፡ለምጻም፡ነበረ፤ለምጻምም፡ኾኖ፡ከእግዚአብሔር፡ቤት፡ ተቈርጧልና፥በተለየ፡ቤት፡ይቀመጥ፡ነበር፤ልጁም፡ኢዮአታም፡በንጉሡ፡ቤት፡ላይ፡ኾኖ፡በምድሩ፡ሕዝብ፡ ላይ፡ይፈርድ፡ነበር።

22የቀረውንም፡የፊተኛውንና፡የዃለኛውን፡የዖዝያንን፡ነገር፡ነቢዩ፡የዓሞጽ፡ልጅ፡ኢሳይያስ፡ጽፎታል።

23ዖዝያንም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥ለምጻም፡ነው፡ብለውም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡በነገሥታቱ፡መቃብር፡ ዕርሻ፡ውስጥ፡ቀበሩት፤ልጁም፡ኢዮአታም፡በርሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source