1ኢዮአታምም፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የኻያ፡ዐምስት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፥በኢየሩሳሌምም፡ዐሥራ፡ ስድስት፡ዓመት፡ነገሠ፤እናቱም፡የሳዶቅ፡ልጅ፡ኢየሩሳ፡ትባል፡ነበር።
2አባቱም፡ዖዝያን፡እንዳደረገ፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቅን፡ነገር፡አደረገ፤ነገር፡ ግን፥ወደእግዚአብሔር፡መቅደስ፡አልገባም፤ሕዝቡም፡ገና፡ይበድል፡ነበር።
3የእግዚአብሔርን፡ቤት፡የላይኛውን፡በር፡ሠራ፥በዖፌልም፡ቅጥር፡ላይ፡እጅግ፡ሠራ።
4በተራራማውም፡በይሁዳ፡አገር፡ላይ፡ከተማዎችን፡ሠራ፥በዱር፡ስፍራዎችም፡ዐምባዎችንና፡ግንቦችን፡ሠራ።
5ከዐሞንም፡ልጆች፡ንጉሥ፡ጋራ፡ተዋጋ፡አሸነፋቸውም።በዚያም፡ዓመት፡የዐሞን፡ልጆች፡መቶ፡መክሊት፡ ብር፥ዐሥር፡ሺሕም፡የቈሬስ፡መስፈሪያ፡ስንዴ፥ዐሥር፡ሺሕም፡የቈሬስ፡መስፈሪያ፡ገብስ፡ ሰጡት።እንዲሁም፡ደግሞ፡የዐሞን፡ልጆች፡በኹለተኛውና፡በሦስተኛው፡ዓመት፡ሰጡት።
6ኢዮአታምም፡በአምላኩ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡መንገዱን፡አቅንቷልና፥በረታ።
7የቀረውም፡የኢዮአታም፡ነገር፥ሰልፉም፡ዅሉ፥ሥራውም፥እንሆ፥በእስራኤልና፡በይሁዳ፡ነገሥታት፡ መጽሐፍ፡ተጽፏል።
8መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የኻያ፡ዐምስት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፥በኢየሩሳሌምም፡ዐሥራ፡ስድስት፡ ዓመት፡ነገሠ።
9ኢዮአታምም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በዳዊትም፡ከተማ፡ቀበሩት፤ልጁም፡አካዝ፡በርሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።