1አካዝ፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የኻያ፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፥በኢየሩሳሌምም፡ዐሥራ፡ስድስት፡ዓመት፡ ነገሠ፤እንደ፡አባቱም፡እንደ፡ዳዊት፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቅን፡ነገር፡አላደረገም።
2ነገር፡ግን፥በእስራኤል፡ነገሥታት፡መንገድ፡ኼደ፥ደግሞም፡ለበዓሊም፡ቀልጠው፡የተሠሩትን፡ምስሎችን፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ሠራ።
3ደግሞም፡በሄኖም፡ልጅ፡ሸለቆ፡ውስጥ፡ዐጠነ፤እግዚአብሔር፡ከእስራኤል፡ልጆች፡ፊት፡እንዳሳደዳቸው፡ እንደ፡አሕዛብም፡ክፉ፡ልማድ፡ልጆቹን፡በእሳት፡አቃጠለ።
4በኰረብታው፡መስገጃዎችና፡በተራራዎች፡ላይ፡በለመለመውም፡ዛፍ፡ዅሉ፡በታች፡ይሠዋና፡ያጥን፡ነበር።
5ስለዚህ፥አምላኩ፡እግዚአብሔር፡በሶርያ፡ንጉሥ፡እጅ፡አሳልፎ፡ሰጠው፤ሶርያውያንም፡መቱት፥ከርሱም፡ ብዙ፡ምርኮኛዎች፡ወስደው፡ወደ፡ደማስቆ፡አመጡ።ደግሞም፡በእስራኤል፡ንጉሥ፡እጅ፡አሳልፎ፡ ሰጠው፤ርሱም፡በታላቅ፡አመታት፡መታው።
6የአባቶቻቸውንም፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡ትተው፡ነበርና፥የሮሜልዩ፡ልጅ፡ፋቁሔ፡ባንድ፡ቀን፡ከይሁዳ፡ መቶ፡ኻያ፡ሺሕ፡ገደለ፤ዅሉም፡ጽኑዓን፡ነበሩ።
7ከኤፍሬምም፡ወገን፡የነበረው፡ኀያል፡ሰው፡ዝክሪ፡የንጉሡን፡ልጅ፡መዕሴያንና፡የቤቱን፡አዛዥ፡ ዐዝሪቃምን፥ለንጉሡም፡በማዕርግ፡ኹለተኛ፡የኾነውን፡ሕልቃናን፡ገደለ።
8የእስራኤል፡ልጆች፡ከወንድሞቻቸው፡ኹለት፡መቶ፡ሺሕ፡ሴቶችን፥ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆችንም፡ ማረኩ፥እጅግም፡ምርኮ፡ከነርሱ፡ወስደው፡ወደ፡ሰማርያ፡አገቡ።
9በዚያም፡ዖዴድ፡የተባለ፡የእግዚአብሔር፡ነቢይ፡ነበረ፤ወደ፡ሰማርያም፡የሚመጣውን፡ጭፍራ፡ሊገናኘው፡ ወጣ፥እንዲህም፡አላቸው፦እንሆ፥የአባቶቻችኹ፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ይሁዳን፡ስለ፡ተቈጣ፡በእጃችኹ፡ አሳልፎ፡ሰጣቸው፥እናንተም፡ወደ፡ሰማይ፡በሚደርስ፡ቍጣ፡ገደላችዃቸው።
10አኹንም፡የይሁዳንና፡የኢየሩሳሌም፡ልጆች፡ባሪያዎች፡ኾነው፡ይገዙላችኹ፡ዘንድ፡ታስባላችኹ፤ነገር፡ ግን፥አምላካችኹን፡እግዚአብሔርን፡የበደላችኹት፡በደል፡በእናንተ፡ዘንድ፡የለምን፧
11አኹንም፡ስሙኝ፤የእግዚአብሔር፡ቍጣ፡በላያችኹ፡ነዷ፟ልና፥ከወንድሞቻችኹ፡የወሰዳችዃቸውን፡ ምርኮኛዎች፡መልሱ።
12ደግሞም፡ከኤፍሬም፡ልጆች፡አለቃዎች፡የዮሐናን፡ልጅ፡ዐዛርያስ፥የምሺሌሞትም፡ልጅ፡ በራክያ፥የሰሎምም፡ልጅ፡ይሒዝቅያ፥የሐድላይም፡ልጅ፡ዓሜሳይ፡ከሰልፍ፡በተመለሱት፡ላይ፡ተቃወሟቸው።
13ደግሞም፦በእግዚአብሔር፡ፊት፡በእኛ፡ላይ፡በደል፡ታመጡብናላችኹና፥ኀጢአታችንንና፡በደላችንን፡ ታበዙብናላችኹና፡የተማረኩትን፡ወደዚህ፡አታግቡ፤በደላችን፡ታላቅ፡ነውና፥የመቅሠፍቱም፡ቍጣ፡በእስራኤል፡ ላይ፡ነውና፥አሏቸው።
14ሰልፈኛዎቹም፡ምርኮኛዎቹንና፡ምርኮውን፡በአለቃዎችና፡በጉባኤ፡ዅሉ፡ፊት፡ተዉ።
15በስማቸውም፡የተጻፉ፡ሰዎች፡ተነሥተው፡ምርኮኛዎቹን፡ወሰዱ፥በመካከላቸውም፡ዕራቍታቸውን፡ለነበሩት፡ ዅሉ፡ከምርኮው፡አለበሷቸው፥አጐናጸፏቸውም፥ጫማም፡በእግራቸው፡ አደረጉላቸው፥መገቧቸውም፥አጠጧቸውም፥ቀቧቸውም፤ደካማዎቹንም፡ዅሉ፡በአህያዎች፡ላይ፡ አስቀመጧቸው፥ዘንባባም፡ወዳለበት፡ከተማ፡ወደ፡ኢያሪኮ፡ወደ፡ወንድሞቻቸው፡አመጧቸው፤ወደ፡ሰማርያም፡ ተመለሱ።
16በዚያን፡ጊዜም፡ንጉሡ፡አካዝ፡ርዳታ፡ፈልጎ፡ወደአሶር፡ንጉሥ፡ላከ፤
17የኤዶምያስ፡ሰዎች፡ዳግመኛ፡መጥተው፥ይሁዳንም፡መትተው፡ብዙ፡ምርኮኛ፡ወስደው፡ነበርና።
18ደግሞም፡ፍልስጥኤማውያን፡በቈላውና፡በደቡብ፡በኩል፡ባሉት፡በይሁዳ፡ከተማዎች፡አደጋ፡ጥለው፡ ነበር፤ቤትሳሚስንና፡ኤሎንን፥ግዴሮትንም፥ሦኮንና፡መንደሮቿን፥ተምናንና፡መንደሮቿን፥ጊምዞንና፡ መንደሮቿን፡ወስደው፡በዚያ፡ተቀምጠው፡ነበር።
19የይሁዳም፡ንጉሥ፡አካዝ፡እግዚአብሔርን፡ክዷልና፥ከርሱም፡እጅግ፡ርቋልና፥እግዚአብሔር፡ስለ፡ርሱ፡ ይሁዳን፡አዋረደው። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
20የአሶርም፡ንጉሥ፡ቴልጌልቴልፌልሶር፡መጥቶ፡አስጨነቀው፡እንጂ፡አልረዳውም።
21አካዝም፡ከእግዚአብሔር፡ቤት፡ከንጉሡና፡ከአለቃዎቹም፡ቤት፡እኩሌታውን፡ገፈፈ፥ለአሶርም፡ንጉሥ፡ ሰጠ፤ነገር፡ግን፥አንዳች፡አልተጠቀመበትም።
22ይህም፡ንጉሥ፡አካዝ፡በተጨነቀ፡ጊዜ፡እግዚአብሔርን፡መበደል፡አበዛ።
23ለመቱትም፡ለደማስቆ፡አማልክት፦የሶርያን፡ነገሥታት፡አማልክት፡ረድተዋቸዋልና፥እኔን፡ይረዱ፡ዘንድ፡ እሠዋላቸዋለኹ፡ብሎ፡ሠዋላቸው።ነገር፡ግን፥ለርሱና፡ለእስራኤል፡ዅሉ፡እንቅፋት፡ኾኑ።
24አካዝም፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ዕቃዎች፡ዅሉ፡ወስዶ፡ሰባበራቸው፥የእግዚአብሔርንም፡ቤት፡ደጅ፡ ቈለፈ፤በኢየሩሳሌምም፡ማእዘን፡ዅሉ፡መሠዊያ፡ሠራ።
25በይሁዳም፡ከተማዎች፡ዅሉ፡ለሌላዎች፡አማልክት፡ያጥን፡ዘንድ፡የኰረብታ፡መስገጃዎች፡ አሠራ፤የአባቶቹንም፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡አስቈጣ።
26የቀረውም፡ነገርና፡ሥራው፡ዅሉ፥የፊተኛውና፡የዃለኛው፥እንሆ፥በይሁዳና፡በእስራኤል፡ነገሥታት፡ መጽሐፍ፡ተጽፏል።
27አካዝም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በከተማዪቱም፡በኢየሩሳሌም፡ቀበሩት፤ነገር፡ግን፥ወደእስራኤል፡ ነገሥታት፡መቃብር፡አላገቡትም፤ልጁም፡ሕዝቅያስ፡በርሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።