Skip to content
← 2 Chronicles

Chapter 29 · Amharic

2 Chronicles

1ሕዝቅያስም፡የኻያ፡ዐምስት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡በነበረ፡ጊዜ፡መንገሥ፡ዠመረ፥በኢየሩሳሌም፡ኻያ፡ዘጠኝ፡ ዓመት፡ነገሠ፤እናቱም፡የዘካርያስ፡ልጅ፡አቡ፡ትባል፡ነበር።

2አባቱም፡ዳዊት፡እንዳደረገ፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቅን፡ነገር፡አደረገ።

3በነገሠም፡በመዠመሪያው፡ዓመት፡በመዠመሪያው፡ወር፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ደጆች፡ ከፈተ፥ዐደሳቸውም።

4ካህናቱንና፡ሌዋውያኑንም፡አስመጣ፥በምሥራቅ፡በኩል፡ባለው፡አደባባይም፡ሰበሰባቸው፥

5እንዲህም፡አላቸው፦ሌዋውያን፡ሆይ፥ስሙኝ፤ተቀደሱ፥የአባቶቻችኹንም፡አምላክ፡የእግዚአብሔርን፡ ቤት፡ቀድሱ፤ርኩሱን፡ነገር፡ዅሉ፡ከመቅደሱ፡አስወግዱ።

6አባቶቻችን፡ተላልፈዋል፥በአምላካችንም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡አድርገዋል፤ርሱንም፡ ትተዋል፥ፊታቸውንም፡ከእግዚአብሔር፡መኖሪያ፡መልሰዋል፥

7ወደ፡ርሷም፡ዠርባቸውን፡አዙረዋል፤ደግሞም፡የወለሉን፡ደጆች፡ቈልፈዋል፥መብራቶቹንም፡ አጥፍተዋል፥በመቅደሱም፡ውስጥ፡ለእስራኤል፡አምላክ፡አላጠኑም፥የሚቃጠለውንም፡መሥዋዕት፡አላቀረቡም።

8ስለዚህም፡የእግዚአብሔር፡ቍጣ፡በይሁዳና፡በኢየሩሳሌም፡ላይ፡ኾነ፥በዐይናችኹም፡እንደምታዩ፡ ለድንጋጤና፡ለመደነቂያ፡ለመዘበቻም፡አሳልፎ፡ሰጣቸው።

9እንሆም፥ስለዚህ፡አባቶቻችን፡በሰይፍ፡ወደቁ፥ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆቻችንም፡ሚስቶቻችንም፡ተማረኩ።

10አኹንም፡የቍጣው፡ጽናት፡ከእኛ፡እንዲመለስ፡ከእስራኤል፡አምላክ፡ከእግዚአብሔር፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡ ኣደርግ፡ዘንድ፡በልቤ፡ዐስቤያለኹ።

11ልጆቼ፡ሆይ፥በፊቱ፡ትቆሙና፡ታገለግሉት፡ዘንድ፥አገልጋዮቹም፡ትኾኑ፡ዘንድ፥ታጥኑለትም፡ዘንድ፡ እግዚአብሔር፡መርጧችዃልና፥ቸል፡አትበሉ።

12ሌዋውያኑም፥ከቀአት፡ልጆች፡የዐማሲ፡ልጅ፡መሐትና፡የዐዛርያስ፡ልጅ፡ኢዮኤል፥ከሜራሪም፡ልጆች፡ የዐብዲ፡ልጅ፡ቂስና፡የይሃሌልኤል፡ልጅ፡ዐዛርያስ፥ከጌድሶንም፡ልጆች፡የዛማት፡ልጅ፡ዩአክና፡የዩአክ፡ልጅ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ዔዴን፥

14ከኤሊጸፋንም፡ልጆች፡ሺምሪና፡ይዒኤል፥ከአሣፍም፡ልጆች፡ዘካርያስና፡መታንያ፥ከኤማንም፡ልጆች፡ ይሒኤልና፡ሰሜኢ፥ከኤዶታምም፡ልጆች፡ሸማያና፡ዑዝኤል፡ተነሡ።

15ወንድሞቻቸውንም፡ሰብስበው፡ተቀደሱ፤በእግዚአብሔር፡ቃል፡እንደመጣው፡እንደ፡ንጉሡ፡ትእዛዝ፡ የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ያነጹ፡ዘንድ፡ገቡ።

16ካህናቱም፡ያነጹት፡ዘንድ፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ወደ፡ውስጡ፡ገቡ፥በእግዚአብሔርም፡መቅደስ፡ ያገኙትን፡ርኩስ፡ነገር፡ዅሉ፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡አደባባይ፡አወጡት።ሌዋውያንም፡ወስደው፡ወደ፡ሜዳ፡ ወደ፡ቄድሮን፡ወንዝ፡ጣሉት።

17በመዠመሪያውም፡ወር፡በመዠመሪያው፡ቀን፡ይቀደሱ፡ዠመር፥በዚያውም፡ወር፡በስምንተኛው፡ቀን፡ ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ወለል፡ደረሱ፤የእግዚአብሔርንም፡ቤት፡በስምንት፡ቀን፡ቀደሱ፥በመዠመሪያውም፡ ወር፡በዐሥራ፡ስድስተኛው፡ቀን፡ፈጸሙ።

18ወደ፡ውስጡም፡ወደ፡ንጉሡ፡ወደ፡ሕዝቅያስ፡ገብተው፦የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ዅሉ፥ለሚቃጠል፡ መሥዋዕት፡የሚኾነውን፡መሠዊያና፡ዕቃውንም፡ዅሉ፥የገጹንም፡ኅብስት፡ገበታና፡ዕቃውን፡ዅሉ፡አንጽተናል፤

19ንጉሡም፡አካዝ፡ነግሦ፡ሳለ፡በመተላለፍ፡ያረከሰውን፡ዕቃ፡ዅሉ፡አዘጋጅተናል፡ ቀድሰናልም፤እንሆም፥በእግዚአብሔር፡መሠዊያ፡ፊት፡ኾነዋል፡አሉት።

20ንጉሡም፡ሕዝቅያስ፡ማልዶ፡ተነሣ፡የከተማዪቱንም፡አለቃዎች፡ሰበሰበ፥ወደእግዚአብሔርም፡ቤት፡ወጣ።

21ስለ፡መንግሥቱና፡ስለ፡መቅደሱም፡ስለ፡ይሁዳም፡ሰባት፡ወይፈኖች፥ሰባትም፡አውራ፡በጎች፥ሰባትም፡ የበግ፡ጠቦቶች፥ሰባትም፡አውራ፡ፍየሎች፡ለኀጢአት፡መሥዋዕት፡አመጡ።የአሮንንም፡ልጆች፡ ካህናቱን፦በእግዚአብሔር፡መሠዊያ፡ላይ፡አሳርጓቸው፡አላቸው።

22ወይፈኖቹንም፡ዐረዱ፥ካህናቱም፡ደሙን፡ተቀብለው፡በመሠዊያው፡ላይ፡ረጩት፤አውራ፡በጎቹንም፡ ዐረዱ፥ደሙንም፡በመሠዊያው፡ላይ፡ረጩት፤ጠቦቶቹንም፡ዐረዱ፡ደሙንም፡በመሠዊያው፡ላይ፡ረጩት።

23የኀጢአትም፡መሥዋዕት፡የሚኾኑትን፡አውራ፡ፍየሎች፡በንጉሡና፡በጉባኤው፡ፊት፡ አቀረቡ፥እጃቸውንም፡ጫኑባቸው፥ካህናቱም፡አረዷቸው፤

24ንጉሡም፡የሚቃጠል፡መሥዋዕትና፡የኀጢአት፡መሥዋዕት፡ለእስራኤል፡ዅሉ፡እንዲደረግ፡አዞ፟፡ ነበርና፥ለእስራኤል፡ዅሉ፡ማስተስረያ፡ያደርጉ፡ዘንድ፡የኀጢአቱን፡መሥዋዕት፡ደም፡በመሠዊያው፡ላይ፡ አቀረቡ።

25ይህንም፡ትእዛዝ፡እግዚአብሔር፡በነቢያቱ፡እጅ፡አዟ፟ልና፥እንደ፡ዳዊትና፡እንደ፡ንጉሡ፡ባለራእይ፡እንደ፡ ጋድ፥እንደ፡ነቢዩም፡እንደ፡ናታን፡ትእዛዝ፥ጸናጽልና፡በገና፡መሰንቆም፡አስይዞ፡ሌዋውያንን፡በእግዚአብሔር፡ ቤት፡አቆመ።

26ሌዋውያንም፡የዳዊትን፡የዜማ፡ዕቃ፡ይዘው፥ካህናቱም፡መለከቱን፡ይዘው፡ቆመው፡ነበር።

27ሕዝቅያስም፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕት፡በመሠዊያው፡ላይ፡ያሳርጉ፡ዘንድ፡አዘዘ፤የሚቃጠለውም፡ መሥዋዕት፡ማረግ፡በተዠመረ፡ጊዜ፡የእግዚአብሔር፡መዝሙር፡ደግሞ፡ተዠመረ፥መለከቱም፡ ተነፋ፥የእስራኤልም፡ንጉሥ፡የዳዊት፡ዜማ፡ዕቃ፡ተመታ።

28ጉባኤውም፡ዅሉ፡ሰገዱ፥መዘምራኑም፡ዘመሩ፥መለከተኛዎችም፡ነፉ፤የሚቃጠለው፡መሥዋዕት፡ እስኪፈጸም፡ድረስ፡ይህ፡ዅሉ፡ኾነ።

29ማቅረቡንም፡በፈጸሙ፡ጊዜ፡ንጉሡና፡ከርሱ፡ጋራ፡የነበሩ፡ዅሉ፡አጐነበሱ፡ሰገዱም።

30ንጉሡም፡ሕዝቅያስና፡አለቃዎቹ፡ሌዋውያንን፡በዳዊትና፡በባለራእዩ፡በአሣፍ፡ቃል፡እግዚአብሔርን፡ ያመሰግኑ፡ዘንድ፡አዘዙ።በደስታም፡አመሰገኑ፥አጐነበሱም፡ሰገዱም። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

31ሕዝቅያስም፦አኹን፡ለእግዚአብሔር፡ተቀድሳችዃል፤ቅረቡ፥መሥዋዕቱንና፡የምስጋናውን፡መሥዋዕት፡ ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡አምጡ፡ብሎ፡ተናገረ።ጉባኤውም፡መሥዋዕቱንና፡የምስጋናውን፡መሥዋዕት፡ አመጡ፤ልባቸውም፡የፈቀደ፡ዅሉ፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕት፡አመጡ።

32ጉባኤውም፡ያመጡት፡የሚቃጠል፡መሥዋዕት፡ቍጥር፡ሰባ፡ወይፈን፥መቶም፡አውራ፡በጎች፥ኹለት፡ መቶም፡የበግ፡ጠቦቶች፡ነበረ፤ይህ፡ዅሉ፡ለእግዚአብሔር፡የሚቃጠል፡መሥዋዕት፡ነበረ።

33የተቀደሱትም፡ቍጥር፡ስድስት፡መቶ፡በሬዎች፡ሦስት፡ሺሕም፡በጎች፡ነበረ።

34ነገር፡ግን፥ካህናቱ፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕት፡ለመግፈፍ፡ጥቂቶች፡ነበሩ፤ስለዚህም፡ሌዋውያን፡በቅን፡ ልብ፡ከካህናት፡ይልቅ፡ይቀደሱ፡ነበርና፥ሥራው፡እስኪፈጸም፡ድረስ፥ካህናቱም፡እስኪቀደሱ፡ድረስ፡ ወንድሞቻቸው፡ሌዋውያን፡ያግዟቸው፡ነበር።

35የሚቃጠለውም፡መሥዋዕት፡የደኅንነቱም፡መሥዋዕት፡ስብ፥ከሚቃጠለውም፡መሥዋዕት፡ዅሉ፡ጋራ፡ የሚቀርበው፡የመጠጥ፡ቍርባን፥ብዙ፡ነበረ።እንዲሁም፡የእግዚአብሔር፡ቤት፡አገልግሎት፡ተዘጋጀ።

36ሕዝቅያስና፡ሕዝቡም፡ዅሉ፡እግዚአብሔር፡ለሕዝቡ፡ስላዘጋጀው፡ነገር፡ደስ፡አላቸው።ይህም፡ነገር፡ በድንገት፡ተደረገ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source