1ለእስራኤልም፡አምላክ፡ለእግዚአብሔር፡ፋሲካ፡ያደርጉ፡ዘንድ፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ እንዲመጡ፡ሕዝቅያስ፡ወደ፡እስራኤልና፡ወደ፡ይሁዳ፡ዅሉ፡ላከ፥ደግሞም፡ወደ፡ኤፍሬምና፡ወደ፡ምናሴ፡ ደብዳቤ፡ጻፈ።
3ካህናቱም፡በሚበቃ፡ቍጥር፡ስላልተቀደሱ፥ሕዝቡም፡ገና፡በኢየሩሳሌም፡ስላልተሰበሰቡ፡በጊዜው፡ ያደርጉት፡ዘንድ፡አልቻሉምና፡ንጉሡና፡አለቃዎቹ፡የኢየሩሳሌምም፡ጉባኤ፡ዅሉ፡በኹለተኛው፡ወር፡ፋሲካውን፡ ያደርጉ፡ዘንድ፡ተመካክረው፡ነበር።
4ነገሩም፡ለንጉሡና፡ለጉባኤው፡ዅሉ፡ዐይን፡መልካም፡ነበረ።
5እንደ፡ተጻፈም፡በብዙ፡ቍጥር፡አላደረጉም፡ነበርና፥የእስራኤልን፡አምላክ፡የእግዚአብሔርን፡ፋሲካ፡ በኢየሩሳሌም፡ያደርጉ፡ዘንድ፡እንዲመጡ፡ከቤርሳቤሕ፡ዠምሮ፡እስከ፡ዳን፡ድረስ፡ለእስራኤል፡ዅሉ፡ዐዋጅ፡ እንዲነገር፡ወሰኑ።
6እንደ፡ንጉሡም፡ትእዛዝ፡መልክተኛዎቹ፡እንዲህ፡የሚለውን፡የንጉሡንና፡የአለቃዎቹን፡ደብዳቤ፡ይዘው፡ ወደ፡እስራኤልና፡ወደ፡ይሁዳ፡ዅሉ፡ኼዱ።የእስራኤል፡ልጆች፡ሆይ፥እግዚአብሔር፡ከአሶር፡ነገሥታት፡እጅ፡ ወዳመለጠ፡ቅሬታችኹ፡እንዲመለስ፡ወደአብርሃምና፡ወደይሥሐቅ፡ወደእስራኤልም፡አምላክ፡ተመለሱ።
7እናንተም፡እንደምታዩ፡የተፈቱ፡እስኪያደርጋቸው፡ድረስ፡የአባቶቻቸውን፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡እንደ፡ በደሉ፡እንደ፡አባቶቻችኹና፡እንደ፡ወንድሞቻችኹ፡አትኹኑ።
8አባቶቻችኹም፡እንደ፡ነበሩ፡ዐንገተ፡ደንዳና፡አትኹኑ፤እጃችኹንም፡ለእግዚአብሔር፡ስጡ፥ለዘለዓለም፡ ወደተቀደሰው፡ወደ፡መቅደሱም፡ግቡ፥ጽኑ፡ቍጣውም፡ከእናንተ፡እንዲመለስ፡አምላካችኹን፡እግዚአብሔርን፡ አምልኩ።
9አምላካችኹም፡እግዚአብሔር፡ቸርና፡መሓሪ፡ነውና፥ወደ፡ርሱም፡ብትመለሱ፡ፊቱን፡ከእናንተ፡አያዞርምና፡ ወደ፡እግዚአብሔር፡ብትመለሱ፡ወንድሞቻችኹና፡ልጆቻችኹ፡በማረኳቸው፡ፊት፡ምሕረትን፡ ያገኛሉ፥ደግሞም፡ወደዚች፡ምድር፡ይመለሳሉ።
10መልእክተኛዎቹም፡ከከተማ፡ወደ፡ከተማ፡በኤፍሬምና፡በምናሴ፡አገር፡እስከ፡ዛብሎን፡ኼዱ፤እነዚያ፡ ግን፡በንቀት፡ሣቁባቸው፥አፌዙባቸውም።
11ነገር፡ግን፥ከአሴርና፡ከምናሴ፡ከዛብሎንም፡ዐያሌ፡ሰዎች፡ሰውነታቸውን፡አዋረዱ፥ወደ፡ኢየሩሳሌምም፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org መጡ።
12ደግሞም፡አንድ፡ልብ፡ይሰጣቸው፡ዘንድ፥በእግዚአብሔርም፡ቃል፡የኾነውን፡የንጉሡንና፡የአለቃዎቹን፡ ትእዛዝ፡ያደርጉ፡ዘንድ፡የእግዚአብሔር፡እጅ፡በይሁዳ፡ላይ፡ኾነ።
13በኹለተኛውም፡ወር፡የቂጣውን፡በዓል፡ያደርግ፡ዘንድ፡እጅግ፡ታላቅ፡ጉባኤ፡የኾነ፡ሕዝብ፡በኢየሩሳሌም፡ ተከማቸ።
14ተነሥተውም፡በኢየሩሳሌም፡የነበሩትን፡መሠዊያዎችና፡ለጣዖታት፡የሚያጥኑበትን፡ዕቃ፡ዅሉ፡ አስወገዱ፥በቄድሮንም፡ወንዝ፡ጣሉት።
15በኹለተኛውም፡ወር፡በዐሥራ፡አራተኛው፡ቀን፡ፋሲካውን፡ዐረዱ፤ካህናቱና፡ሌዋውያኑም፡ ዐፈሩ፥ተቀደሱም፥ወደእግዚአብሔርም፡ቤት፡የሚቃጠል፡መሥዋዕት፡አመጡ።
16እንደእግዚአብሔርም፡ሰው፡እንደ፡ሙሴ፡ሕግ፡በሥርዐታቸው፡ቆሙ፤ካህናቱም፡ከሌዋውያን፡እጅ፡ የተቀበሉትን፡ደም፡ይረጩ፡ነበር።
17በጉባኤውም፡ያልተቀደሱ፡እጅግ፡ሰዎች፡ነበሩ፤ስለዚህም፡ሌዋውያን፡ለእግዚአብሔር፡ይቀድሷቸው፡ዘንድ፡ ንጹሓን፡ላልኾኑት፡ዅሉ፡ፋሲካውን፡ያርዱላቸው፡ነበር።
18እንደ፡ትእዛዙም፡ሳይኾን፡ከኤፍሬምና፡ከምናሴ፡ከይሳኮርና፡ከዛብሎንም፡ወገን፡እጅግ፡ሰዎች፡ሳይነጹ፡ ፋሲካውን፡በሉ።
19ሕዝቅያስም፦ምንም፡እንደ፡መቅደሱ፡ማንጻት፡ባይነጻ፡የአባቶቹን፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡ለመፈለግ፡ ልቡን፡የሚያቀናውን፡ዅሉ፡ቸሩ፡እግዚአብሔር፡ይቅር፡ይበለው፡ብሎ፡ስለ፡እነርሱ፡ጸለየ።
20እግዚአብሔርም፡ሕዝቅያስን፡ሰማው፥ሕዝቡንም፡ፈወሰ።
21በኢየሩሳሌምም፡ተገኝተው፡የነበሩ፡የእስራኤል፡ልጆች፡የቂጣውን፡በዓል፡በታላቅ፡ደስታ፡ሰባት፡ቀን፡ አደረጉ፤ሌዋውያኑና፡ካህናቱም፡በዜማ፡ዕቃ፡ለእግዚአብሔር፡እየዘመሩ፡ዕለት፡ዕለት፡እግዚአብሔርን፡ ያመሰግኑ፡ነበር።
22ሕዝቅያስም፡በእግዚአብሔር፡አገልግሎት፡አስተዋዮች፡የነበሩትን፡ሌዋውያንን፡ዅሉ፡ያጽናና፡ ነበር።የደኅንነትንም፡መሥዋዕት፡እያቀረቡ፥የአባቶቻቸውንም፡አምላክ፡እያመሰገኑ፡ሰባት፡ቀን፡በዓል፡አደረጉ።
24የይሁዳም፡ንጉሥ፡ሕዝቅያስ፡ስለ፡ቍርባን፡ሺሕ፡ወይፈኖችና፡ሰባት፡ሺሕ፡በጎች፡ለጉባኤው፡ ሰጥቶ፡ነበርና፥አለቃዎቹም፡ሺሕ፡ወይፈኖችና፡ዐሥር፡ሺሕ፡በጎች፡ለጉባኤው፡ሰጥተው፡ነበርና፥ከካህናቱም፡ እጅግ፡ብዙ፡ተቀድሰው፡ነበርና፥ጉባኤው፡ዅሉ፡እንደ፡ገና፡ሰባት፡ቀን፡በዓል፡ያደርጉ፡ዘንድ፡ ተማከሩ፤በደስታም፡እንደ፡ገና፡ሰባት፡ቀን፡በዓል፡አደረጉ።
25የይሁዳም፡ጉባኤ፡ዅሉ፥ካህናቱና፡ሌዋውያኑ፥ከእስራኤልም፡የመጡ፡ጉባኤ፡ዅሉ፥ከእስራኤልም፡አገር፡ የመጡትና፡በይሁዳ፡የኖሩት፡እንግዳዎች፡ደስ፡አላቸው።
26በኢየሩሳሌምም፡ታላቅ፡ደስታ፡ኾነ፤ከእስራኤል፡ንጉሥ፡ከዳዊት፡ልጅ፡ከሰሎሞን፡ዘመን፡ዠምሮ፡ እንደዚህ፡ያለ፡በዓል፡በኢየሩሳሌም፡አልተደረገም፡ነበር።
27ካህናቱና፡ሌዋውያኑም፡ተነሥተው፡ሕዝቡን፡ባረኩ፤ድምፃቸውም፡ተሰማ፥ጸሎታቸውም፡ወደ፡ቅዱስ፡ መኖሪያው፡ወደ፡ሰማይ፡ዐረገ።