1ይህም፡ዅሉ፡በተፈጸመ፡ጊዜ፡በዚያ፡የተገኙ፡እስራኤል፡ዅሉ፡ወደይሁዳ፡ከተማዎች፡ወጥተው፡ዅሉን፡ ፈጽመው፡እስካጠፏቸው፡ድረስ፡ሐውልቶቹን፡ሰባበሩ፥የማምለኪያ፡ዐጸዶቹንም፡ቈረጡ፥በይሁዳና፡ በብንያምም፡ዅሉ፡ደግሞም፡በኤፍሬምና፡በምናሴ፡የነበሩትን፡የኰረብታው፡መስገጃዎችና፡መሠዊያዎች፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org አፈረሱ።የእስራኤልም፡ልጆች፡ዅሉ፡ወደ፡ርስታቸውና፡ወደ፡ከተማዎቻቸው፡ተመለሱ።
2ሕዝቅያስም፡የካህናትንና፡የሌዋውያንን፡ሰሞን፡በየክፍላቸውና፡በያገልግሎታቸው፡አቆመ፤በእግዚአብሔር፡ ቤት፡አደባባይ፡በሮች፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕትና፡የደኅንነቱን፡መሥዋዕት፡ያቀርቡ፡ዘንድ፥ያገለግሉም፡ ዘንድ፥ያመሰግኑም፡ያከብሩም፡ዘንድ፡ካህናቱንና፡ሌዋውያኑን፡አቆመ።
3በእግዚአብሔርም፡ሕግ፡እንደ፡ተጻፈ፡በጧትና፡በማታ፥በሰንበታቱም፥በመባቻዎቹም፥በበዓላትም፡ ለሚቀርበው፡ለሚቃጠለው፡መሥዋዕት፡ንጉሡ፡ከገንዘቡ፡የሚከፍለውን፡ወሰነ።
4በእግዚአብሔርም፡ቤት፡ለአገልግሎት፡እንዲጸኑ፡ለካህናቱና፡ለሌዋውያን፡ክፍላቸውን፡ይሰጡ፡ዘንድ፡ በኢየሩሳሌም፡የሚኖሩትን፡ሕዝብ፡አዘዘ።
5ይህንም፡ነገር፡እንዳዘዘ፡የእስራኤል፡ልጆች፡የእኽሉንና፡የወይኑን፡ጠጅ፡የዘይቱንና፡ የማሩንም፥የዕርሻውንም፡ፍሬ፡ዅሉ፡በኵራት፡ሰጡ፤የዅሉንም፡ዓሥራት፡አብዝተው፡አቀረቡ።
6በይሁዳም፡ከተማዎች፡የሚኖሩ፡የእስራኤልና፡የይሁዳ፡ልጆች፡የበሬውንና፡የበጉን፡ ዓሥራት፥ለአምላካቸውም፡ለእግዚአብሔር፡የተቀደሰውን፡ዓሥራት፡አመጡ፥ከምረውም፡አኖሩት።
7በሦስተኛው፡ወር፡መከመር፡ዠመሩ፤በሰባተኛውም፡ወር፡ጨረሱ።
8ሕዝቅያስና፡አለቃዎቹም፡መጥተው፡ክምሩን፡ባዩ፡ጊዜ፡እግዚአብሔርና፡ሕዝቡን፡እስራኤልን፡ባረኩ።
9ሕዝቅያስም፡ካህናቱንና፡ሌዋውያኑን፡ስለ፡ክምሩ፡ጠየቀ።
10ከሳዶቅም፡ወገን፡የኾነ፡ዋነኛው፡ካህን፡ዓዛሪያስ፦ሕዝቡ፡ቍርባኑን፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ማቅረብ፡ ከዠመረ፡ወዲህ፡በልተናል፥ጠግበናልም፥እግዚአብሔር፡ሕዝቡን፡ባርኳልና፥ብዙ፡ተርፏል፤የተረፈውም፡ይህ፡ ክምር፡ትልቅ፡ነው፡ብሎ፡ተናገረ።
11ሕዝቅያስም፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ጐተራ፡ያዘጋጁ፡ዘንድ፡አዘዘ፤እነርሱም፡አዘጋጁ።
12ቍርባኑና፡ዓሥራቱን፡የተቀደሱትንም፡በእምነት፡ወደዚያ፡አገቡት።ሌዋዊውም፡ኮናንያ፡ ተሾመባቸው፥ወንድሙም፡ሰሜኢ፡በማዕርግ፡ኹለተኛ፡ነበረ፤
13በንጉሡም፡በሕዝቅያስና፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡አለቃ፡በዐዛርያስ፡ትእዛዝ፡ ይሒዒል፥ዓዛዝያ፥ናሖት፥ዐሳሄል፥ይሬሞት፥ዮዛባት፥ኤሊኤል፥ሰማክያ፥መሐት፥በናያስ፥ከኮናንያና፡ ከወንድሙ፡ከሰሜኢ፡እጅ፡በታች፡ተቈጣጣሪዎች፡ነበሩ።
14የሌዋዊውም፡የይምና፡ልጅ፡የምሥራቁ፡ደጅ፡በረኛ፡ቆሬ፡የእግዚአብሔርን፡መባና፡የተቀደሱትን፡ነገሮች፡ እንዲያካፍል፡ሕዝቡ፡ለእግዚአብሔር፡በፈቃድ፡ባቀረቡት፡ላይ፡ተሾመ።
15በካህናቱም፡ከተማዎች፡ለታላላቆችና፡ለታናናሾች፡ወንድሞቻቸው፡በየሰሞናቸው፡ክፍላቸውን፡በእምነት፡ ይሰጡ፡ዘንድ፡ዔዴን፥ሚንያሚን፥ኢያሱ፥ሸማያ፥አማርያ፥ሴኬንያ፡ከእጁ፡በታች፡ነበሩ።
16ከሦስትም፡ዓመት፡ወደ፡ላይ፡ላሉ፡በየሰሞናቸው፡ለሥራቸውና፡ለአገልግሎታቸው፡ዕለት፡ዕለት፡ ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ለሚገቡ፡ወንዶች፡ዅሉ፤
17በያባቶቻቸውም፡ቤት፡ለተቈጠሩ፡ካህናት፥ከኻያ፡ዓመትም፡ወደ፡ላይ፡ላሉ፡በየሥርዐታቸውና፡ በየሰሞናቸው፡ለተቈጠሩ፡ሌዋውያን፥
18በማኅበሩም፡ዅሉ፡በየትውልዳቸው፡ለተቈጠሩ፡ለሕፃናታቸውና፡ለሚስቶቻቸው፡ለወንዶችና፡ለሴቶች፡ ልጆቻቸውም፡ይሰጡ፡ነበር፤በእምነት፡ተቀድሰዋልና።
19በየከተማዪቱም፡ዅሉ፡በከተማቸው፡መሰምሪያዎቹ፡ላሉ፡ለአሮን፡ልጆች፡ለካህናቱ፥ከካህናቱም፡ወገን፡ ላሉ፡ወንዶች፡ዅሉ፥በትውልዳቸውም፡ለተቈጠሩ፡ሌዋውያን፡ዅሉ፡ክፍላቸውን፡ይሰጡ፡ዘንድ፡በስማቸው፡ የተጻፉ፡ሰዎች፡ነበሩ።
20ሕዝቅያስም፡በይሁዳ፡ዅሉ፡እንዲህ፡አደረገ፤በአምላኩም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡መልካምንና፡ቅንን፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ነገር፡እውነትንም፡አደረገ።
21ስለእግዚአብሔርም፡ቤት፡አገልግሎት፡በዠመረው፡ሥራ፡ዅሉ፥በሕጉና፡በትእዛዙም፥አምላኩን፡ ለመፈለግ፡በፍጹም፡ልቡ፡አደረገው፥ተከናወነለትም።