Skip to content
← 2 Chronicles

Chapter 3 · Amharic

2 Chronicles

1ሰሎሞንም፡እግዚአብሔር፡ለአባቱ፡ለዳዊት፡በተገለጠበት፡በሞሪያ፡ተራራ፡ዳዊት፡ባዘጋጀው፡ስፍራ፡ በኢያቡሳዊው፡በኦርና፡ዐውድማ፡በኢየሩሳሌም፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡መሥራት፡ዠመረ።

2በነገሠም፡በአራተኛው፡ዓመት፡በኹለተኛው፡ወር፡መሥራት፡ዠመረ።

3ሰሎሞንም፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ይሠራ፡ዘንድ፡የጣለው፡መሠረት፡ይህ፡ነው፤ርዝመቱም፡በዱሮው፡ ስፍር፡ስድሳ፡ክንድ፥ወርዱም፡ኻያ፡ክንድ፡ነበረ።

4በቤቱም፡ፊት፡የነበረው፡ወለል፡ርዝመቱ፡እንደ፡ቤቱ፡ወርድ፡ኻያ፡ክንድ፥ቁመቱም፡መቶ፡ኻያ፡ክንድ፡ ነበረ፤ውስጡንም፡በጥሩ፡ወርቅ፡ለበጠው።

5ታላቁንም፡ቤት፡በጥድ፡ዕንጨት፡ከደነው፥በጥሩም፡ወርቅ፡ለበጠው፤የዘንባባና፡የሰንሰለት፡አምሳል፡ ቀረጸበት።

6ቤቱንም፡በዕንቍ፡አስጌጠው፤ወርቁንም፡የፈርዋይም፡ወርቅ፡ነበረ።

7ቤቱንም፡ሠረገላዎቹንም፡መድረኮቹንም፡ግንቦቹንም፡ደጆቹንም፡በወርቅ፡ለበጠ፤በግንቦቹም፡ላይ፡ ኪሩቤልን፡ቀረጸ።

8ቅድስተ፡ቅዱሳኑንም፡ሠራ፤ርዝመቱም፡እንደ፡ቤቱ፡ወርድ፡ኻያ፡ክንድ፥ወርዱም፡ኻያ፡ክንድ፡ ነበረ፤ስድስት፡መቶ፡መክሊት፡በሚያኽል፡በጥሩ፡ወርቅ፡ለበጠው።

9የምስማሮቹም፡ሚዛን፡ዐምሳ፡ሰቅል፡ወርቅ፡ነበረ።የደርቡንም፡ጓዳዎች፡በወርቅ፡ለበጠ።

10በቅድስተ፡ቅዱሳንም፡ውስጥ፡ከዕንጨት፡ሥራ፡ኹለቱ፡ኪሩቤልን፡ሠራ፥በወርቅም፡ለበጣቸው።

11የኪሩቤልም፡ክንፎች፡ኻያ፡ክንድ፡ሙሉ፡ተዘርግተው፡ነበር፤የአንዱ፡ኪሩብ፡ክንፍ፡ዐምስት፡ክንድ፡ ነበረ፥የቤቱንም፡ግንብ፡ይነካ፡ነበረ፤ኹለተኛው፡ክንፍ፡ዐምስት፡ክንድ፡ነበረ፥የኹለተኛውንም፡ኪሩብ፡ክንፍ፡ ይነካ፡ነበር።

12የኹለተኛውም፡ኪሩብ፡ክንፍ፡ዐምስት፡ክንድ፡ነበረ፥የቤቱንም፡ግንብ፡ይነካ፡ነበር፤ኹለተኛውም፡ክንፍ፡ ዐምስት፡ክንድ፡ነበረ፥የሌላውንም፡ኪሩብ፡ክንፍ፡ይነካ፡ነበር።

13የእነዚህም፡ኪሩቤል፡ክንፎች፡ኻያ፡ክንድ፡ሙሉ፡ተዘርግተው፡ነበር፤በእግራቸውም፡ቆመው፡ ነበር፥ፊቶቻቸውም፡ወደ፡ቤቱ፡ይመለከቱ፡ነበር።

14ከሰማያዊውም፡ከሐምራዊውም፡ከቀዩም፡ሐር፡ከጥሩም፡በፍታ፡መጋረጃውን፡ሠራ፥ኪሩቤልንም፡ ጠለፈበት።

15በቤቱም፡ፊት፡ቁመታቸው፡ሠላሳ፡ዐምስት፡ክንድ፡የነበረውን፡ኹለቱን፡ዐምዶች፡ሠራ፥በያንዳንዳቸውም፡ ላይ፡የነበረው፡ጕልላት፡ዐምስት፡ክንድ፡ነበረ።

16እንደ፡ድሪ፡ያሉ፡ሰንሰለቶችንም፡ሠርቶ፡በአዕማዱ፡ራስ፡ላይ፡አደረጋቸው፤መቶም፡ሮማኖች፡ሠርቶ፡ በሰንሰለቱ፡ላይ፡አደረጋቸው።

17አዕማዶቹንም፡አንደኛውን፡በቀኝ፥ኹለተኛውን፡በግራ፡በመቅደሱ፡ፊት፡አቆማቸው፤በቀኝም፡የነበረውን፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ስም፡ያቁም፡በግራም፡የነበረውን፡ስም፡በለዝ፡ብሎ፡ጠራቸው።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source