Skip to content
← 2 Chronicles

Chapter 4 · Amharic

2 Chronicles

1ደግሞም፡ርዝመቱ፡ኻያ፡ክንድ፥ወርዱም፡ኻያ፡ክንድ፥ቁመቱም፡ዐሥር፡ክንድ፡የነበረውን፡የናሱን፡ መሠዊያ፡ሠራ።

2ከፈሰሰም፡ናስ፡ከዳር፡እስከ፡ዳር፡ዐሥር፡ክንድ፥ቁመቱም፡ዐምስት፡ክንድ፥በዙሪያውም፡ሠላሳ፡ክንድ፡ የኾነ፡ክብ፡ኵሬ፡ሠራ።

3በበታቹም፡ላንድ፡ክንድ፡ዐሥር፥ለአንድም፡ክንድ፡ዐሥር፥ጕብጕቦች፡አዞረበት፤ኵሬውም፡በቀለጠ፡ጊዜ፡ ጕብጕቦቹ፡በኹለት፡ተራ፡ከርሱ፡ጋራ፡ዐብረው፡ቀልጠው፡ነበር።

4በዐሥራ፡ኹለትም፡በሬዎች፡ምስል፡ላይ፡ተቀምጦ፡ነበር፤ከነርሱም፡ሦስቱ፡ወደ፡ሰሜን፡ሦስቱም፡ወደ፡ ምዕራብ፡ሦስቱም፡ወደ፡ደቡብ፡ሦስቱም፡ወደ፡ምሥራቅ፡ይመለከቱ፡ነበር፤ኵሬውም፡በላያቸው፡ ነበር፥የዅሉም፡ዠርባቸው፡በስተውስጥ፡ነበረ።

5ውፍረቱም፡አንድ፡ጋት፡ያኽል፡ነበረ፤ከንፈሩም፡እንደ፡ጽዋ፡ከንፈር፥እንደ፡ሱፍ፡አበባ፡ኾኖ፡ተሠርቶ፡ ነበር፤ሦስት፡ሺሕም፡የባዶስ፡መስፈሪያ፡ይይዝ፡ነበር።

6ደግሞም፡ዐሥር፡የመታጠቢያ፡ሰኖች፡ሠራ፥ለሚቃጠለውም፡መሥዋዕት፡የሚቀርበው፡ነገር፡ዅሉ፡ ይታጠብባቸው፡ዘንድ፡ዐምስቱን፡በቀኝ፥ዐምስቱንም፡በግራ፡አኖራቸው፤ኵሬው፡ግን፡ካህናት፡ይታጠቡበት፡ ነበር።

7ዐሥሩንም፡መቅረዞች፡እንደ፡ሥርዐታቸው፡ከወርቅ፡ሠርቶ፡ዐምስቱን፡በቀኝ፥ዐምስቱንም፡በግራ፡ በመቅደሱ፡ውስጥ፡አኖራቸው።

8ዐሥሩንም፡ገበታዎች፡ሠርቶ፡ዐምስቱን፡በቀኝ፥ዐምስቱንም፡በግራ፡በመቅደሱ፡ውስጥ፡አኖራቸው።አንድ፡ መቶም፡የወርቅ፡ድስቶች፡ሠራ።

9ደግሞም፡የካህናቱን፡አደባባይ፥ታላቁንም፡አደባባይ፥የአደባባዩንም፡ደጆች፡ሠራ፥ደጆቻቸውንም፡በናስ፡ ለበጠ።

10ኵሬውንም፡በቤቱ፡ቀኝ፡በአዜብ፡በኩል፡አኖረው።

11ኪራምም፡ምንቸቶቹንና፡መጫሪያዎቹን፡ድስቶቹንም፡ሠራ።ኪራምም፡ለንጉሡ፡ለሰሎሞን፡በእግዚአብሔር፡ ቤት፡የሠራውን፡ሥራ፡ዅሉ፡ጨረሰ።

12ኹለቱን፡አዕማድ፥ጽዋዎቹንም፥በአዕማዱም፡ላይ፡የነበሩትን፡ኹለት፡ጕልላቶች፥በአዕማዱም፡ላይ፡ የነበሩትን፡የጕልላቶች፡ኹለቱን፡ጽዋዎች፡የሚሸፍኑትን፡ኹለቱን፡መርበቦች፡ሠራ።

13በአዕማዱም፡ላይ፡የነበሩትን፡ኹለቱን፡ጕልላቶች፡ይሸፍኑ፡ዘንድ፥ለያንዳንዱ፡መርበብ፡ኹለት፡ኹለት፡ ተራ፡ሮማኖች፥ለኹለቱ፡መርበቦች፡አራት፡መቶ፡ሮማኖች፡አደረገ።

14መቀመጫዎቹንና፡በመቀመጫዎቹ፡ላይ፡የሚቀመጡትን፡የመታጠቢያ፡ሰኖች፥

15አንዱንም፡ኵሬ፥በበታቹም፡የሚኾኑትን፡ዐሥራ፡ኹለት፡በሬዎች፡ሠራ።

16ምንቸቶቹንም፡መጫሪያዎቹንም፡ሜንጦዎቹንም፡ዕቃቸውንም፡ዅሉ፡ኪራም፡ለንጉሡ፡ለሰሎሞን፡ ስለእግዚአብሔር፡ቤት፡ከለስላሳ፡ናስ፡ሠራ።

17ንጉሡም፡በዮርዳኖስ፡ሜዳ፡በሱኮትና፡በጽሬዳ፡መካከል፡ባለው፡በወፍራሙ፡መሬት፡ውስጥ፡አስፈሰሰው።

18ሰሎሞንም፡እነዚህን፡ዕቃዎች፡ዅሉ፡እጅግ፡አብዝቶ፡ሠራ፤የናሱም፡ሚዛን፡አይቈጠርም፡ነበር።

19ሰሎሞንም፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡የነበረውን፡ዕቃ፡ዅሉ፡የወርቁንም፡መሠዊያ፥የገጹንም፡ኅብስት፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org የነበረባቸውን፡ገበታዎች፥

20በቅድስተ፡ቅዱሳኑም፡ፊት፡እንደ፡ሥርዐታቸው፡ያበሩ፡ዘንድ፡መቅረዞችንና፡ቀንዲሎቻቸውን፡ከጥሩ፡ ወርቅ፡ሠራ።

21አበባዎቹንና፡ቀንዲሎቹን፡መኰስተሪያዎቹንም፡ከጥሩ፡ወርቅ፡ሠራ።

22ጕጦቹንም፡ድስቶቹንም፡ጭልፋዎቹንም፡ማንደጃዎቹንም፡ከጥሩ፡ወርቅ፡ሠራ።የውስጠኛውም፡ቤት፡ የቅድስተ፡ቅዱሳን፡ደጆች፡የቤተ፡መቅደሱም፡ደጆች፡የወርቅ፡ነበሩ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source