Skip to content
← 2 Chronicles

Chapter 33 · Amharic

2 Chronicles

1ምናሴም፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የዐሥራ፡ኹለት፡ዓመት፡ልጅ፡ነበረ፥በኢየሩሳሌምም፡ዐምሳ፡ዐምስት፡ ዓመት፡ነገሠ።

2እግዚአብሔርም፡ከእስራኤል፡ልጆች፡ፊት፡እንዳወጣቸው፡እንደ፡አሕዛብ፡ያለ፡ርኵሰት፡በእግዚአብሔር፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ፊት፡ክፉ፡ነገር፡አደረገ።

3አባቱም፡ሕዝቅያስ፡ያፈረሳቸውን፡የኰረብታውን፡መስገጃዎች፡መልሶ፡ሠራ፤ለበዓሊምም፡መሠዊያ፡ ሠራ፥የማምለኪያ፡ዐጸዶችንም፡ተከለ፥ለሰማይም፡ሰራዊት፡ዅሉ፡ሰገደ፥አመለካቸውም።

4እግዚአብሔርም፦ስሜ፡በኢየሩሳሌም፡ለዘለዓለም፡ይኖራል፡ባለው፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡መሠዊያዎችን፡ ሠራ።

5በእግዚአብሔርም፡ቤት፡በኹለቱ፡አደባባዮች፡ላይ፡ለሰማይ፡ሰራዊት፡ዅሉ፡መሠዊያዎችን፡ሠራ።

6በሄኖምም፡ልጅ፡ሸለቆ፡ውስጥ፡ልጆቹን፡በእሳት፡አሳለፈ፤ሞራ፡ገላጭም፡ኾነ፥አስማትም፡ አደረገ፥መተተኛም፡ነበረ፥መናፍስት፡ጠሪዎችንና፡ጠንቋዮችንም፡ሰበሰበ፤ያስቈጣውም፡ዘንድ፡ በእግዚአብሔር፡ፊት፡እጅግ፡ክፉ፡ነገር፡አደረገ።

8እግዚአብሔርም፡ለዳዊትና፡ለልጁ፡ለሰሎሞን፦በዚህ፡ቤት፡ከእስራኤልም፡ነገድ፡ዅሉ፡በመረጥዃት፡ በኢየሩሳሌም፡ስሜን፡ለዘለዓለም፡አኖራለኹ፤ያዘዝዃቸውንም፡ዅሉ፥በሙሴ፡የተሰጠውን፡ሕግና፡ሥርዐት፡ ፍርድንም፡ዅሉ፡ቢያደርጉ፡ቢጠብቁም፥ለአባቶቻችኹ፡ከሰጠዃት፡ምድር፡የእስራኤልን፡እግር፡እንደ፡ገና፡ አላርቅም፡ባለበት፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ውስጥ፡የሠራውን፡የጣዖት፡የተቀረጸውን፡ምስል፡አቆመ።

9ምናሴም፡እግዚአብሔር፡ከእስራኤል፡ልጆች፡ፊት፡ካጠፋቸው፡ከአሕዛብ፡ይልቅ፡ክፉ፡ይሠሩ፡ዘንድ፡ በይሁዳና፡በኢየሩሳሌም፡የሚኖሩትን፡አሳተ።

10እግዚአብሔርም፡ምናሴንና፡ሕዝቡን፡ተናገራቸው፤ግን፡አልሰሙትም።

11ስለዚህም፡እግዚአብሔር፡የአሶርን፡ንጉሥ፡ሰራዊት፡አለቃዎች፡አመጣባቸው፤ምናሴንም፡በዛንጅር፡ ያዙት፥በሰንሰለትም፡አስረው፡ወደ፡ባቢሎን፡ወሰዱት።

12በተጨነቀም፡ጊዜ፡አምላኩን፡እግዚአብሔርን፡ፈለገ፥በአባቶቹም፡አምላክ፡ፊት፡ሰውነቱን፡እጅግ፡ አዋረደ፥

13ወደ፡ርሱም፡ጸለየ፤ርሱም፡ተለመነው፥ጸሎቱንም፡ሰማው፥ወደ፡መንግሥቱም፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ መለሰው፤ምናሴም፡እግዚአብሔር፡ርሱ፡አምላክ፡እንደ፡ኾነ፡ዐወቀ።

14ከዚህ፡በዃላ፡በዳዊት፡ከተማ፡በስተውጭው፡ከግዮን፡ምዕራብ፡በሸለቆው፡ውስጥ፡እስከዓሳ፡በር፡መግቢያ፡ ድረስ፡ቅጥር፡ሠራ።በዖፌልም፡አዞረበት፥እጅግም፡ከፍ፡አደረገው፤በተመሸጉትም፡በይሁዳ፡ከተማዎች፡ ዅሉ፡የጭፍራ፡አለቃዎችን፡አኖረ።

15እንግዳዎችንም፡አማልክትና፡ጣዖቱንም፡ከእግዚአብሔር፡ቤት፡አራቀ፥የእግዚአብሔርም፡ቤት፡ባለበት፡ ተራራ፡ላይና፡በኢየሩሳሌም፡የሠራቸውን፡መሠዊያዎች፡ዅሉ፡ወስዶ፡ከከተማዪቱ፡በስተውጭ፡ጣላቸው።

16የእግዚአብሔርንም፡መሠዊያ፡ደግሞ፡ዐደሰ፥የደኅንነትና፡የምስጋናም፡መሥዋዕት፡ሠዋበት፤ይሁዳም፡ የእስራኤልን፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡እንዲያመልኩ፡አዘዘ።

17ሕዝቡ፡ግን፡ገና፡በኰረብታው፡መስገጃዎች፡ይሠዋ፡ነበር፤ቢኾንም፡ለአምላኩ፡ለእግዚአብሔር፡ብቻ፡ ነበር።

18የምናሴም፡የቀረው፡ነገር፥ወደ፡አምላኩም፡የጸለየው፡ጸሎት፥በእስራኤልም፡አምላክ፡በእግዚአብሔር፡ ስም፡የነገሩት፡የነቢያት፡ቃል፥እንሆ፥በእስራኤል፡ነገሥታት፡መጽሐፍ፡ተጽፏል።

19ደግሞም፡ጸሎቱ፥እግዚአብሔርም፡እንደተለመነው፥ኀጢአቱና፡መተላለፉ፡ዅሉ፥ራሱንም፡ሳያዋርድ፡ የኰረብታው፡መስገጃዎችን፡የሠራበት፡የማምለኪያ፡ዐጸዱንና፡የተቀረጹትንም፡ምስሎች፡የተከለበት፡ ስፍራ፥እንሆ፥በባለራእዩ፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡ተጽፏል።

20ምናሴም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በቤቱም፡ቀበሩት፤ልጁም፡ዓሞጽ፡በርሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።

21ዓሞጽ፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የኻያ፡ኹለት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፥በኢየሩሳሌምም፡ኹለት፡ዓመት፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ነገሠ።

22አባቱም፡ምናሴ፡እንዳደረገ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡አደረገ፤ዓሞጽም፡አባቱ፡ምናሴ፡ለሠራቸው፡ ለተቀረጹት፡ምስሎች፡ዅሉ፡ሠዋ፥አመለካቸውም።

23አባቱም፡ምናሴ፡ሰውነቱን፡እንዳዋረደ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡አንዳላዋረደ፡በእግዚአብሔርም፡ሰውነቱን፡ አላዋረደም፤ነገር፡ግን፥ዓሞጽ፡መተላለፉን፡እጅግ፡አበዛ።

24ባሪያዎቹም፡ተማምለው፡በቤቱ፡ገደሉት።

25የአገሩ፡ሕዝብ፡ግን፡በንጉሡ፡በዓሞጽ፡ላይ፡የተማማሉትን፡ዅሉ፡ገደሉ፤የአገሩም፡ሕዝብ፡ልጁን፡ ኢዮስያስን፡በርሱ፡ፋንታ፡አነገሡ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source