Skip to content
← 2 Chronicles

Chapter 34 · Amharic

2 Chronicles

1ኢዮስያስም፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የስምንት፡ዓመት፡ልጅ፡ነበረ፥በኢየሩሳሌምም፡ሠላሳ፡አንድ፡ ዓመት፡ነገሠ።

2በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ቅን፡ነገር፡አደረገ፥በአባቱም፡በዳዊት፡መንገድ፡ኼደ፤ወደ፡ቀኝም፡ወደ፡ ግራም፡አላለም።

3በነገሠም፡በስምንተኛው፡ዓመት፡ገና፡ብላቴና፡ሳለ፡የአባቱን፡የዳዊትን፡አምላክ፡ይፈልግ፡ ዠመር፤በዐሥራ፡ኹለተኛውም፡ዓመት፡ይሁዳንና፡ኢየሩሳሌምን፡ከኰረብታው፡መስገጃዎችና፡ከማምለኪያ፡ ዐጸዶቹ፥ከተቀረጹትና፡ቀልጠው፡ከተሠሩት፡ምስሎች፡ያነጻ፡ዠመር።

4የበዓሊምንም፡መሠዊያዎች፡በፊቱ፡አፈረሱ፤በላዩም፡የነበሩትን፡የፀሓዩን፡ምስሎች፡የማምለኪያ፡ ዐጸዶቹንም፡ቈረጠ፤የተቀረጹትንና፡ቀልጠው፡የተሠሩትን፡ምስሎች፡ሰባበረ፥አደቀቃቸውም፥ይሠዉላቸው፡ በነበሩት፡ሰዎች፡መቃብርም፡ላይ፡በተናቸው።

5የካህናታቸውንም፡ዐጥንት፡በመሠዊያቸው፡ላይ፡አቃጠለ፤ይሁዳንና፡ኢየሩሳሌምን፡አንጻ።

6የምናሴንና፡የኤፍሬምንም፡የስምዖንና፡የንፍታሌምንም፡ከተማዎች፥በዙሪያቸውም፡ያለውን፡ቦታ፡እንዲሁ፡ አነጻ።

7መሠዊያዎቹንም፡አፈረሰ፥የማምለኪያ፡ዐጸዶቹንና፡የተቀረጹትን፡ምስሎች፡አደቀቀ፥በእስራኤልም፡አገር፡ ዅሉ፡የፀሓይን፡ምስሎች፡ዅሉ፡ቈራረጠ፥ወደ፡ኢየሩሳሌምም፡ተመለሰ።

8በነገሠም፡በዐሥራ፡ስምንተኛው፡ዓመት፡ምድሪቱንና፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ካነጻ፡በዃላ፥የኤዜልያስ፡ ልጅ፡ሳፋን፥የከተማዪቱም፡አለቃ፡መዕሴያ፥ታሪክ፡ጸሓፊም፡የኢዮአካዝ፡ልጅ፡ኢዮአክ፡የእግዚአብሔርን፡ የአምላኩን፡ቤት፡ይጠግኑ፡ዘንድ፡ሰደዳቸው።

9ወደ፡ታላቁም፡ካህን፡ወደ፡ኬልቅያስ፡መጡ፤ሌዋውያኑም፡በረኛዎች፡ከምናሴና፡ከኤፍሬም፡ከቀረውም፡ ከእስራኤል፡ዅሉ፥ከይሁዳና፡ከብንያም፡ዅሉ፡በኢየሩሳሌምም፡ከሚኖሩት፡የሰበሰቡትን፥ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ የቀረበውን፡ገንዘብ፡ሰጡት።

10የእግዚአብሔርንም፡ቤት፡በሚሠሩት፡ላይ፡ለተሾሙት፡ሰጡ፤እነርሱም፡ይጠግኑና፡ያድሱ፡ ዘንድ፥የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ለሚሠሩ፡ሠራተኛዎች፡ሰጡ።

11የይሁዳ፡ነገሥታት፡ላፈረሱት፡ቤት፡ሠረገላዎች፡ያደርጉ፡ዘንድ፥ለማጋጠሚያም፡ዕንጨት፡የተጠረበውንም፡ ድንጋይ፡ይገዙ፡ዘንድ፡ለዐናጢዎችና፡ለጠራቢዎች፡ሰጡ።

12ሰዎቹም፡ሥራውን፡በመታመን፡አደረጉ፤በእነርሱም፡ላይ፡የተሾሙት፥ሥራውንም፡የሚያሠሩት፡ ሌዋውያን፡ከሜራሪ፡ልጆች፡ኢኤትና፡ዐብድዩ፥ከቀአትም፡ልጆች፡ዘካርያስና፡ሜሱላም፡ነበሩ።ከሌዋውያንም፡ ወገን፡በዜማ፡ዕቃ፡ዐዋቂዎች፡የነበሩ፡ዅሉ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

13በተሸካሚዎችና፡ልዩ፡ልዩ፡ሥራ፡በሚሠሩ፡ላይ፡ተሾመው፡ነበር፤ጸሓፊዎቹና፡አለቃዎቹም፡በረኛዎቹም፡ ከሌዋውያን፡ወገን፡ነበሩ።

14ወደእግዚአብሔርም፡ቤት፡የቀረበውን፡ገንዘብ፡ባመጡ፡ጊዜ፡ካህኑ፡ኬልቅያስም፡በሙሴ፡እጅ፡ የተሰጠውን፡የእግዚአብሔርን፡ሕግ፡መጽሐፍ፡አገኘ።

15ኬልቅያስም፡ጸሓፊውን፡ሳፋንን፦የሕጉን፡መጽሐፍ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡አግኝቻለኹ፡ብሎ፡ ተናገረው።ኬልቅያስም፡መጽሐፉን፡ለሳፋን፡ሰጠው።

16ሳፋንም፡መጽሐፉን፡ወደ፡ንጉሡ፡አመጣ፤ለንጉሡም።ባሪያዎችኽ፡የተሰጣቸውን፡ትእዛዝ፡ዅሉ፡ ያደርጋሉ፤

17በእግዚአብሔርም፡ቤት፡የተገኘውን፡ገንዘብ፡አፈሰሱ፥በሥራውም፡ላይ፡ለተሾሙትና፡ለሠራተኛዎቹ፡ሰጡ፡ ብሎ፡አወራለት።

18ጸሓፊውም፡ሳፋን፡ለንጉሡ፦ካህኑ፡ኬልቅያስ፡መጽሐፍ፡ሰጠኝ፡ብሎ፡ነገረው።ሳፋንም፡በንጉሡ፡ፊት፡ አነበበው።

19ንጉሡም፡የሕጉን፡ቃል፡በሰማ፡ጊዜ፡ልብሱን፡ቀደደ።

20ንጉሡም፡ኬልቅያስን፥የሳፋንንም፡ልጅ፡አኪቃምን፥የሚክያስንም፡ልጅ፡ዐብዶንን፥ጸሓፊውንም፡ ሳፋንን፥የንጉሡንም፡ብላቴና፡ዐሳያን፦

21በዚህ፡መጽሐፍ፡የተጻፈውን፡ዅሉ፡ያደርጉ፡ዘንድ፡አባቶቻችን፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ ስላልጠበቁ፥በላያችን፡የነደደ፡የእግዚአብሔር፡ቍጣ፡እጅግ፡ነውና፥ኼዳችኹ፡ስለተገኘው፡የመጽሐፍ፡ቃል፡ ለእኔ፡በእስራኤልና፡በይሁዳም፡ለቀሩት፡እግዚአብሔርን፡ጠይቁ፡ብሎ፡አዘዛቸው።

22ኬልቅያስና፡እነዚያ፡ንጉሥ፡ያዘዛቸው፡ወደልብስ፡ጠባቂው፡ወደሐስራ፡ልጅ፡ወደቲቁዋ፡ልጅ፡ወደሴሌም፡ ሚስት፡ወደ፡ነቢዪቱ፡ወደ፡ሕልዳና፡ኼዱ፤ርሷም፡በኢየሩሳሌም፡በከተማዪቱ፡በኹለተኛው፡ክፍል፡ተቀምጣ፡ ነበር፤ይህንም፡ነገር፡ነገሯት።

23ርሷም፡አለቻቸው፦የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ወደ፡እኔ፡ለላካችኹ፡ሰው፡ እንዲህ፡ብላችኹ፡ንገሩት፦

24እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥በይሁዳ፡ንጉሥ፡ፊት፡በተነበበው፡መጽሐፍ፡የተጻፉትን፡ቃላት፡ ዅሉ፥ማለት፡ክፉ፡ነገርን፥በዚህ፡ስፍራና፡በሚኖሩበት፡ላይ፡አመጣለኹ።

25በእጃቸው፡ሥራ፡ዅሉ፡ሊያስቈጡኝ፡ትተውኛልና፥ለሌላዎችም፡አማልክት፡ዐጥነዋልና፥ቍጣዬ፡በዚህ፡ ስፍራ፡ይነዳ፟ል፥አይጠፋምም።

26እግዚአብሔርን፡ለመጠየቅ፡ለላካችኹ፡ለይሁዳ፡ንጉሥ፡እንዲህ፡በሉት፦የእስራኤል፡አምላክ፡ እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ስለሰማኸው፡ቃል፡ልብኽ፡ገር፡ኾኗልና፥

27በፊቴም፡ራስኽን፡አዋርደኻልና፥በዚህም፡ስፍራና፡በሚኖሩበት፡ላይ፡ቃሌን፡በሰማኽ፡ጊዜ፡ራስኽን፡ አዋርደኻልና፥ልብስኽንም፡ቀደ፟ኽ፡በፊቴ፡አልቅሰኻልና፥እኔ፡ደግሞ፡ሰምቻለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።

28እንሆ፥ወደ፡አባቶችኽ፡እሰበስብኻለኹ፥በሰላምም፡ወደ፡መቃብርኽ፡ትሰበሰባለኽ፤በዚህም፡ስፍራና፡ በሚኖሩበት፡ላይ፡የማመጣውን፡ክፉ፡ነገር፡ዅሉ፡ዐይኖችኽ፡አያዩም።ይህንም፡ለንጉሥ፡አወሩለት።

29ንጉሡም፡ላከ፥የይሁዳንና፡የኢየሩሳሌምንም፡ሽማግሌዎች፡ዅሉ፡ሰበሰበ።

30ንጉሡም፡የይሁዳም፡ሰዎች፡ዅሉ፥በኢየሩሳሌምም፡የሚኖሩና፡ካህናቱ፥ሌዋውያኑም፥ሕዝቡም፡ዅሉ፡ ከታናሹ፡ዠምሮ፡እስከ፡ታላቁ፡ድረስ፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ወጡ፤በእግዚአብሔርም፡ቤት፡የተገኘውን፡ የቃል፡ኪዳኑን፡መጽሐፍ፡ቃል፡ዅሉ፡በዦሯቸው፡አነበበ።

31ንጉሡም፡በስፍራው፡ቆሞ፡እግዚአብሔርን፡ተከትሎ፡እንዲኼድ፥ትእዛዙንና፡ምስክሩን፡ሥርዐቱንም፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org በፍጹም፡ልቡና፡በፍጹም፡ነፍሱ፡እንዲጠብቅ፥በዚህም፡መጽሐፍ፡የተጻፈውን፡የቃል፡ኪዳን፡ቃል፡ እንዲያደርግ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቃል፡ኪዳን፡አደረገ።

32በኢየሩሳሌምና፡በብንያምም፡የተገኙትን፡ዅሉ፡በዚህ፡ነገር፡አማለ፤በኢየሩሳሌምም፡የሚኖሩት፡ የአባቶቻቸው፡አምላክ፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ኪዳን፡እንዳዘዘ፡አደረጉ።

33ኢዮስያስም፡ከእስራኤል፡ልጆች፡ምድር፡ዅሉ፡ርኩሱን፡ዅሉ፡አስወገደ፥በእስራኤልም፡የተገኙትን፡ዅሉ፡ አምላካቸውን፡እግዚአብሔርን፡እንዲያመልኩ፡አደረገ።በዘመኑ፡ዅሉ፡የአባቶቻቸውን፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡ ከመከተል፡አልራቁም።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source