1ሰሎሞንም፦እግዚአብሔር፦በጨለማ፡ውስጥ፡እኖራለኹ፡ብሏል፤
2እኔ፡ግን፡ለዘለዓለም፡ትኖርበት፡ዘንድ፡ማደሪያ፡ቤትን፡ሠራኹልኽ፡አለ።
3ንጉሡም፡ፊቱን፡ዘወር፡አድርጎ፡የእስራኤልን፡ጉባኤ፡ዅሉ፡መረቀ፤የእስራኤልም፡ጉባኤ፡ዅሉ፡ቆመው፡ ነበር።
4ርሱም፡አለ፦ለአባቴ፡ለዳዊት፡በአፉ፡የተናገረ፡በእጁም፡የፈጸመ፡የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ ይባረክ፤
5ርሱም፦ሕዝቤን፡ከግብጽ፡ካወጣኹበት፡ቀን፡ዠምሮ፡ስሜ፡የሚጠራበት፡ቤት፡በዚያ፡ይሠራልኝ፡ዘንድ፡ ከእስራኤል፡ነገድ፡ዅሉ፡ማንኛውንም፡ከተማ፡አልመረጥኹም፤በሕዝቤም፡በእስራኤል፡ላይ፡አለቃ፡ይኾን፡ ዘንድ፡ማንንም፡አልመረጥኹም፤
6ነገር፡ግን፥ስሜ፡በዚያ፡እንዲጠራባት፡ኢየሩሳሌምን፡መርጫለኹ፥በሕዝቤም፡በእስራኤል፡ላይ፡እንዲኾን፡ ዳዊትን፡መርጫለኹ፡ብሏልና።
7አባቴም፡ዳዊት፡ለእስራኤል፡አምላክ፡ለእግዚአብሔር፡ቤት፡ይሠራ፡ዘንድ፡በልቡ፡ዐስቦ፡ነበር።
8እግዚአብሔርም፡አባቴን፡ዳዊትን፦ለስሜ፡ቤት፡ትሠራ፡ዘንድ፡በልብኽ፡ዐስበኻልና፥ይህን፡በልብኽ፡ መልካም፡አደረግኽ።
9ነገር፡ግን፥ከወገብኽ፡የሚወጣው፡ልጅኽ፡ርሱ፡ለስሜ፡ቤትን፡ይሠራል፡እንጂ፡ቤት፡የምትሠራልኝ፡ አንተ፡አይደለኽም፡አለው።
10እግዚአብሔርም፡የተናገረውን፡ቃል፡ፈጸመ፤እግዚአብሔርም፡ተስፋ፡እንደ፡ሰጠ፡በአባቴ፡በዳዊት፡ፋንታ፡ ተነሣኹ፥በእስራኤልም፡ዙፋን፡ላይ፡ተቀመጥኹ፥ለእስራኤልም፡አምላክ፡ለእግዚአብሔር፡ስም፡ቤት፡ሠራኹ።
11ከእስራኤልም፡ልጆች፡ጋራ፡ያደረገው፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ኪዳን፡ያለበትን፡ታቦት፡በዚያው፡ውስጥ፡ አኖርኹ።
13ሰሎሞንም፡ርዝመቱ፡ዐምስት፡ክንድ፥ወርዱም፡ዐምስት፡ክንድ፥ቁመቱም፡ሦስት፡ክንድ፡የኾነ፡ የናስ፡መደገፊያ፡ሠርቶ፡በአደባባዩ፡መካከል፡ተክሎት፡ነበር፥በላዩም፡ቆመ፥በእስራኤልም፡ጉባኤ፡ዅሉ፡ ፊት፡በጕልበቱ፡ተንበርክኮ፡እጁን፡ወደ፡ሰማይ፡ዘረጋ፤የእስራኤልም፡ጉባኤ፡ዅሉ፡እያዩ፡በእግዚአብሔር፡ መሠዊያ፡ፊት፡ቆሞ፡እጆቹንም፡ዘርግቶ፡እንዲህ፡አለ።
14አቤቱ፡የእስራኤል፡አምላክ፡ሆይ፥በሰማይ፡ወይም፡በምድር፡አንተን፡የሚመስል፡አምላክ፡የለም፤በፍጹም፡ ልባቸው፡በፊትኽ፡ለሚኼዱ፡ባሪያዎችኽ፡ቃል፡ኪዳንንና፡ምሕረትን፡የምትጠብቅ፥
15ለባሪያኽ፡ለአባቴ፡ለዳዊት፡የሰጠኸውን፡ተስፋ፡የጠበቀኽ፤በአፍኽ፡ተናገርኽ፥ዛሬም፡እንደኾነው፡ በእጅኽ፡ፈጸምኸው።
16አኹንም፥አቤቱ፡የእስራኤል፡አምላክ፡ሆይ።አንተ፡በፊቴ፡እንደ፡ኼድኽ፡ልጆችኽ፡በሕጌ፡ይኼዱ፡ ዘንድ፡መንገዳቸውን፡ቢጠብቁ፡በእስራኤል፡ዙፋን፡የሚቀመጥ፡ሰው፡በፊቴ፡አታጣም፡ብለኽ፡ተስፋ፡ የሰጠኸውን፡ለባሪያኽ፡ለአባቴ፡ለዳዊት፡ጠብቅ።
17አኹንም፥አቤቱ፡የእስራኤል፡አምላክ፡ሆይ፥ለባሪያኽ፡ለዳዊት፡የተናገረኸው፡ቃል፡ይጽና።
18በእውኑ፡እግዚአብሔር፡ከሰው፡ጋራ፡በምድር፡ላይ፡ይኖራልን፧እንሆ፥ሰማይ፡ከሰማያትም፡በላይ፡ያለ፡ ሰማይ፡ይይዝኽ፡ዘንድ፡አይችልም፤ይልቁንስ፡እኔ፡የሠራኹት፡ቤት፡እንዴት፡ያንስ፡ይኾን፧
19ነገር፡ግን፥አቤቱ፡አምላኬ፡ሆይ፥ወደባሪያኽ፡ጸሎትና፡ልመና፡ተመልከት፥ባሪያኽም፡በፊትኽ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org የሚጸልየውን፡ጸሎትና፡ጥሪውን፡ስማ።
20ባሪያኽ፡ወደዚህ፡ስፍራ፡የሚጸልየውን፡ጸሎት፡ትሰማ፡ዘንድ።በዚያ፡ስሜ፡ይኾናል፡ወዳልኸው፡ ስፍራ፥ወደዚህ፡ቤት፡ዐይኖችኽ፡ቀንና፡ሌሊት፡የተገለጡ፡ይኹኑ።
21ባሪያኽና፡ሕዝብኽ፡እስራኤል፡ወደዚህ፡ስፍራ፡የሚጸልዩትን፡ልመና፡ስማ፤በማደሪያኽ፡በሰማይ፡ ስማ፤ሰምተኽም፡ይቅር፡በል።
22ሰው፡ባልንጀራውን፡ቢበድል፥በላዩም፡መሐላ፡ቢጫን፥ርሱም፡መጥቶ፡በዚህ፡ቤት፡በመሠዊያኽ፡ፊት፡ ቢምል፥
23በሰማይ፡ስማ፥አድርግም፥በባሪያዎችኽም፡ላይ፡ዳኛ፡ኹን፥በበደለኛውም፡ላይ፡ፍረድ፥መንገዱንም፡ በራሱ፡ላይ፡መልስበት፤ንጹሑንም፡አጽድቀው፥እንደ፡ጽድቁም፡ክፈለው።
24ሕዝብኽም፡እስራኤል፡አንተን፡ስለ፡በደሉ፡በጠላት፡ፊት፡ድል፡ተመትተው፡ወዳንተ፡ ቢመለሱ፥ስምኽንም፡ቢያከብሩ፥በዚህም፡ቤት፡በፊትኽ፡ቢጸልዩና፡ቢለምኑኽ፥አንተ፡በሰማይ፡ስማ፥
25የሕዝብኽንም፡የእስራኤልን፡ኀጢአት፡ይቅር፡በል፤ለእነርሱም፡ለአባቶቻቸውም፡ወደሰጠኻት፡ምድር፡ መልሳቸው።
26አንተን፡ስለ፡በደሉ፡ሰማያት፡በተዘጉ፡ጊዜ፡ዝናብም፡ባልዘነበ፡ጊዜ፥ወደዚህ፡ስፍራ፡ቢጸልዩ፥ስምኽንም፡ ቢያከብሩ፥ባስጨነቅኻቸውም፡ጊዜ፡ከኀጢአታቸው፡ቢመለሱ፥አንተ፡በሰማይ፡ስማ፥
27የባሪያዎችኽንና፡የሕዝብኽን፡የእስራኤልን፡ኀጢአት፡ይቅር፡በል፥የሚኼዱበትንም፡መልካም፡መንገድ፡ አሳያቸው፤ለሕዝብኽም፡ርስት፡አድርገኽ፡ለሰጠኻት፡ምድር፡ዝናብን፡ስጥ።
28በምድር፡ላይ፡ራብ፡ወይም፡ቸነፈር፡ወይም፡ዋግ፡ወይም፡ዐረማሞ፡ወይም፡አንበጣ፡ወይም፡ኵብኵባ፡ ቢኾን፥ጠላቶቻቸውም፡የአገሩን፡ከተማዎች፡ከበ፟ው፡ቢያስጨንቋቸው፥ማናቸውም፡መቅሠፍትና፡ደዌ፡ቢኾን፥
29ማንም፡ሰው፡ወይም፡ሕዝብኽ፡እስራኤል፡ዅሉ፥ማናቸውም፡ሰው፡ሕመሙንና፡ሐዘኑን፡ዐውቆ፡ ጸሎትና፡ልመና፡ቢያደርግ፡እጆቹንም፡ወደዚህ፡ቤት፡ቢዘረጋ፥
31ለአባቶቻችን፡በሰጠኸው፡ምድር፡ላይ፡በሚኖሩበት፡ዘመን፡ዅሉ፡ይፈሩኽ፡ዘንድ፡በመንገዶችኽም፡ ይኼዱ፡ዘንድ፥በማደሪያኽ፡በሰማይ፡ስማ፥ይቅርም፡በል፤አንተ፡ብቻ፡የሰውን፡ልጆች፡ልብ፡ታውቃለኽና፡ ልቡን፡ለምታውቀው፡ሰው፡ዅሉ፡እንደ፡መንገዱ፡ዅሉ፡መጠን፡ክፈለው።
32ከሕዝብኽም፡ከእስራኤል፡ያልኾነ፡እንግዳ፡ስለ፡ታላቁ፡ስምኽ፡ስለ፡ብርቱውም፡እጅኽ፡ስለተዘረጋውም፡ ክንድኽ፡ከሩቅ፡አገር፡በመጣ፡ጊዜ፥መጥቶም፡ወደዚህ፡ቤት፡በጸለየ፡ጊዜ፥
33አንተ፡በማደሪያኽ፡በሰማይ፡ስማ፤የምድርም፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ስምኽን፡ያውቁ፡ዘንድ፥እንደ፡ሕዝብኽም፡ እንደ፡እስራኤል፡ይፈሩኽ፡ዘንድ፥በዚህም፡በሠራኹት፡ቤት፡ስምኽ፡እንደ፡ተጠራ፡ያውቁ፡ዘንድ፥እንግዳው፡ የሚለምንኽን፡ዅሉ፡አድርግ።
34ሕዝብኽም፡ጠላቶቻቸውን፡ለመውጋት፡አንተ፡በምትልካቸው፡መንገድ፡ቢወጡ፥አንተም፡ወደመረጥኻት፡ ወደዚች፡ከተማ፡እኔም፡ለስምኽ፡ወደሠራኹት፡ቤት፡ለአንተ፡ቢጸልዩ፥
35ጸሎታቸውንና፡ልመናቸውን፡በሰማይ፡ስማ፥ፍርድንም፡አድርግላቸው።
36የማይበድል፡ሰው፡የለምና፡አንተን፡ቢበድሉ፥ተቈጥተኽም፡ለጠላት፡አሳልፈኽ፡ብትሰጣቸው፥ሩቅም፡ ወይም፡ቅርብ፡ወደ፡ኾነ፡አገር፡ቢማርኳቸው፥
37በተማረኩበትም፡አገር፡ኾነው፡በልባቸው፡ንስሓ፡ቢገቡ፥በምርኳቸውም፡አገር፡ሳሉ፡ ተመልሰው፦ኀጢአት፡ሠርተናል፥በድለንማል፥ክፉም፡አድርገናል፡ብለው፡ቢለምኑኽ፥
38በተማረኩበትም፡በምርኳቸው፡አገር፡ሳሉ፡በፍጹም፡ልባቸውና፡በፍጹም፡ነፍሳቸው፡ወዳንተ፡ ቢመለሱ፥ለአባቶቻቸውም፡ወደሰጠኻት፡ወደ፡ምድራቸው፡ወደመረጥኻትም፡ከተማ፡ለስምኽም፡ወደሠራኹት፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ቤት፡ቢጸልዩ፥
39ጸሎታቸውንና፡ልመናቸውን፡በማደሪያኽ፡በሰማይ፡ስማ፥ፍርድንም፡አድርግላቸው፤አንተንም፡የበደሉኽን፡ ሕዝብኽን፡ይቅር፡በል።
40አኹንም፥አምላኬ፡ሆይ፥በዚህ፡ስፍራ፡ወደሚኾነው፡ጸሎት፡ዐይኖችኽ፡የተገለጡ፥ዦሮዎችኽም፡ የሚያደምጡ፡እንዲኾኑ፡እለምንኻለኹ።
41አኹንም፥አቤቱ፡አምላክ፡ሆይ፥ከኀይልኽ፡ታቦት፡ጋራ፡ወደ፡ዕረፍትኽ፡ተነሣ፤አቤቱ፡አምላክ፡ ሆይ፥ካህናትኽ፡ደኅንነትን፡ይልበሱ፤ቅዱሳንኽም፡በደስታ፡ደስ፡ይበላቸው።
42አቤቱ፡አምላክ፡ሆይ፥የቀባኸውን፡ሰው፡ፊት፡አትመልስ፡ለባሪያም፡ለዳዊት፡ያደረግኽለትን፡ምሕረት፡ ዐስብ።