Skip to content
← 2 Chronicles

Chapter 7 · Amharic

2 Chronicles

1ሰሎሞንም፡ጸሎቱን፡በፈጸመ፡ጊዜ፡እሳት፡ከሰማይ፡ወርዶ፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕትና፡ሌላ፡መሥዋዕቱን፡ በላ፤የእግዚአብሔርም፡ክብር፡ቤቱን፡ሞላ።

2የእግዚአብሔርም፡ክብር፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ሞልቶት፡ነበርና፥ካህናቱ፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ መግባት፡አልቻሉም።

3የእስራኤልም፡ልጆች፡ዅሉ፡እሳቱ፡ሲወርድ፡የእግዚአብሔርም፡ክብር፡በቤቱ፡ላይ፡ሲኾን፡ያዩ፡ ነበር፤በወለሉም፡ላይ፡በግንባራቸው፡ወደ፡ምድር፡ተደፍተው፡ሰገዱ።ርሱ፡መልካም፡ነውና፥ምሕረቱም፡ ለዘለዓለም፡ነውና፥ብለውም፡እግዚአብሔርን፡አመሰገኑ።

4ንጉሡም፡ሕዝቡም፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡መሥዋዕት፡ያቀርቡ፡ነበር።

5ንጉሡም፡ሰሎሞን፡ኻያ፡ኹለት፡ሺሕ፡በሬዎችና፡መቶ፡ኻያ፡ሺሕ፡በጎች፡ሠዋ።እንዲሁ፡ንጉሡና፡ ሕዝቡ፡ዅሉ፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ቀደሱ።

6ካህናቱም፡በየሥርዐታቸው፥ሌዋውያኑም፡ደግሞ፦ምሕረቱ፡ለዘለዓለም፡ነውና፥እግዚአብሔርን፡አመስግኑ፡ የሚለውን፡የዳዊትን፡መዝሙር፡እየዘመሩ፥ንጉሡ፡ዳዊት፡እግዚአብሔርን፡ለማመስገን፡የሠራውን፡ የእግዚአብሔርን፡የዜማ፡ዕቃ፡ይዘው፡ቆመው፡ነበር፤ካህናቱም፡በፊታቸው፡መለከት፡ይነፉ፡ ነበር፤እስራኤልም፡ዅሉ፡ቆመው፡ነበር።

7ሰሎሞን፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ፊት፡የነበረውን፡የአደባባዩን፡ውስጥ፡ቀደሰ፤ሰሎሞንም፡የሠራው፡የናስ፡ መሠዊያ፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕትና፡የእኽሉን፡ቍርባን፡ስቡንም፡መያዝ፡አልቻለምና፡የሚቃጠለውን፡ መሥዋዕትና፡የደኅንነቱን፡መሥዋዕት፡ስብ፡በዚያ፡አቀረበ።

8ሰሎሞንም፡ከርሱም፡ጋራ፡እጅግ፡ታላቅ፡ጉባኤ፡የኾኑ፥ከሐማት፡መግቢያ፡ዠምሮ፡እስከግብጽ፡ወንዝ፡ ድረስ፡ያሉ፡እስራኤል፡ዅሉ፥በዚያን፡ጊዜ፡ሰባት፡ቀን፡በዓል፡አደረጉ።

9ሰባት፡ቀንም፡መሠዊያውን፡ቀድሰው፥ሰባት፡ቀንም፡በዓል፡አድርገው፡ነበርና፥በስምንተኛው፡ቀን፡ የተቀደሰውን፡ጉባኤ፡አደረጉ።

10በሰባተኛውም፡ወር፡በኻያ፡ሦስተኛውም፡ቀን፡ሕዝቡን፡ወደ፡ድንኳናቸው፡አሰናበተ፤እግዚአብሔር፡ ለዳዊትና፡ለሰሎሞን፡ለሕዝቡም፡ለእስራኤል፡ስላደረገው፡ቸርነት፡ደስ፡ብሏቸው፡ሐሴትን፡እያደረጉ፡ኼዱ።

11ሰሎሞንም፡የእግዚአብሔርን፡ቤትና፡የንጉሡን፡ቤት፡ጨረሰ፤በእግዚአብሔር፡ቤትና፡በራሱ፡ቤት፡ ይሠራው፡ዘንድ፡በልቡ፡ያሰበውን፡ዅሉ፡አከናወነ።

12እግዚአብሔርም፡ለሰሎሞን፡በሌሊት፡ተገልጦ፡እንዲህ፡አለው፦ጸሎትኽን፡ሰምቻለኹ፥ይህንም፡ስፍራ፡ ለራሴ፡ለመሥዋዕት፡ቤት፡መርጫለኹ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

13ዝናብ፡እንዳይወርድ፡ሰማያቱን፡ብዘጋ፥ወይም፡ምድሪቱን፡ይበላ፡ዘንድ፡አንበጣን፡ባዘ፟ው፥ወይም፡ በሕዝብ፡ላይ፡ቸነፈር፡ብሰድ፟፥

14በስሜ፡የተጠሩት፡ሕዝቤ፡ሰውነታቸውን፡አዋርደው፡ቢጸልዩ፥ፊቴንም፡ቢፈልጉ፥ከክፉ፡መንገዳቸውም፡ ቢመለሱ፥በሰማይ፡ኾኜ፡እሰማለኹ፥ኀጢአታቸውንም፡ይቅር፡እላለኹ፥ምድራቸውንም፡እፈውሳለኹ።

15አኹንም፡በዚህ፡ስፍራ፡ለሚጸለይ፡ጸሎት፡ዐይኖቼ፡ይገለጣሉ፥ዦሮዎቼም፡ያደምጣሉ።

16አኹንም፡ስሜ፡ለዘለዓለም፡በዚያ፡ይኖር፡ዘንድ፡ይህን፡ቤት፡መርጫለኹ፡ቀድሻለኹም፤ዐይኖቼና፡ ልቤም፡ዘወትር፡በዚያ፡ይኾናሉ።

17አንተም፡ደግሞ፡አባትኽ፡ዳዊት፡እንደ፡ኼደ፡በፊቴ፡ብትኼድ፥እንዳዘዝኹኽም፡ዅሉ፡ ብታደርግ፥ሥርዐቴንና፡ፍርዴንም፡ብትጠብቅ፥

18ከአባትኽ፡ከዳዊት፡ጋራ።በእስራኤል፡ላይ፡አለቃ፥የሚኾን፡ከዘርኽ፡አይታጣም፡ብዬ፡ቃል፡ኪዳን፡ እንዳደረግኹ፡የመንግሥትኽን፡ዙፋን፡አጸናለኹ።

19እናንተ፡ግን፡እኔን፡ከመከተል፡ብትመለሱ፥የሰጠዃችኹንም፡ሥርዐቴንና፡ትእዛዜን፡ ብትተዉ፥ኼዳችኹም፡ሌላዎችን፡አማልክት፡ብታመልኩ፡ብትሰግዱላቸውም፥

20ለአባቶቻችኹ፡ከሰጠዃቸው፡ምድር፡እነቅላችዃለኹ፤ለስሜም፡የቀደስኹትን፡ይህን፡ቤት፡ከፊቴ፡ እጥለዋለኹ፥በአሕዛብም፡ዅሉ፡መካከል፡ምሳሌና፡ተረት፡አደርገዋለኹ።

21ከፍ፡ከፍ፡ብሎ፡የነበረውንም፡ይህን፡ቤት፡እያዩ፡በዚያ፡የሚያልፉ፡ሰዎች፡ዅሉ፦እግዚአብሔር፡በዚህ፡ አገርና፡በዚህ፡ቤት፡ስለ፡ምን፡እንዲህ፡አደረገ፧ብለው፡ይደነቃሉ።

22መልሰውም፦ከግብጽ፡ምድር፡ያወጣቸውን፡የአባቶቻቸውን፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡ትተው፡ሌላዎችን፡ አማልክት፡ስለ፡ተከተሉ፥ስለ፡ሰገዱላቸውም፥ስለ፡አመለኳቸውም፥ስለዚህ፡ይህን፡ክፉ፡ነገር፡ዅሉ፡ አመጣባቸው፡ይላሉ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source