1ለአክአብም፡በሰማርያ፡ሰባ፡ልጆች፡ነበሩት፤ኢዩም፡ደብዳቤ፡ጻፈ፤የአክአብን፡ልጆች፡ለሚያሳድጉ፡ ለሰማርያ፡ታላላቆችና፡ሽማግሌዎች።
2ይህ፡ደብዳቤ፡አኹን፡በደረሳችኹ፡ጊዜ፡የጌታችኹ፡ልጆች፡ሠረገላዎችና፡ፈረሶችም፡የተመሸገችም፡ ከተማ፡መሣሪያዎችም፡በእናንተ፡ዘንድ፡አሉና፥
3ከጌታችኹ፡ልጆች፡ደስ፡የሚያሠኛችኹንና፡የሚሻላችኹን፡ምረጡ፥በአባቱም፡ዙፋን፡አስቀምጡት፥ስለ፡ ጌታችኹም፡ቤት፡ተዋጉ፡ብሎ፡ወደ፡ሰማርያ፡ሰደደ፤
4እነርሱ፡ግን፡እጅግ፡ፈርተው፦እንሆ፥ኹለቱ፡ነገሥታት፡በፊቱ፡ይቆሙ፡ዘንድ፡አልቻሉም፤እኛስ፡ እንዴት፡እንቆማለን፧አሉ።
5የቤቱ፡አለቃ፥የከተማዪቱም፡አለቃ፥ሽማግሌዎችና፡ልጆቹን፡የሚያሳድጉ፦እኛ፡ባሪያዎችኽ፡ ነን፥ያዘዝኸንም፡ዅሉ፡እናደርጋለን፤ንጉሥም፡በላያችን፡አናነግሥም፤የምትወደ፟ውን፡አድርግ፡ብለው፡ወደ፡ ኢዩ፡ላኩ።
6ኹለተኛም፦ወገኖቼስ፡እንደ፡ኾናችኹ፥ነገሬንም፡ከሰማችኹ፥የጌታችኹን፡ልጆች፡ራስ፡ቍረጡ፥ነገም፡ በዚህ፡ሰዓት፡ወደ፡ኢይዝራኤል፡ወደ፡እኔ፡ይዛችኹ፡ኑ፡ብሎ፡ደብዳቤ፡ጻፈላቸው።የንጉሡም፡ልጆች፡ ሰባው፡ሰዎች፡በሚያሳድጓቸው፡በከተማዪቱ፡ታላላቆች፡ዘንድ፡ነበሩ።
7ደብዳቤውም፡በደረሳቸው፡ጊዜ፡የንጉሡን፡ልጆች፡ሰባውን፡ሰዎች፡ይዘው፡ገደሏቸው፤ራሳቸውንም፡ በቅርጫት፡አድርገው፡ወደ፡ርሱ፡ወደ፡ኢይዝራኤል፡ላኩ።
8መልእክተኛም፡መጥቶ፦የንጉሡን፡ልጆች፡ራስ፡ይዘው፡መጥተዋል፡ብሎ፡ነገረው።ርሱም፦እስከ፡ነገ፡ ድረስ፡በበሩ፡አደባባይ፡ኹለት፡ክምር፡አድርጋችኹ፡አኑሯቸው፡አለ።
9በነጋውም፡ወጥቶ፡ቆመ፥ሕዝቡንም፡ዅሉ፦እናንተ፡ንጹሓን፡ናችኹ፤እንሆ፥ጌታዬን፡የወነጀልኹ፡ የገደልኹትም፡እኔ፡ነኝ፤እነዚህንስ፡ዅሉ፡የገደለ፡ማን፡ነው፧
10እግዚአብሔር፡በአክአብ፡ቤት፡ላይ፡ከተናገረው፡ከእግዚአብሔር፡ቃል፡በምድር፡ላይ፡አንዳች፡ እንዳይወድቅ፡አኹን፡ዕወቁ፤እግዚአብሔር፡በባሪያው፡በኤልያስ፡የተናገረውን፡አድርጓል፡አላቸው።
11ኢዩም፡ከአክአብ፡ቤት፡የቀረውን፡ዅሉ፥ታላላቆቹንም፡ዅሉ፥ወዳጆቹንና፡ካህናቱን፡ማንም፡ሳይቀር፡ በኢይዝራኤል፡ገደላቸው።
12ተነሥቶም፡ወደ፡ሰማርያ፡ኼደ፤በመንገድም፡ወዳለው፡ወደበግ፡ጠባቂዎች፡ቤት፡በደረሰ፡ጊዜ፥
13ኢዩ፡ከይሁዳ፡ንጉሥ፡ከአካዝያስ፡ወንድሞች፡ጋራ፡ተገናኝቶ፦እናንተ፡እነማን፡ ናችኹ፧አለ።እነርሱም፦እኛ፡የአካዝያስ፡ወንድሞች፡ነን፤የንጉሡንና፡የእቴጌዪቱን፡ልጆች፡ደኅንነት፡ ለመጠየቅ፡እንወርዳለን፡አሉት።
14ርሱም፦በሕይወታቸው፡ያዟቸው፡አለ።ያዟቸውም፥በበግ፡ጠባቂዎችም፡ቤት፡አጠገብ፡ባለው፡ጕድጓድ፡ አርባ፡ኹለቱን፡ሰዎች፡ገደሏቸው፤ማንንም፡አላስቀረም።
15ከዚያም፡በኼደ፡ጊዜ፡የሬካብን፡ልጅ፡ኢዮናዳብን፡ተገናኘው፤ደኅንነቱንም፡ጠይቆ፦ልቤ፡ከልብኽ፡ጋራ፡ እንደ፡ኾነ፡ያኽል፡ልብኽ፡ከልቤ፡ጋራ፡በቅንነት፡ነውን፧አለው፤ኢዮናዳብም፦እንዲሁ፡ነው፡ አለው።ኢዩም፦እንዲሁ፡እንደ፡ኾነስ፡እጅኽን፡ስጠኝ፡አለ።እጁንም፡ሰጠው፤ወደ፡ሠረገላውም፡አውጥቶ፡ ከርሱ፡ጋራ፡አስቀመጠውና።
16ከእኔ፡ጋራ፡ና፥ለእግዚአብሔርም፡መቅናቴን፡እይ፡አለው።በሠረገላውም፡አስቀመጠው።
17ወደ፡ሰማርያም፡በመጣ፡ጊዜ፡ለኤልያስ፡እንደተናገረው፡እንደእግዚአብሔር፡ቃል፡እስኪያጠፋው፡ድረስ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ከአክአብ፡በሰማርያ፡የቀረውን፡ዅሉ፡ገደለ።
18ኢዩም፡ሕዝቡን፡ዅሉ፡ሰብስቦ፦አክአብ፡በዓልን፡በጥቂቱ፡አመለከው፤ኢዩ፡ግን፡በብዙ፡ያመልከዋል።
19አኹንም፡የበዓልን፡ነቢያት፡ዅሉ፥አገልጋዮቹንም፡ዅሉ፥ካህናቱንም፡ዅሉ፡ወደ፡እኔ፡ጥሩ፤ማንም፡ አይቅር፤ለበዓል፡ታላቅ፡መሥዋዕት፡አቀርባለኹ፥የቀረውም፡ዅሉ፡በሕይወት፡አይኖርም፡አላቸው።ኢዩም፡ የበዓልን፡አገልጋዮች፡ያጠፋ፡ዘንድ፡በተንኰል፡ይህን፡አደረገ።
20ኢዩም፦ለበዓል፡ዋና፡ጉባኤ፡ቀድሱ፡አለ።
21እነርሱም፡ዐወጁ።ኢዩም፡ወደ፡እስራኤል፡ዅሉ፡ላከ፥የበዓልም፡አገልጋዮች፡ዅሉ፡መጡ፤ሳይመጣ፡ የቀረ፡አንድ፡ስንኳ፡አልነበረም።ወደበዓልም፡ቤት፡ገቡ፥የበዓልም፡ቤት፡ከዳር፡እስከ፡ዳር፡ድረስ፡ሞልቶ፡ ነበር፤
22ዕቃ፡ቤቱንም፦ለበዓል፡አገልጋዮች፡ዅሉ፡ልብስ፡አውጣ፡አለው።
23ልብሱንም፡አወጣላቸው፦ኢዩም፡የሬካብም፡ልጅ፡ኢዮናዳብ፡ወደበዓል፡ቤት፡ገቡ።የበዓልንም፡ አገልጋዮች፦መርምሩ፥ከበዓል፡አገልጋዮች፡ብቻ፡በቀር፡እግዚአብሔርን፡ከሚያመልኩ፡ወገን፡በእናንተ፡ ዘንድ፡አንድ፡እንኳ፡እንዳይኖር፡ተመልከቱ፡አላቸው።
24የሚቃጠል፡መሥዋዕትና፡ሌላ፡መሥዋዕትም፡ያቀረቡ፡ዘንድ፡ገቡ፤ኢዩም፦በእጃችኹ፡አሳልፌ፡ ከምሰጣችኹ፡ሰዎች፡አንድ፡ሰው፡ያመለጠ፡እንደ፡ኾነ፡ነፍሱ፡በዚያ፡ነፍስ፡ፋንታ፡ትኾናለች፡ብሎ፡በውጪ፡ ሰማንያ፡ሰዎችን፡አዘጋጅቶ፡ነበር።
25የሚቃጠለውንም፡መሥዋዕት፡አቅርበው፡በፈጸሙ፡ጊዜ፡ኢዩ፡ዘበኛዎቹንና፡አለቃዎቹን፦ግቡና፡ ግደሏቸው፤አንድም፡አይውጣ፡አላቸው።በሰይፍም፡ስለት፡ገደሏቸው፤ዘበኛዎችና፡አለቃዎችም፡ወደ፡ውጭ፡ ጣሏቸው፥ወደበዓልም፡ቤት፡ከተማ፡ኼዱ።
26ከበዓልም፡ቤት፡ሐውልቶቹን፡አወጡ፡አቃጠሏቸውም።
27የበዓልን፡ሐውልት፡ቀጠቀጡ፥የበዓልንም፡ቤት፡አፈረሱ፥እስከ፡ዛሬም፡ድረስ፡የውዳቂ፡መጣያ፡ አደረጉት።
28እንዲሁም፡ኢዩ፡በዓልን፡ከእስራኤል፡አጠፋ።
29ነገር፡ግን፥እስራኤልን፡ካሳተው፡ከናባጥ፡ልጅ፡ከኢዮርብዓም፡ኀጢአት፥በቤቴልና፡በዳን፡ከነበሩት፡ ከወርቁ፡እንቦሶች፥ኢዩ፡አልራቀም።
30እግዚአብሔርም፡ኢዩን፦በፊቴ፡ቅን፡ነገር፡አድርገኻልና፥በልቤም፡ያለውን፡ዅሉ፡በአክአብ፡ቤት፡ላይ፡ አድርገኻልና፥ልጆችኽ፡እስከ፡አራት፡ትውልድ፡ድረስ፡በእስራኤል፡ዙፋን፡ላይ፡ይቀመጣሉ፡አለው።
31ኢዩ፡ግን፡በእስራኤል፡አምላክ፡በእግዚአብሔር፡ሕግ፡በፍጹም፡ልቡ፡ይኼድ፡ዘንድ፡ አልተጠነቀቀም፤እስራኤልንም፡ካሳተው፡ከኢዮርብዓም፡ኀጢአት፡አልራቀም።
32በዚያም፡ወራት፡እግዚአብሔር፡እስራኤልን፡ይከፋፍላቸው፡ዘንድ፡ዠመረ፤አዛሄልም፡በእስራኤል፡ዳርቻ፡ ዅሉ፡መታቸው።
33በዮርዳኖስ፡ምሥራቅ፡ያለውን፡የገለዓድን፡አገር፡ዅሉ፥በአርኖን፡ወንዝ፡አጠገብ፡ካለችው፡ከዐሮዔር፡ ዠምሮ፡የጋድንና፡የሮቤልን፡የምናሴንም፡አገር፥ገለዓድንና፡ባሳንን፡መታ።
34የቀረውም፡የኢዩ፡ነገር፥የሠራውም፡ሥራ፡ዅሉ፥ጭከናውም፡ዅሉ፥በእስራኤል፡ነገሥታት፡ታሪክ፡ መጽሐፍ፡የተጻፈ፡አይደለምን፧
35ኢዩም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በሰማርያም፡ቀበሩት።በፋንታውም፡ልጁ፡ኢዮአካዝ፡ነገሠ።
36ኢዩም፡በሰማርያ፡በእስራኤል፡ላይ፡የነገሠበት፡ዘመን፡ኻያ፡ስምንት፡ዓመት፡ነበረ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org