Skip to content
← 2 Kings

Chapter 11 · Amharic

2 Kings

1የአካዝያስም፡እናት፡ጎቶልያ፡ልጇ፡እንደ፡ሞተ፡ባየች፡ጊዜ፡ተነሥታ፡የመንግሥትን፡ዘር፡ዅሉ፡አጠፋች።

2የንጉሡ፡የኢዮራም፡ልጅ፡የአካዝያስ፡እኅት፡ዮሳቤት፡የአካዝያስን፡ልጅ፡ኢዮአስን፡ወስዳ፡ከተገደሉት፡ ከንጉሥ፡ልጆች፡መካከል፡ሰረቀችው፤ርሱንና፡ሞግዚቱንም፡ወደ፡ዕልፍኝ፡ወሰደች፥እንዳይገደልም፡ከጎቶልያ፡ ሸሸጉት።

3በርሷም፡ዘንድ፡ተሸሽጎ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ስድስት፡ዓመት፡ያኽል፡ተቀመጠ።ጎቶልያም፡በምድር፡ ላይ፡ነገሠች።

4በሰባተኛውም፡ዓመት፡ዮዳዔ፡ልኮ፡በካራውያንና፡በዘበኛዎች፡ላይ፡ያሉትን፡የመቶ፡አለቃዎች፡ ወሰደ፥ወደእግዚአብሔርም፡ቤት፡አገባቸው፤ከነርሱም፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡አደረገ፥በእግዚአብሔርም፡ቤት፡ አማላቸው፥የንጉሡንም፡ልጅ፡አሳያቸው።

5እንዲህም፡ብሎ፡አዘዛቸው።እንዲህ፡አድርጉ፤በሰንበት፡ቀን፡ከምትገቡት፡ከእናንተ፡ከሦስት፡አንዱ፡እጅ፡ የንጉሡን፡ቤት፡ዘብ፡ጠብቁ፤

6ከእናንተ፡ከሦስት፡አንዱ፡እጅ፡በሱር፡በር፡ኹኑ፤አንዱም፡እጅ፡ከዘበኛዎች፡ቤት፡በዃላ፡ባለው፡በር፡ ኹኑ፤ቤቱንም፡ጠብቁ፥ከልክሉም፤

7ከእናንተም፡በሰንበት፡ቀን፡የምትወጡት፡ኹለቱ፡እጅ፡በንጉሥ፡ዙሪያ፡ኾናችኹ፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ ጠብቁ።

8ንጉሡንም፡በዙሪያው፡ክበቡት፥የጦር፡ዕቃችኹም፡በእጃችኹ፡ይኹን፤በሰልፋችኹ፡መካከል፡የሚገባ፡ ይገደል፤ንጉሡም፡በወጣና፡በገባ፡ጊዜ፡ከርሱ፡ጋራ፡ኹኑ።

9መቶ፡አለቃዎችም፡ካህኑ፡ዮዳዔ፡ያዘዘውን፡ዅሉ፡አደረጉ፤ከነርሱም፡እያንዳንዱ፡በሰንበት፡ይገቡ፡ የነበሩትን፥በሰንበቱም፡ይወጡ፡የነበሩትን፡ሰዎች፡ይዘው፡ወደ፡ካህኑ፡ወደ፡ዮዳዔ፡መጡ።

10ካህኑም፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡የነበረውን፡የንጉሡን፡የዳዊትን፡ጋሻና፡ጦር፡ዅሉ፡ለመቶ፡አለቃዎች፡ ሰጣቸው።

11ዘበኛዎቹም፡ዅሉ፡እያንዳንዳቸው፡የጦር፡ዕቃቸውን፡በእጃቸው፡ይዘው፡በንጉሡ፡ዙሪያ፡ከቤቱ፡ቀኝ፡ እስከ፡ቤቱ፡ግራ፡ድረስ፡በመሠዊያውና፡በቤቱ፡አጠገብ፡ቆሙ።

12የንጉሡንም፡ልጅ፡አውጥቶ፡ዘውዱን፡ጫነበት፥ምስክሩንም፡ሰጠው፤ቀብተውም፡ንጉሥ፡ አደረጉትና።ንጉሡ፡ሺሕ፡ዓመት፡ይንገሥ፡እያሉ፡እጃቸውን፡አጨበጨቡ።

13ጎቶልያም፡የሰራዊቱንና፡የሕዝቡን፡ድምፅ፡በሰማች፡ጊዜ፡ወደ፡ሕዝቡ፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡መጣች።

14እንሆም፥ንጉሡ፡እንደተለመደው፡በዐምዱ፡አጠገብ፡ቆሞ፥ከንጉሡም፡ጋራ፡አለቃዎችና፡መለከተኛዎች፡ ቆመው፡አየች፤የአገሩም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ደስ፡ብሏቸው፡ቀንደ፡መለከት፡ይነፉ፡ነበር።ጎቶልያም፡ልብሷን፡ ቀዳ፟፦ዐመፅ፡ነው፥ዐመፅ፡ነው፡ብላ፡ጮኸች።

15ካህኑም፡ዮዳዔ፡በጭፍራው፡ላይ፡የተሾሙትን፡የመቶ፡አለቃዎች፦ወደሰልፉ፡መካከል፡ አውጧት፤የሚከተላትንም፡በሰይፍ፡ግደሉት፡ብሎ፡አዘዛቸው፤ካህኑ፦በእግዚአብሔር፡ቤት፡አትገደል፡ ብሏልና።

16እጃቸውንም፡በርሷ፡ላይ፡ጫኑ፥በፈረሱም፡መግቢያ፡መንገድ፡ወደንጉሥ፡ቤት፡ወሰዷት፥በዚያም፡ ገደሏት።

17ዮዳዔም፡የእግዚአብሔር፡ሕዝብ፡ይኾኑ፡ዘንድ፡በእግዚአብሔርና፡በንጉሡ፡በሕዝቡም፡መካከል፡ቃል፡ ኪዳን፡አደረገ፤ደግሞም፡በንጉሡና፡በሕዝቡ፡መካከል፡ቃል፡ኪዳን፡አደረገ።

18የአገሩም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ወደበዓል፡ቤት፡ኼደው፡አፈረሱት፤መሠዊያዎቹንና፡ምስሎቹን፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org አደቀቁ፥የበዓልንም፡ካህን፡ማታንን፡በመሠዊያው፡ፊት፡ገደሉት።ካህኑም፡ለእግዚአብሔር፡ቤት፡ አስተዳዳሪዎችን፡ሾመ።

19መቶ፡አለቃዎቹንና፡ካራውያንንም፥ዘበኛዎችንና፡የአገሩንም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ወሰደ፤ንጉሡንም፡ ከእግዚአብሔር፡ቤት፡አወረዱት፥በዘበኛዎችም፡በር፡መንገድ፡ወደንጉሡ፡ቤት፡አመጡት፤በነገሥታቱም፡ ዙፋን፡ተቀመጠ።

20የአገሩም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ደስ፡አላቸው፥ከተማዪቱም፡ጸጥ፡አለች።ጎቶልያንም፡በንጉሡ፡ቤት፡አጠገብ፡ በሰይፍ፡ገደሏት።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source