Skip to content
← 2 Kings

Chapter 12 · Amharic

2 Kings

1ኢዮአስም፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የሰባት፡ዓመት፡ልጅ፡ነበረ።

2በኢዩ፡በሰባተኛው፡ዓመት፡ኢዮአስ፡መንገሥ፡ዠመረ፥በኢየሩሳሌምም፡አርባ፡ዓመት፡ነገሠ፤እናቱም፡ ሳብያ፡የተባለች፡የቤርሳቤሕ፡ሴት፡ነበረች።

3ካህኑ፡ዮዳዔም፡ያስተምረው፡በነበረ፡ዘመን፡ዅሉ፡ኢዮአስ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቅን፡ነገር፡አደረገ።

4ነገር፡ግን፥በኰረብታዎቹ፡ላይ፡ያሉት፡መስገጃዎች፡አልተወገዱም፤ሕዝቡም፡ገና፡በኰረብታዎቹ፡ላይ፡ ባሉት፡መስገጃዎች፡ይሠዋና፡ያጥን፡ነበር።

5ኢዮአስም፡ካህናቱን፦ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡የሚገባውን፡የተቀደሰውን፡ገንዘብ፡ዅሉ፥ስለነፍሱም፡ዋጋ፡ የሚቀርበውን፡ገንዘብ፥በልባቸውም፡ፈቃድ፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡የሚያመጡትን፡ገንዘብ፡ዅሉ፥

6ካህናቱ፡እያንዳንዱ፡ሰው፡ከሚያመጣው፡ይውሰዱ፡በመቅደስም፡ውስጥ፡የተናዱትን፡ይጠግኑበት፡አላቸው።

7ነገር፡ግን፥እስከ፡ንጉሡ፡እስከ፡ኢዮአስ፡እስከ፡ኻያ፡ሦስተኛው፡ዓመት፡ድረስ፡በመቅደሱ፡ውስጥ፡ የተናዱትን፡ካህናቱ፡አልጠገኑትም፡ነበር።

8ኢዮአስም፡ካህኑን፡ዮዳዔንና፡ካህናቱን፡ጠርቶ፦በመቅደሱ፡ውስጥ፡የተናዱትን፡ስፍራዎች፡ስለ፡ምን፡ አትጠግኗቸውም፧ከእንግዲህ፡ወዲያ፡ገንዘቡ፡ለቤቱ፡መጠገኛ፡ይሰጥ፡እንጂ፡ከሚያመጡት፡ሰዎች፡አትቀበሉ፡ አላቸው።

9ካህናቱም፦ከሕዝቡ፡ገንዘቡን፡አንወስድም፥በቤቱም፡ውስጥ፡የተናዱትን፡አንጠግንም፡ብለው፡ዕሺ፡አሉ።

10ካህኑ፡ዮዳዔ፡ግን፡ሣጥን፡ወስዶ፡መክደኛውን፡ነደለው፥በመሠዊያውም፡አጠገብ፡ወደእግዚአብሔር፡ ቤት፡በሚገቡበት፡መግቢያ፡በስተቀኝ፡አኖረው፤ደጁንም፡የሚጠብቁ፡ካህናት፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ የሚመጣውን፡ገንዘብ፡ዅሉ፡ያኖሩበት፡ነበር።

11በሣጥንም፡ውስጥ፡ብዙ፡ገንዘብ፡መኖሩን፡ባዩ፡ጊዜ፡የንጉሡ፡ጸሓፊና፡የካህናቱ፡አለቃ፡ይመጡ፡ ነበር፥በእግዚአብሔርም፡ቤት፡የተገኘውን፡ቈጥረው፡በከረጢት፡ውስጥ፡ያኖሩት፡ነበር።

12የተመዘነውንም፡ገንዘብ፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ለመሥራት፡በተሾሙት፡እጅ፡ይሰጡ፡ነበር።

13የተናደውን፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ለመጠገን፡መክፈል፡ለሚያሻው፡ዅሉ፡ድንጋይና፡ዕንጨት፡ይገዙ፡ ዘንድ፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ለሚሠሩ፡ዐናጢዎችና፡ሠራተኛዎች፡ግንበኛዎችና፡ድንጋይ፡ወቃሪዎች፡ይሰጡት፡ ነበር።

14ነገር፡ግን፥ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ከሚመጣው፡ገንዘብ፡ለእግዚአብሔር፡ቤት፡የሚኾኑ፡የብር፡ ጽዋዎችና፡ጕጠቶች፡ድስቶችም፡መለከቶችም፡የወርቅና፡የብር፡ዕቃዎችም፡አልተሠሩም፡ነበር።

15ነገር፡ግን፥ለሚሠሩት፡ይሰጡት፡ነበር፤የእግዚአብሔርንም፡ቤት፡ጠገኑበት።

16ለሠራተኛዎችም፡ይከፍሉ፡ዘንድ፡ገንዘቡን፡የሚወስዱትን፡ሰዎች፡አይቈጣጠሯቸውም፡ነበር፤በታማኝነት፡ ይሠሩ፡ነበርና። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

17ስለበደልና፡ሰለኀጢአት፡መሥዋዕት፡የቀረበውም፡ገንዘብ፡ለካህናት፡ነበረ፡እንጂ፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ አያገቡትም፡ነበር።

18በዚያም፡ወራት፡የሶርያ፡ንጉሥ፡አዛሄል፡ወጥቶ፡ጌትን፡ወጋ፥ያዘውም፤አዛሄልም፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ ለመውጣት፡ፊቱን፡አቀና።

19የይሁዳም፡ንጉሥ፡ኢዮአስ፡አባቶቹ፡የይሁዳ፡ነገሥታት፡ኢዮሳፍጥና፡ኢዮራም፡አካዝያስም፡የቀደሱትን፡ ቅዱስ፡ነገር፥ርሱም፡የቀደሰውን፥በእግዚአብሔርም፡ቤትና፡በንጉሡ፡ቤት፡መዛግብት፡የተገኘውን፡ወርቅ፡ ዅሉ፡ወሰደ፥ወደሶርያም፡ንጉሥ፡ወደ፡አዛሄል፡ላከው።ርሱም፡ከኢየሩሳሌም፡ተመለሰ።

20የቀረውም፡የኢዮአስ፡ነገር፥የሠራውም፡ሥራ፡ዅሉ፥በይሁዳ፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡ አይደለምን፧

21ባሪያዎቹም፡ተነሥተው፡ዐመፁበት፥ወደ፡ሲላ፡በሚወርደውም፡መንገድ፡በሚሎ፡ቤት፡ገደሉት።

22ባሪያዎቹም፡የሰምዓት፡ልጅ፡ዮዘካርና፡የሾሜር፡ልጅ፡ዮዛባት፡መቱት፥ሞተም፤በዳዊትም፡ከተማ፡ ከአባቶቹ፡ጋራ፡ቀበሩት፤ልጁም፡አሜስያስ፡በፋንታው፡ነገሠ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source