Skip to content
← 2 Kings

Chapter 13 · Amharic

2 Kings

1በይሁዳ፡ንጉሥ፡በአካዝያስ፡ልጅ፡በኢዮአስ፡በኻያ፡ሦስተኛው፡ዓመት፡የኢዩ፡ልጅ፡ኢዮአካዝ፡በእስራኤል፡ ላይ፡በሰማርያ፡ነገሠ፤ዐሥራ፡ሰባትም፡ዓመት፡ነገሠ።

2በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ክፉ፡ነገር፡አደረገ፥እስራኤልንም፡ያሳተውን፡የናባጥን፡ልጅ፡የኢዮርብዓምን፡ ኀጢአት፡ተከተለ፤ከርሷም፡አልራቀም።

3የእግዚአብሔርም፡ቍጣ፡በእስራኤል፡ላይ፡ነደደ፥በዘመኑም፡ዅሉ፡በሶርያው፡ንጉሥ፡በአዛሄል፡ እጅ፥በአዛሄልም፡ልጅ፡በወልደ፡አዴር፡እጅ፡አሳልፎ፡ይሰጣቸው፡ነበር።

4ኢዮአካዝም፡እግዚአብሔርን፡ለመነ፤እግዚአብሔርም፡የሶርያ፡ንጉሥ፡እስራኤልን፡ያስጨነቀበትን፡ጭንቀት፡ አይቷልና፥ሰማው።

5እግዚአብሔርም፡ለእስራኤል፡ታዳጊ፡ሰጠ፥ከሶርያውያንም፡እጅ፡ዳኑ፤የእስራኤልም፡ልጆች፡እንደ፡ ቀድሞው፡ጊዜ፡በድንኳናቸው፡ተቀመጡ።

6ነገር፡ግን፥በርሷ፡ኼዱ፡እንጂ፡እስራኤልን፡ካሳተው፡ከኢዮርብዓም፡ቤት፡ኀጢአት፡አልራቁም፤ደግሞም፡ የማምለኪያ፡ዐጸድ፡በሰማርያ፡ቆሞ፡ቀረ።

7ለኢዮአካዝም፡ከዐምሳ፡ፈረሰኛዎች፥ከዐሥርም፡ሠረገላዎች፥ከዐሥር፡ሺሕም፡እግረኛዎች፡በቀር፡ሕዝብ፡ አልቀረለትም፤የሶርያ፡ንጉሥ፡አጥፍቷቸዋልና፥በዐውድማም፡እንዳለ፡ዕብቅ፡አድቅቋቸዋልና።

8የቀረውም፡የኢዮአካዝ፡ነገር፥ያደረገውም፡ዅሉ፥ጭከናውም፥በእስራኤል፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡ የተጻፈ፡አይደለምን፧

9ኢዮአካዝም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በሰማርያም፡ቀበሩት፤ልጁም፡ዮአስ፡በፋንታው፡ነገሠ።

10በይሁዳ፡ንጉሥ፡በኢዮአስ፡በሠላሳ፡ሰባተኛው፡ዓመት፡የኢዮአካዝ፡ልጅ፡ዮአስ፡በእስራኤል፡ላይ፡ በሰማርያ፡ነገሠ፤ዐሥራ፡ስድስትም፡ዓመት፡ነገሠ።

11በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፋ፡ነገር፡አደረገ፤እስራኤልን፡በሳተው፡በናባጥ፡ልጅ፡በኢዮርብዓም፡ኀጢአት፡ ዅሉ፡ኼደ፡እንጂ፡ከርሷ፡አልራቀም።

12የቀረውም፡የዮአስ፡ነገር፥ያደረገውም፡ዅሉ፥ከይሁዳም፡ከአሜስያስ፡ጋራ፡የተዋጋበት፡ ጭከና፥በእስራኤል፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡አይደለምን፧

13ዮአስም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥ኢዮርብዓምም፡በዙፋኑ፡ላይ፡ተቀመጠ፤ዮአስም፡በሰማርያ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ከእስራኤል፡ነገሥታት፡ጋራ፡ተቀበረ።

14ኤልሳዕም፡በሚሞትበት፡በሽታ፡ታመመ፤የእስራኤልም፡ንጉሥ፡ዮአስ፡ወደ፡ርሱ፡ወርዶ፡በፊቱ፡ አለቀሰና፦አባቴ፡ሆይ፥አባቴ፡ሆይ፥የእስራኤል፡ሠረገላና፡ፈረሰኛዎች፡አለ።

15ኤልሳዕም፦ቀስትና፡ፍላጻዎች፡ውሰድ፡አለው፤ቀስቱንና፡ፍላጻዎችንም፡ወሰደ።

16የእስራኤልንም፡ንጉሥ፦እጅኽን፡በቀስቱ፡ላይ፡ጫን፡አለው።እጁንም፡ጫነበት፤ኤልሳዕም፡እጁን፡ በንጉሡ፡እጅ፡ላይ፡ጭኖ፦

17የምሥራቁን፡መስኮት፡ክፈት፡አለ፤ከፈተውም።ኤልሳዕም፦ወርውር፡ አለ፤ወረወረውም።ርሱም፦የእግዚአብሔር፡መድኀኒት፡ፍላጻ፡ነው፤በሶርያ፡ላይ፡የመድኀኒት፡ፍላጻ፡ ነው፤እስክታጠፋቸው፡ድረስ፡ሶርያውያንን፡በአፌቅ፡ትመታለኽ፡አለ።

18ደግሞም፦ፍላጻዎቹን፡ውሰድ፡አለው፤ወሰዳቸውም።የእስራኤልንም፡ንጉሥ፦ምድሩን፡ምታው፡ አለው።ሦስት፡ጊዜም፡መቶ፟፡ቆመ።

19የእግዚአብሔርም፡ሰው፡ተቈጥቶ፦ዐምስት፡ወይም፡ስድስት፡ጊዜ፡መትተኸው፡ኖሮ፡ሶርያን፡ እስክታጠፋው፡ድረስ፡በመታኸው፡ነበር፤አኹን፡ግን፡ሦስት፡ጊዜ፡ብቻ፡ሶርያን፡ትመታለኽ፡አለ።

20ኤልሳዕም፡ሞተ፥ቀበሩትም።ከሞዐብም፡አደጋ፡ጣዮች፡በየዓመቱ፡ወደ፡አገሩ፡ይገቡ፡ነበር።

21ሰዎችም፡አንድ፡ሰው፡ሲቀብሩ፡አደጋ፡ጣዮችን፡አዩ፥ሬሳውንም፡በኤልሳዕ፡መቃብር፡ ጣሉት፤የኤልሳዕንም፡ዐጥንት፡በነካ፡ጊዜ፡ሰውዮው፡ድኖ፡በእግሩ፡ቆመ።

22የሶርያም፡ንጉሥ፡አዛሄል፡በኢዮአካዝ፡ዘመን፡ዅሉ፡እስራኤልን፡አስጨነቀ፤

23እግዚአብሔር፡ግን፡ራራላቸው፥ማራቸውም፥ከአብርሃምና፡ከይሥሐቅ፡ከያዕቆብም፡ጋራ፡ስላደረገውም፡ ቃል፡ኪዳን፡እነርሱን፡ተመለከተ፤ሊያጠፋቸውም፡አልወደደም፥ፈጽሞም፡ከፊቱ፡አልጣላቸውም።

24የሶርያም፡ንጉሥ፡አዛሄል፡ሞተ፤ልጁም፡ወልደ፡አዴር፡በፋንታው፡ነገሠ።

25አዛሄልም፡ከአባቱ፡ከኢዮአካዝ፡እጅ፡በሰልፍ፡የወሰዳቸውን፡ከተማዎች፡የኢዮአካዝ፡ልጅ፡ዮአስ፡ ከአዛሄል፡ልጅ፡ከወልደ፡አዴር፡እጅ፡ወሰደ።ዮአስም፡ሦስት፡ጊዜ፡መታው፥የእስራኤልንም፡ከተማዎች፡ መለሰ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source