Skip to content
← 2 Kings

Chapter 14 · Amharic

2 Kings

1በእስራኤል፡ንጉሥ፡በኢዮአካዝ፡ልጅ፡በዮአስ፡በኹለተኛው፡ዓመት፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡የኢዮአስ፡ልጅ፡ አሜስያስ፡ነገሠ።

2መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የኻያ፡ዐምስት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፤በኢየሩሳሌምም፡ኻያ፡ዘጠኝ፡ዓመት፡ ነገሠ።እናቱም፡ዮዓዳን፡የተባለች፡የኢየሩሳሌም፡ሴት፡ነበረች።

3በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ቅን፡ነገር፡አደረገ፤ነገር፡ግን፥አባቱ፡ኢዮአስ፡እንዳደረገ፡ዅሉ፡እንጂ፡እንደ፡ አባቱ፡እንደ፡ዳዊት፡አላደረገም።

4ነገር፡ግን፥በኰረብታዎቹ፡ላይ፡ያሉት፡መስገጃዎች፡አልተወገዱም፤ሕዝቡም፡ገና፡በኰረብታዎች፡ላይ፡ ባሉት፡መስገጃዎች፡ይሠዋና፡ያጥን፡ነበር።

5መንግሥቱም፡በጸናለት፡ጊዜ፡አባቱን፡የገደሉትን፡ባሪያዎች፡ገደለ።

6በሙሴ፡ሕግ፡መጽሐፍም፡እንደ፡ተጻፈ፥እግዚአብሔርም፦ዅሉ፡በኀጢአቱ፡ይሙት፡እንጂ፡አባቶች፡ በልጆች፡አይሙቱ፥ልጆችም፡በአባቶች፡አይሙቱ፡ብሎ፡እንዳዘዘ፡የነፍሰ፡ገዳዮቹን፡ልጆች፡አልገደለም።

7ርሱም፡በጨው፡ሸለቆ፡ከኤዶምያስ፡ዐሥር፡ሺሕ፡ሰው፡ገደለ፤ሴላን፡በሰልፍ፡ወስዶ፡ስሟን፡እስከ፡ዛሬ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ድረስ፡ዮቅትኤል፡ብሎ፡ጠራት።

8በዚያን፡ጊዜም፡አሜስያስ፦ና፡ርስ፡በርሳችን፡ፊት፡ለፊት፡እንተያይ፡ብሎ፡ወደእስራኤል፡ንጉሥ፡ ወደኢዩ፡ልጅ፡ወደኢዮአካዝ፡ልጅ፡ወደ፡ዮአስ፡መልእክተኛዎችን፡ላከ።

9የእስራኤልም፡ንጉሥ፡ዮአስ፦የሊባኖስ፡ኵርንችት፥ልጅኽን፡ለልጄ፡ሚስት፡አድርገኽ፡ስጠው፡ብሎ፡ ወደሊባኖስ፡ዝግባ፡ላከ፤የሊባኖስም፡አውሬ፡ዐልፎ፡ኵርንችቱን፡ረገጠ።

10ኤዶምያስን፡በእውነት፡መታኽ፥ልብኽንም፡ከፍ፡ከፍ፡አደረግኽ፤በዚያ፡ተመካ፥በቤትኽም፡ ተቀመጥ፤አንተ፡ከይሁዳ፡ጋራ፡ትወድቅ፡ዘንድ፡ስለ፡ምን፡መከራ፡ትሻለኽ፧ብሎ፡ወደይሁዳ፡ንጉሥ፡ወደ፡ አሜስያስ፡ላከ።

11አሜስያስ፡ግን፡አልሰማም፤የእስራኤልም፡ንጉሥ፡ዮአስ፡ወጣ፥ርሱና፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡አሜስያስም፡ በይሁዳ፡ባለች፡በቤት፡ሳሚስ፡ርስ፡በርሳቸው፡ተያዩ።

12ይሁዳም፡በእስራኤል፡ፊት፡ተመታ፤እያንዳንዱም፡ወደ፡ድንኳኑ፡ሸሸ።

13የእስራኤልም፡ንጉሥ፡ዮአስ፡የይሁዳን፡ንጉሥ፡የአካዝያስን፡ልጅ፡የኢዮአስን፡ልጅ፡አሜስያስን፡ በቤትሳሚስ፡ይዞ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡መጣ፤የኢየሩሳሌምንም፡ቅጥር፡ከኤፍሬም፡በር፡ዠምሮ፡እስክ፡ማእዘኑ፡ በር፡ድረስ፡አራት፡መቶ፡ክንድ፡አፈረሰ።

14ወርቁንና፡ብሩን፡ዅሉ፥በእግዚአብሔርም፡ቤትና፡በንጉሡ፡ቤት፡መዛግብት፡የነበሩትን፡ዕቃዎች፡ ዅሉ፥በመያዣም፡የተያዙትን፡ወስዶ፡ወደ፡ሰማርያ፡ተመለሰ።

15የቀረውም፡ያደረገው፡የዮአስ፡ነገር፥ጭከናውም፥ከይሁዳም፡ንጉሥ፡ከአሜስያስ፡ጋራ፡እንደ፡ ተዋጋ፥በእስራኤል፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡አይደለምን፧

16ዮአስም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በሰማርያም፡ከእስራኤል፡ነገሥታት፡ጋራ፡ተቀበረ፤ልጁም፡ ኢዮርብዓም፡በፋንታው፡ነገሠ።

17የይሁዳም፡ንጉሥ፣የኢዮአስ፡ልጅ፣አሜስያስ፥ከእስራኤል፡ንጉሥ፣ከኢዮአካዝ፡ልጅ፣ከዮአስ፡ሞት፡ በዃላ፡ዐሥራ፡ዐምስት፡ዓመት፡ኖረ።

18የቀረውም፡የአሜስያስ፡ነገር፡በይሁዳ፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡አይደለምን፧

19በኢየሩሳሌምም፡የዐመፅ፡መሐላ፡አደረጉበት፥ርሱም፡ወደ፡ለኪሶ፡ኰበለለ፤በዃላውም፡ወደ፡ለኪሶ፡ ላኩ፥በዚያም፡ገደሉት።

20በፈረስም፡ጭነው፡አመጡት፥በኢየሩሳሌምም፡በዳዊት፡ከተማ፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡ተቀበረ። ንጉሡም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡ካንቀላፋ፡በዃላ፥ኤላትን፡ሠርቶ፡ወደ፡ይሁዳ፡መለሳት።

21የይሁዳም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡የዐሥራ፡ስድስት፡ዓመት፡ልጅ፡የነበረውን፡ዐዛርያስን፡ወስዶ፡በአባቱ፡ በአሜስያስ፡ፋንታ፡አነገሠው።

23በይሁዳ፡ንጉሥ፡በኢዮአስ፡ልጅ፡በአሜስያስ፡በዐሥራ፡ዐምስተኛው፡ዓመት፡የእስራኤል፡ንጉሥ፡የዮአስ፡ ልጅ፡ኢዮርብዓም፡በሰማርያ፡መንገሥ፡ዠመረ፤አርባ፡አንድ፡ዓመትም፡ነገሠ።

24በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ክፉ፡ነገር፡አደረገ፤እስራኤልንም፡ካሳተው፡ከናባጥ፡ልጅ፡ከኢዮርብዓም፡ ኀጢአት፡ዅሉ፡አልራቀም።

25የጋትሔፌር፡በነበረው፡በዐማቴ፡ልጅ፡በባሪያው፡በነቢዩ፡በዮናስ፡እጅ፡እንደተናገረው፡እንደ፡እስራኤል፡ አምላክ፡እንደእግዚአብሔር፡ቃል፡የእስራኤልን፡ድንበር፡ከሐማት፡መግቢያ፡ዠምሮ፡እስከዐረባ፡ባሕር፡ድረስ፡ መለሰ።

26የታሰረውና፡የተለቀቀውም፡እንደ፡ጠፋ፥እስራኤልንም፡የሚረዳ፡እንዳልነበረ፡እግዚአብሔር፡እጅግ፡ የመረረውን፡የእስራኤልን፡ጭንቀት፡አየ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

27እግዚአብሔርም፡የእስራኤልን፡ስም፡ከሰማይ፡በታች፡ይደመስስ፡ዘንድ፡አልተናገረም፤ነገር፡ግን፥በዮአስ፡ ልጅ፡በኢዮርብዓም፡እጅ፡አዳናቸው።

28የቀረውም፡የኢዮርብዓም፡ነገር፥ያደረገውም፡ዅሉ፥ጭከናውም፥እንደ፡ተዋጋም፥የይሁዳ፡የነበረውን፡ ደማስቆንና፡ሐማትን፡ለእስራኤል፡እንደ፡መለሰ፥በእስራኤል፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡አይደለምን፧

29ኢዮርብዓምም፡ከአባቶቹ፡ከእስራኤል፡ነገሥታት፡ጋራ፡አንቀላፋ፤ልጁም፡ዘካርያ፡በፋንታው፡ነገሠ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source