Skip to content
← 2 Kings

Chapter 15 · Amharic

2 Kings

1በእስራኤል፡ንጉሥ፡በኢዮርብዓም፡በኻያ፡ሰባተኛው፡ዓመት፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡የአሜስያስ፡ልጅ፡ዐዛርያስ፡ ነገሠ።

2መንገሥም፡በዠመረ፡ጊዜ፡የዐሥራ፡ስድስት፡ዓመት፡ልጅ፡ነበረ፤በኢየሩሳሌምም፡ዐምሳ፡ኹለት፡ዓመት፡ ነገሠ፤እናቱም፡ይኮልያ፡የተባለች፡የኢየሩሳሌም፡ሴት፡ነበረች።

3አባቱ፡አሜስያስ፡እንዳደረገው፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቅን፡ነገር፡አደረገ።

4ነገር፡ግን፥በኰረብታዎች፡ላይ፡ያሉት፡መስገጃዎች፡አልተወገዱም፤ሕዝቡም፡ገና፡በኰረብታዎች፡ላይ፡ ባሉት፡መስገጃዎች፡ይሠዋና፡ያጥን፡ነበር።

5እግዚአብሔርም፡ንጉሡን፡ቀሠፈው፥እስከሚሞትበትም፡ቀን፡ድረስ፡ለምጻም፡ኾነ፥በተለየ፡ቤትም፡ ይቀመጥ፡ነበር፥የንጉሡም፡ልጅ፡ኢዮአታም፡በንጉሥ፡ቤት፡ላይ፡ሠልጥኖ፡ለአገሩ፡ሕዝብ፡ይፈርድ፡ነበር።

6የቀረውም፡የዐዛርያስ፡ነገር፥የሠራውም፡ሥራ፡ዅሉ፥በይሁዳ፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡ አይደለምን፧

7ዐዛርያስም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በዳዊትም፡ከተማ፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡ቀበሩት፤ልጁም፡ኢዮአታም፡ በርሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።

8በይሁዳ፡ንጉሥ፡በዐዛርያስ፡በሠላሳ፡ስምንተኛው፡ዓመት፡የኢዮርብዓም፡ልጅ፡ዘካርያስ ፡በእስራኤል፡ላይ፡ በሰማርያ፡ስድስት፡ወር፡ነገሠ።

9አባቶቹም፡እንዳደረጉት፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡ነገር፡አደረገ፤እስራኤልን፡ካሳታቸው፡ከናባጥ፡ልጅ፡ ከኢዮርብዓም፡ኀጢአት፡አልራቀም።

10የኢያቤስ ም፡ልጅ፡ሰሎም፡ተማማለበት፥በይብልዓም፡መቶ፟፡ገደለው፥በርሱም፡ፋንታ፡ነገሠ።

11የቀረውም፡የዘካርያ፡ነገር፥እንሆ፥በእስራኤል፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡ተጽፏል።

12ለኢዩ፦ልጆችኽ፡እስከ፡አራት፡ትውልድ፡ድረስ፡በእስራኤል፡ዙፋን፡ላይ፡ይቀመጣሉ፡ተብሎ፡ የተነገረው፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ይህ፡ነበረ፤እንዲሁም፡ኾነ።

13በይሁዳ፡ንጉሠ፡በዖዝያን፡በሠላሳ፡ዘጠነኛው፡ዓመት፡የኢያቤስ፡ልጅ፡ሰሎም፡ነገሠ፤በሰማርያም፡አንድ፡ ወር፡ያኽል፡ነገሠ።

14የጋዲም፡ልጅ፡ምናሔም፡ከቴርሳ፡ወጥቶ፡ወደ፡ሰማርያ፡መጣ፥በሰማርያም፡የኢያቤስን፡ልጅ፡ሰሎምን፡ መታ፥ገደለውም፤በርሱም፡ፋንታ፡ነገሠ።

15የቀረውም፡የሰሎም፡ነገር፥የተማማለውም፡ዐመፅ፥እንሆ፥በእስራኤል፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡ ተጽፏል።

16በዚያን፡ጊዜም፡ምናሔም፡ከቴርሳ፡ወጥቶ፡ቲፍሳን፡በርሷም፡ያሉትን፡ዅሉ፡ዳርቻዋንም፡ መታ፤ይከፍቱለትም፡ዘንድ፡አልወደዱምና፡መታት፤በርሷም፡የነበሩትን፡እርጕዞች፡ዅሉ፡ቀደዳቸው። 171 ዕብ.፥ዘካርያህ። 172 ዕብ.፥ያቤሽ፡(ይቡስ•የደረቀ)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

17በይሁዳ፡ንጉሥ፡በዐዛርያስ፡በሠላሳ፡ዘጠነኛው፡ዓመት፡የጋዲ፡ልጅ፡ምናሔም፡በእስራኤል፡ላይ፡መንገሥ፡ ዠመረ፤በሰማርያም፡ዐሥር፡ዓመት፡ነገሠ።

18በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ክፉ፡ነገር፡አደረገ፤እስራኤልን፡ካሳተው፡ከናባጥ፡ልጅ፡ከኢዮርብዓም፡ኀጢአት፡ አልራቀም።

19በዘመኑም፡የአሶር፡ንጉሥ፡ፎሐ ፡በምድሪቱ፡ላይ፡ወጣ፤ምናሔምም፡መንግሥቱን፡በእጁ፡ያጸናለት፡ ዘንድ፡የፎሐ፡እጅ፡ከርሱ፡ጋራ፡እንዲኾን፡አንድ፡ሺሕ፡መክሊት፡ብር፡ሰጠው።

20ምናሔምም፡ብሩን፡ለአሶር፡ንጉሥ፡ይሰጥ፡ዘንድ፡በእስራኤል፡ባለጠጋዎች፡ዅሉ፡ላይ፡በያንዳንዱ፡ላይ፡ ዐምሳ፡ሰቅል፡ብር፡አስገብሮ፡አወጣ።የአሶርም፡ንጉሥ፡ተመለሰ፥በአገሪቱም፡አልተቀመጠም።

21የቀረውም፡የምናሔም፡ነገር፥የሠራውም፡ሥራ፡ዅሉ፥በእስራኤል፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡ አይደለምን፧

22ምናሔም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፤ልጁም፡ፋቂስያስ፡በርሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።

23በይሁዳ፡ንጉሥ፡በዐዛርያስ፡በዐምሳኛው፡ዓመት፡የምናሔም፡ልጅ፡ፋቂስያስ፡በእስራኤል፡ላይ፡በሰማርያ፡ መንገሥ፡ዠመረ፤ኹለት፡ዓመትም፡ነገሠ።

24በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ክፉ፡ነገር፡አደረገ፤እስራኤልን፡ካሳተው፡ከናባጥ፡ልጅ፡ከኢዮርብዓም፡ኀጢአት፡ አልራቀም።

25የሰራዊቱም፡አለቃ፡የሮሜልዩ፡ልጅ፡ፋቁሔ፡ተማማለበት፥በሰማርያም፡በንጉሡ፡ቤት፡ግንብ፡ውስጥ፡ ከአርጎብና፡ከአርያ፡ጋራ፡መታው፤ከርሱም፡ጋራ፡ዐምሳ፡የገለዓድ፡ሰዎች፡ነበሩ፤ገደለውም፥፥በርሱም፡ ፋንታ፡ነገሠ።

26የቀረውም፡የፋቂስያስ፡ነገር፥የሠራውም፡ሥራ፡ዅሉ፥እንሆ፥በእስራኤል፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡ ተጽፏል።

27በይሁዳ፡ንጉሥ፡በዐዛርያስ፡በዐምሳ፡ኹለተኛው፡ዓመት፡የሮሜልዩ፡ልጅ፡ፋቁሔ፡በእስራኤል፡ላይ፡ በሰማርያ፡መንገሥ፡ዠመረ፤ኻያ፡ዓመትም፡ነገሠ።

28በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ክፉ፡ነገር፡አደረገ፤እስራኤልን፡ካሳተው፡ከናባጥ፡ልጅ፡ከኢዮርብዓም፡ኀጢአት፡ አልራቀም።

29በእስራኤልም፡ንጉሥ፡በፋቁሔ፡ዘመን፡የአሶር፡ንጉሥ፡ቴልጌልቴልፌልሶር፡መጥቶ፡ዒዮንና፡ አቤልቤትመዓካን፥ያኖዋንም፥ቃዴስንና፡አሶርንም፥ገለዓድንና፡ገሊላንም፥የንፍታሌምን፡አገር፡ዅሉ፡ ወሰደ፤ወደ፡አሶርም፡አፈለሳቸው።

30በዖዝያንም፡ልጅ፡በኢዮአታም፡በኻያኛው፡ዓመት፡የኤላ፡ልጅ፡ሆሴዕ፡በሮሜልዩ፡ልጅ፡በፋቁሔ፡ላይ፡ ተማማለ፥መቶ፟ም፡ገደለው፥በርሱም፡ፋንታ፡ነገሠ።

31የቀረውም፡የፋቁሔ፡ነገር፥የሠራውም፡ሥራ፡ዅሉ፥እንሆ፥በእስራኤል፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡ ተጽፏል።

32በእስራኤል፡ንጉሥ፡በሮሜልዩ፡ልጅ፡በፋቁሔ፡በኹለተኛው፡ዓመት፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡የዖዝያን፡ልጅ፡ ኢዮአታም፡ነገሠ።

33መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የኻያ፡ዐምስት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፥በኢየሩሳሌምም፡ዐሥራ፡ስድስት፡ ዓመት፡ነገሠ፤እናቱ፡የሳዶቅ፡ልጅ፡ኢየሩሳ ፡ነበረች።

34በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቅን፡ነገር፡አደረገ፤አባቱ፡ዖዝያን፡እንዳደረገ፡ዅሉ፡እንዲሁ፡አደረገ። 173 ፉል፥ወይም፡ፑል። 174 ዕብ፡፥የሩሻህ፡(ርስት•የተወረሰች)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

35ነገር፡ግን፥በኰረብታዎች፡ላይ፡ያሉት፡መስገጃዎች፡አልተወገዱም፤ሕዝቡም፡ገና፡በኰረብታዎች፡ላይ፡ ባሉት፡መስገጃዎች፡ይሠዋና፡ያጥን፡ነበር።ርሱም፡የላይኛውን፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡በር፡ሠራ።

36የቀረውም፡የኢዮአታም፡ነገር፥የሠራውም፡ሥራ፡ዅሉ፥በይሁዳ፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡ አይደለምን፧

37በዚያም፡ወራት፡እግዚአብሔር፡የሶርያን፡ንጉሥ፡ረአሶንንና፡የሮሜልዩን፡ልጅ፡ፋቁሔን፡በይሁዳ፡ላይ፡ መስደድ፡ዠመረ።

38ኢዮአታም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በአባቱም፡በዳዊት፡ከተማ፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡ተቀበረ፤ልጁም፡ አካዝ ፡በርሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source