1በሮሜልዩ፡ልጅ፡በፋቁሔ፡በዐሥራ፡ሰባተኛው፡ዓመት፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡የኢዮአታም፡ልጅ፡አካዝ፡ነገሠ።
2አካዝ፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የኻያ፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፤በኢየሩሳሌምም፡ዐሥራ፡ስድስት፡ዓመት፡ ነገሠ፤እንደ፡አባቱም፡እንደ፡ዳዊት፡በአምላኩ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቅን፡ነገር፡አላደረገም።
3ነገር፡ግን፥በእስራኤል፡ነገሥታት፡መንገድ፡ኼደ፤ደግሞም፡እግዚአብሔር፡ከእስራኤል፡ልጆች፡ፊት፡ እንዳሳደዳቸው፡እንደ፡አሕዛብ፡ርኵሰት፡ልጁን፡በእሳት፡አሳለፈው።
4በመስገጃዎችና፡በኰረብታዎቹ፡ላይ፡በለመለመውም፡ዛፍ፡ዅሉ፡በታች፡ይሠዋና፡ያጥን፡ነበር።
5የዚያን፡ጊዜም፡የሶርያ፡ንጉሥ፡ረአሶንና፡የእስራኤል፡ንጉሥ፡የሮሜልዩ፡ልጅ፡ፋቁሔ፡ሊዋጉ፡ወደ፡ ኢየሩሳሌም፡መጡ፤አካዝንም፡ከበቡት፥ሊያሸንፉት፡ግን፡አልቻሉም።
6በዚያም፡ዘመን፡የሶርያ፡ንጉሥ፡ረአሶን፡ኤላትን፡ወደ፡ሶርያ፡መለሰ፥አይሁድንም፡ከኤላት፡ አሳደደ፤ኤዶማውያንም፡ወደ፡ኤላት፡መጥተው፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡በርሷ፡ተቀምጠዋል።
7አካዝም፦እኔ፡ባሪያኽና፡ልጅኽ፡ነኝ፤መጥተኽ፡ከተነሡብን፡ከሶርያ፡ንጉሥና፡ከእስራኤል፡ንጉሥ፡እጅ፡ አድነኝ፡ብሎ፡ወደአሶር፡ንጉሥ፡ወደ፡ቴልጌልቴልፌልሶር፡መልእክተኛዎችን፡ላከ።
8አካዝም፡በእግዚአብሔር፡ቤትና፡በንጉሡ፡ቤት፡መዛግብት፡የተገኘውን፡ብርና፡ወርቅ፡ወስዶ፡ወደአሶር፡ ንጉሥ፡ገጸ፡በረከት፡አድርጎ፡ሰደደው።
9የአሶርም፡ንጉሥ፡ሰማው፤የአሶርም፡ንጉሥ፡በደማስቆ፡ላይ፡ወጣባት፡ወሰዳትም፥ሕዝቧንም፡ወደ፡ቂር፡ አፈለሳቸው፥ረአሶንንም፡ገደለ።
10ንጉሡም፡አካዝ፡የአሶርን፡ንጉሠ፡ቴልጌልቴልፌልሶርን፡ሊገናኘው፡ወደ፡ደማስቆ፡ኼደ፤በደማስቆ፡ የነበረውን፡መሠዊያ፡አየ፤ንጉሡም፡አካዝ፡የመሠዊያውን፡ምሳሌና፡የአሠራሩን፡መልክ፡ወደ፡ካህኑ፡ወደ፡ ኦርያ፡ላከው።
11ካህኑም፡ኦርያ፡መሠዊያ፡ሠራ፤ንጉሡ፡አካዝ፡ከደማስቆ፡ልኮ፡እንዳዘዘው፡ዅሉ፡እንዲሁ፡ካህኑ፡ኦርያ፡ ንጉሡ፡አካዝ፡ከደማስቆ፡እስኪመጣ፡ድረስ፡ሠራው።
12ንጉሡም፡ከደማስቆ፡በመጣ፡ጊዜ፡መሠዊያውን፡አየ፤ንጉሡም፡ወደ፡መሠዊያው፡ቀርቦ፡በርሱ፡ላይ፡ ወጣ።
13በመሠዊያውም፡ላይ፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕትና፡የእኽሉን፡ቍርባን፡አሳረገ፥የመጠጡንም፡ቍርባን፡ አፈሰሰ፥የደኅንነቱንም፡መሥዋዕት፡ደም፡ረጨ።
14በእግዚአብሔርም፡ፊት፡የነበረውን፡የናሱን፡መሠዊያ፡ከመቅደሱ፡ፊት፡ከመሠዊያውና፡ከእግዚአብሔር፡ ቤት፡መካከል፡ፈቀቅ፡አድርጎ፡በመሠዊያው፡አጠገብ፡በሰሜን፡በኩል፡አኖረው። 175 ዕብ.፥አኃዝ፡(አኃዚ፥ያዥ፣ጠባቂ፣መጋቢ)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
15ንጉሡም፡አካዝ፦የሚቃጠለውን፡የጧት፡መሥዋዕት፥የማታውንም፡የእኽሉን፡ቍርባን፥የንጉሡንም፡ የሚቃጠለውን፡መሥዋዕትና፡የእኽሉን፡ቍርባን፥ለአገሩም፡ሕዝብ፡የሚኾን፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕትና፡ የእኽሉን፡የመጠጡንም፡ቍርባን፡በታላቁ፡መሠዊያ፡ላይ፡አቅርብ፤የሚቃጠለውንም፡መሥዋዕት፡ደም፡ዅሉ፡ የሌላ፡መሥዋዕቱንም፡ደም፡ዅሉ፡ርጭበት፤የናሱ፡መሠዊያ፡ግን፡እኔ፡እጠይቅበት፡ዘንድ፡ይኹን፡ብሎ፡ ካህኑን፡ኦርያን፡አዘዘው።
16ካህኑ፡ኦርያ፡ንጉሡ፡አካዝ፡እንዳዘዘው፡ዅሉ፡እንዲሁ፡አደረገ።
17ንጉሡም፡አካዝ፡የመቀመጫዎችን፡ክፈፍ፡ቈረጠ፥ከነርሱም፡የመታጠቢያውን፡ሰኖች፡ወሰደ፤ኵሬውንም፡ ከበታቹ፡ከነበሩት፡ከናሱ፡በሬዎች፡አወረደው፥በጠፍጣፋውም፡ድንጋይ፡ላይ፡አኖረው።
18በእግዚአብሔርም፡ቤት፡የዙፋኑን፡መሠረት፡ሠራ፤ስለአሶርም፡ንጉሥ፡በውጭ፡ያለውን፡የንጉሡን፡ መንገድ፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡አዞረው።
19የቀረውም፡አካዝ፡ያደረገው፡ነገር፡በይሁዳ፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡አይደለምን፧
20አካዝም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በዳዊትም፡ከተማ፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡ተቀበረ፤ልጁም፡ሕዝቅያስ፡በርሱ፡ ፋንታ፡ነገሠ።