Skip to content
← 2 Kings

Chapter 17 · Amharic

2 Kings

1በይሁዳ፡ንጉሥ፡በአካዝ፡በዐሥራ፡ኹለተኛው፡ዓመት፡የኤላ፡ልጅ፡ሆሴዕ፡በእስራኤል፡ላይ፡በሰማርያ፡ ንጉሥ፡ኾነ፤ዘጠኝ፡ዓመትም፡ነገሠ።

2በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ክፉ፡ነገር፡አደረገ፤ነገር፡ግን፥ከርሱ፡አስቀድሞ፡እንደ፡ነበሩት፡እንደ፡እስራኤል፡ ነገሥታት፡አይደለም።

3የአሶርም፡ንጉሥ፡ስልምናሶር፡በርሱ፡ላይ፡ወጣ፤ሆሴዕም፡ተገዛለት፥ግብርም፡አመጣለት።

4የአሶርም፡ንጉሥ፡በሆሴዕ፡ላይ፡ዐመፅ፡አገኘ፤መልእክተኛዎችን፡ወደግብጽ፡ንጉሥ፡ወደ፡ሴጎር፡ልኮ፡ ነበርና፤እንደ፡ልማዱም፡በየዓመቱ፡ለአሶር፡ንጉሥ፡ግብር፡አልሰጠምና፤ስለዚህ፥የአሶር፡ንጉሥ፡ይዞ፡በወህኒ፡ ቤት፡አሰረው።

5የአሶርም፡ንጉሥ፡በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡ወጣ፥ወደ፡ሰማርያም፡ወጥቶ፡ሦስት፡ዓመት፡ከበባት።

6በሆሴዕ፡በዘጠነኛው፡ዓመት፡የአሶር፡ንጉሥ፡ሰማርያን፡ወሰደ፥እስራኤልንም፡ወደ፡አሶር፡ አፈለሰ፥በአላሔና፡በአቦር፡በጎዛንም፡ወንዝ፡በሜዶንም፡ከተማዎች፡አኖራቸው።

7የእስራኤልም፡ልጆች፡ከግብጽ፡ንጉሥ፡ከፈርዖን፡እጅ፥ከግብጽ፡ምድር፡ያወጣቸውን፡አምላካቸውን፡ እግዚአብሔርን፡በድለው፡ነበርና፥ሌላዎችንም፡አማልክት፡አምልከው፡ነበርና፥

8እግዚአብሔርም፡ከእስራኤል፡ልጆች፡ፊት፡ባሳደዳቸው፡በአሕዛብ፡ሥርዐት፥የእስራኤልም፡ነገሥታት፡ ባደረጓት፡ሥርዐት፡ኼደው፡ነበርና፥እንደዚህ፡ኾነ።

9የእስራኤልም፡ልጆች፡በአምላካቸው፡በእግዚአብሔር፡ላይ፡ቅን፡ያልኾነን፡ንገር፡በስውር፡ አደረጉ፤በከተማዎቻቸውም፡ዅሉ፡ከዘበኛዎች፡ግንብ፡ዠምሮ፡እስከተመሸገች፡ከተማ፡ድረስ፡በከፍታዎቹ፡ ላይ፡መስገጃዎችን፡ሠሩ።

10በረዣዥሙ፡ኰረብታ፡ዅሉ፡ላይ፡በለመለመውም፡ዛፍ፡ዅሉ፡ታች፡ሐውልቶችንና፡የማምለኪያ፡ ዐጸዶችን፡ተከሉ፤

11እግዚአብሔርም፡ከፊታቸው፡ያወጣቸው፡አሕዛብ፡እንዳደረጉት፥በኰረብታዎቹ፡መስገጃዎች፡ዅሉ፡ላይ፡ ያጥኑ፡ነበር፤እግዚአብሔርንም፡ያስቈጡ፡ዘንድ፡ክፉ፡ነገር፡አደረጉ፤

12እግዚአብሔርም፡የከለከላቸውን፡ጣዖቶች፡አመለኩ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

13እግዚአብሔርም፦ከክፉ፡መንገዳችኹ፡ተመለሱ፤ለአባቶቻችኹም፡እንዳዘዝኹት፥በባሪያዎቼ፡በነቢያት፡ የላክኹላችኹን፡ትእዛዜንና፡ሥርዐቴን፡ሕጌንም፡ዅሉ፡ጠብቁ፡ብሎ፡በነቢዩ፡ዅሉና፡በባለራእዩ፡አፍ፡ዅሉ፡ በእስራኤልና፡በይሁዳ፡መሰከረ።

14ነገር፡ግን፥አምላካቸውን፡እግዚአብሔርን፡እንዳላመኑ፡እንደ፡አባቶቻቸው፡ዐንገት፡ዐንገታቸውን፡ አደነደኑ፡እንጂ፡አልሰሙም።

15ሥርዐቱንም፡ከአባቶቻቸውም፡ጋራ፡ያደረገውን፡ቃል፡ኪዳን፥ያጸናላቸውንም፡ምስክሩን፡ናቁ፤ከንቱ፡ ነገርንም፡ተከተሉ፥ምናምንቴዎችም፡ኾኑ፥እግዚአብሔርም፡እንደ፡እነርሱ፡እንዳይሠሩ፡ያዘዛቸውን፡በዙሪያቸው፡ ያሉትን፡አሕዛብን፡ተከተሉ።

16የአምላካቸውንም፡የእግዚአብሔርን፡ትእዛዝ፡ዅሉ፡ተዉ፥ቀልጠው፡የተሠሩትንም፡የኹለቱን፡እንቦሶች፡ ምስሎች፡አደረጉ፥የማምለኪያ፡ዐጸድንም፡ተከሉ፥ለሰማይም፡ሰራዊት፡ዅሉ፡ሰገዱ፥በዓልንም፡አመለኩ።

17ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆቻቸውን፡በእሳት፡አሳለፏቸው፥ሟርተኛዎችና፡አስማተኛዎችም፡ኾኑ፥ያስቈጡትም፡ ዘንድ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡ነገር፡ለማድረግ፡ራሳቸውን፡ሸጡ።

18ስለዚህም፡እግዚአብሔር፡በእስራኤል፡ላይ፡እጅግ፡ተቈጣ፥ከፊቱም፡ጣላቸው፤ከይሁዳም፡ነገድ፡ብቻ፡ በቀር፡ማንም፡አልቀረም።

19ይሁዳም፡ደግሞ፡እስራኤል፡ባደረጋት፡ሥርዐት፡ኼደ፡እንጂ፡የአምላኩን፡የእግዚአብሔርን፡ትእዛዝ፡ አልጠበቀም።

20እግዚአብሔርም፡የእስራኤልን፡ዘር፡ዅሉ፡ጠላ፥አስጨነቃቸውም፥ከፊቱም፡እስኪጥላቸው፡ድረስ፡ በበዝባዦች፡እጅ፡አሳልፎ፡ሰጣቸው።

21እስራኤልንም፡ከዳዊት፡ቤት፡ለየ፤የናባጥንም፡ልጅ፡ኢዮርብዓምን፡አነገሡ፤ኢዮርብዓምም፡ እግዚአብሔርን፡ከመከተል፡እስራኤልን፡መለሰ፥ታላቅም፡ኀጢአት፡አሠራቸው።

22የእስራኤልም፡ልጆች፡ኢዮርብዓም፡ባደረገው፡ኀጢአት፡ዅሉ፡ኼዱ፤

23እግዚአብሔርም፡በባሪያዎቹ፡በነቢያቱ፡ዅሉ፡አፍ፡እንደ፡ተናገረው፡እስራኤልን፡ከፊቱ፡እስኪያወጣ፡ ድረስ፡ከርሷ፡አልራቁም።እስራኤልም፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ከምድሩ፡ወደ፡አሶር፡ፈለሰ።

24የአሶርም፡ንጉሥ፡ከባቢሎንና፡ከኩታ፡ከአዋና፡ከሐማት፡ከሴፈርዋይም፡ሰዎችን፡አመጣ፥በእስራኤልም፡ ልጆች፡ፋንታ፡በሰማርያ፡ከተማዎች፡አኖራቸው፤ሰማርያንም፡ወረሷት፤በከተማዎቿም፡ተቀመጡ።

25በዚያም፡መቀመጥ፡በዠመሩ፡ጊዜ፡እግዚአብሔርን፡አይፈሩትም፡ነበር፤እግዚአብሔርም፡አንበሳዎች፡ ሰደደባቸው፥ይገድሏቸውም፡ነበር።

26ስለዚህም፡ለአሶር፡ንጉሥ፦ያፈለስኻቸው፥በሰማርያም፡ከተማዎች፡ያኖርኻቸው፡የአገሩን፡አምላክ፡ወግ፡ አላወቁም፤የአገሩን፡አምላክ፡ወግ፡አላወቁምና፡አንበሳዎችን፡ሰዶ፟ባቸዋል፥እንሆም፥ገደሏቸው፡ብለው፡ ተናገሩት።

27የአሶርም፡ንጉሥ።ከዚያ፡ካመጣችዃቸው፡ካህናት፡አንዱን፡ውሰዱ፤ኼዶም፡በዚያ፡ይቀመጥ፥የአገሩንም፡ አምላክ፡ወግ፡ያስተምራቸው፡ብሎ፡አዘዘ።

28ከሰማርያም፡ካፈለሷቸው፡ካህናት፡አንዱ፡መጥቶ፡በቤቴል፡ተቀመጠ፥እግዚአብሔርንም፡እንዴት፡ እንዲፈሩት፡ያስተምራቸው፡ነበር።

29በየሕዝባቸውም፡አምላካቸውን፡አደረጉ፥ሰምራውያንም፡በሠሩት፡በኰረብታው፡መስገጃዎች፡ሕዝቡ፡ዅሉ፡ በሚኖሩበት፡ከተማዎቻቸው፡አኖሯቸው።

30የባቢሎንም፡ሰዎች፡ሱኮትበኖትን፡ሠሩ፤የኩታም፡ሰዎች፡ኤርጌል ን፡ሠሩ፤የሐማትም፡ሰዎች፡ 176 ዕብ.፥ኔርጋል። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org አሲማት ን፡ሠሩ፤

31ዐዋውያንም፡ኤልባዝር ንና፡ተርታቅን፡ሠሩ፤የሴፈርዋይም፡ሰዎችም፡ለሴፈርዋይም፡አማልክት፡ ለአድራሜሌክና፡ለዐነሜሌክ፡ልጆቻቸውን፡በእሳት፡ያቃጥሉ፡ነበር።

32እግዚአብሔርንም፡ይፈሩ፡ነበር፥ከመካከላቸውም፡ለኰረብታው፡መስገጃዎች፡ካህናት፡ አደረጉ፥በኰረብታውም፡መስገጃዎች፡ይሠዉ፡ነበር።

33እግዚአብሔርንም፡ሲፈሩ፡ከመካከላቸው፡እንደፈለሱት፡እንደ፡አሕዛብ፡ልማድ፡አምላካቸውን፡ያመልኩ፡ ነበር።

34እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡እንደ፡ቀደመው፡ልማድ፡ያደርጋሉ፤እግዚአብሔርንም፡አይፈሩም፥እግዚአብሔርም፡ እስራኤል፡ብሎ፡የጠራውን፡የያዕቆብን፡ልጆች፡እንዳዘዛቸው፡ሥርዐትና፡ፍርድ፡ሕግና፡ትእዛዝም፡አያደርጉም።

35እግዚአብሔርም፡ከነርሱ፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡አደረገ፥እንዲህም፡ብሎ፡አዘዛቸው።ሌላዎችን፡አማልክት፡ አትፍሩ፥አትስገዱላቸው፥አታምልኳቸው፥አትሠዉላቸው፤

36ነገር፡ግን፥በታላቅ፡ኀይል፡በተዘረጋችም፡ክንድ፡ከግብጽ፡ምድር፡ያወጣችኹን፡እግዚአብሔር፡ርሱን፡ ፍሩ፥ለርሱም፡ስገዱ፥ለርሱም፡ሠዉ፤

37የጻፈላችኹንም፡ሥርዐትና፡ፍርድ፡ሕግና፡ትእዛዝም፡ለዘለዓለም፡ታደርጉ፡ዘንድ፡ጠብቁ፤ሌላዎችንም፡ አማልክት፡አትፍሩ።

38ከእናንተም፡ጋራ፡ያደረግኹትን፡ቃል፡ኪዳን፡አትርሱ፤ሌላዎችንም፡አማልክት፡አትፍሩ።

39አምላካችኹን፡እግዚአብሔርን፡ፍሩ፤ርሱም፡ከጠላቶቻችኹ፡ዅሉ፡እጅ፡ያድናችዃል።

40ነገር፡ግን፥እንደ፡ቀደመው፡ልማዳቸው፡አደረጉ፡እንጂ፡አልሰሙም።

41እነዚህም፡አሕዛብ፡እግዚአብሔርን፡ይፈሩ፡ነበር፤ደግሞም፡የተቀረጹ፡ምስሎቻቸውን፡ያመልኩ፡ ነበር፤ልጆቻቸውም፡የልጅ፡ልጆቻቸውም፡አባቶቻቸው፡እንዳደረጉ፡እንዲሁ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ያደርጋሉ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source