1እንዲህም፡ኾነ፤በእስራኤል፡ንጉሥ፡በኤላ፡ልጅ፡በሆሴዕ፡በሦስተኛው፡ዓመት፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡የአካዝ፡ ልጅ፡ሕዝቅያስ፡ነገሠ።
2መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የኻያ፡ዐምስት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፤በኢየሩሳሌምም፡ኻያ፡ዘጠኝ፡ዓመት፡ ነገሠ፤እናቱም፡የዘካርያስ፡ልጅ፡አቡ ፡ነበረች።
3ርሱም፡አባቱ፡ዳዊት፡እንዳደረገው፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቅን፡ነገርን፡አደረገ።
4በኰረብታም፡ያሉትን፡መስገጃዎች፡አስወገደ፥ሐውልቶችንም፡ቀለጣጠመ፥የማምለኪያ፡ዐጸዶቹንም፡ ቈረጠ፤የእስራኤልም፡ልጆች፡እስከዚህ፡ዘመን፡ድረስ፡ያጥኑለት፡ነበርና፥ሙሴ፡የሠራውን፡የናሱን፡እባብ፡ ሰባበረ፤ስሙንም፡ነሑሽታን፡ብሎ፡ጠራው።
5በእስራኤልም፡አምላክ፡በእግዚአብሔር፡ታመነ፤ከርሱም፡በዃላ፡ከርሱም፡በፊት፡ከነበሩት፡ከይሁዳ፡ ነገሥታት፡ዅሉ፡ርሱን፡የሚመስል፡አልነበረም።
6ከእግዚአብሔርም፡ጋራ፡ተጣበቀ፥ርሱንም፡ከመከተል፡አልራቀም፥እግዚአብሔርም፡ለሙሴ፡ያዘዘውን፡ ትእዛዛቱን፡ጠበቀ።
7እግዚአብሔርም፡ከርሱ፡ጋራ፡ነበረ፥የሚኼድበትም፡መንገድ፡ተከናወነለት፤በአሶርም፡ንጉሥ፡ላይ፡ 177 ዕብ.፥አሺማ። 178 ዕብ.፥ኒብሐዝ። 179 ዕብ.፥አቢይ፡(አባዊ•የአባት)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ዐመፀ፥አልገበረለትም።
8ፍልስጥኤማውያንንም፡እስከ፡ጋዛና፡እስከ፡ዳርቻዋ፡ድረስ፥ከዘበኛዎች፡ግንብ፡ዠምሮ፡እስከምሽጉ፡ከተማ፡ ድረስ፡መታ።
9በንጉሡ፡በሕዝቅያስ፡በአራተኛው፡ዓመት፥በእስራኤል፡ንጉሥ፡በኤላ፡ልጅ፡በሆሴዕ፡በሰባተኛው፡ ዓመት፥የአሶር፡ንጉሥ፡ስልምናሶር፡ወደ፡ሰማርያ፡ወጣ፥ከበባትም።
10ከሦስት፡ዓመት፡በዃላም፡ወሰዳት፤በሕዝቅያስ፡በስድስተኛው፡ዓመት፥በእስራኤል፡ንጉሥ፡በሆሴዕ፡ በዘጠነኛው፡ዓመት፥ሰማርያ፡ተያዘች።
11የአሶር፡ንጉሥ፡እስራኤልን፡ወደ፡አሶር፡አፈለሰ፥በአላሔና፡በአቦር፡በጎዛንም፡ወንዝ፡በሜዶንም፡ ከተማዎች፡አኖራቸው፤
12የአምላካቸውን፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡አልሰሙምና፥ቃል፡ኪዳኑንም፡አፍርሰዋልና፥የእግዚአብሔርም፡ ባሪያ፡ሙሴ፡ያዘዘውን፡ዅሉ፡አልሰሙምና፥አላደረጉምና።
13በንጉሡም፡በሕዝቅያስ፡በዐሥራ፡አራተኛው፡ዓመት፡የአሶር፡ንጉሥ፡ሰናክሬም፡ወደ፡ይሁዳ፡ ወደተመሸጉት፡ከተማዎች፡ዅሉ፡ወጣ፥ወሰዳቸውም።
14የይሁዳም፡ንጉሥ፡ሕዝቅያስ፦በድያለኹ፥ከእኔ፡ተመለስ፤የምትጭንብኝን፡ዅሉ፡እሸከማለኹ፡ብሎ፡ ወደአሶር፡ንጉሥ፡ወደ፡ለኪሶ፡ላከ።የአሶርም፡ንጉሥ፡በይሁዳ፡ንጉሥ፡በሕዝቅያስ፡ላይ፡ሦስት፡መቶ፡ መክሊት፡ብርና፡ሠላሳ፡መክሊት፡ወርቅ፡ጫነበት።
15ሕዝቅያስም፡በእግዚአብሔር፡ቤትና፡በንጉሡ፡ቤት፡መዛግብት፡የተገኘውን፡ብር፡ዅሉ፡ሰጠው።
16በዚያን፡ጊዜም፡ሕዝቅያስ፡ከእግዚአብሔር፡መቅደስ፡ደጆችና፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡ሕዝቅያስ፡ከለበጣቸው፡ መቃኖች፡ወርቁን፡ቈረጠ፥ለአሶርም፡ንጉሥ፡ሰጠው።
17የአሶርም፡ንጉሥ፡ተርታንንና፡ራፌስን፡ራፋስቂስንም፡ከብዙ፡ሰራዊት፡ጋራ፡ከለኪሶ፡ወደ፡ንጉሡ፡ወደ፡ ሕዝቅያስ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ላከ።ወጥተውም፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡መጡ፤በመጡም፡ጊዜ፡በዐጣቢው፡ዕርሻ፡ መንገድ፡ባለችው፡በላይኛዪቱ፡ኵሬ፡መስኖ፡አጠገብ፡ቆሙ።
18ንጉሡንም፡ጠሩ፤የቤቱም፡አዛዥ፣የኬልቅያስ፡ልጅ፡ኤልያቄም፥ጸሓፊውም፡ሳምናስ፣ታሪክ፡ጸሓፊውም፡ የአሣፍ፡ልጅ፡ዮአስ፣ወደ፡እነርሱ፡ወጡ።
19ራፋስቂስም፡አላቸው፦ለሕዝቅያስ፡እንዲህ፡ብላችኹ፡ንገሩት፦ታላቁ፡የአሶር፡ንጉሥ፡እንዲህ፡ ይላል፦ይህ፡የምትታመንበት፡መተማመኛ፡ምንድር፡ነው፧
20የከንፈር፡ቃል፡ለሰልፍ፡ምክርና፡ኀይል፡እንደሚኾን፡ትናገራለኽ፤አኹንም፡በእኔ፡ላይ፡ያመፅኸው፡ በማን፡ተማምነኽ፡ነው፧
21እንሆ፥በዚህ፡በተቀጠቀጠ፡በሸምበቆ፡በትር፡በግብጽ፡ትታመናለኽ፤ሰው፡ቢመረኰዘው፡ተሰብሮ፡በእጁ፡ ይገባል፥ያቈስለውማል፤የግብጽ፡ንጉሥ፡ፈርዖን፡ለሚታመኑበት፡ዅሉ፡እንዲሁ፡ነው።
22እናንተም፦በአምላካችን፡በእግዚአብሔር፡እንታመናለን፡ብትሉኝ፥ሕዝቅያስ፡ይሁዳንና፡ ኢየሩሳሌምን፦በኢየሩሳሌም፡ባለው፡በዚህ፡መሠዊያ፡ፊት፡ሰገዱ፡ብሎ፡የኰረብታ፡መስገጃዎቹንና፡ መሠዊያዎቹን፡ያስፈረሰ፡ይህ፡አይደለምን፧
23አኹን፡እንግዲህ፡ከጌታዬ፡ከአሶር፡ንጉሥ፡ጋራ፡ተወራረድ፥የሚቀመጡባቸውንም፡ሰዎች፡ማግኘት፡ ቢቻልኽ፡እኔ፡ኹለት፡ሺሕ፡ፈረሶች፡እሰጥኻለኹ።
24ስለ፡ሠረገላዎችና፡ስለ፡ፈረሰኛዎች፡በግብጽ፡ስትታመን፥ከጌታዬ፡ባሪያዎች፡የሚያንሰውን፡የአንዱ፡ አለቃ፡ፊት፡ትቃወም፡ዘንድ፡እንዴት፡ይቻልኻል፧
25አኹን፡በእውኑ፡ያለ፡እግዚአብሔር፡ትእዛዝ፡ይህን፡ስፍራ፡አጠፋ፡ዘንድ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ወጥቻለኹን፧እግዚአብሔር፦ወደዚች፡አገር፡ወጥተኽ፡አጥፋት፡አለኝ።
26የኬልቅያስም፡ልጅ፡ኤልያቄም፡ሳምናስም፡ዮአስም፡ራፋስቂስን፦እኛ፡እንሰማለንና፡እባክኽ፥በሶርያ፡ ቋንቋ፡ለባሪያዎችኽ፡ተናገር፤በቅጥርም፡ላይ፡ባለው፡ሕዝብ፡ዦሮ፡በአይሁድ፡ቋንቋ፡አትናገረን፡አሉት።
27ራፋስቂስ፡ግን፦ጌታዬ፡ይህን፡ቃል፡እናገር፡ዘንድ፡ወዳንተና፡ወደ፡ጌታኽ፡ልኮኛልን፧ከእናንተ፡ጋራ፡ ኵሳቸውን፡ይበሉ፡ዘንድ፡ሽንታቸውንም፡ይጠጡ፡ዘንድ፡በቅጥር፡ላይ፡ወደተቀመጡት፡ሰዎች፡ አይደለምን፧አላቸው።
28ራፋስቂስም፡ቆሞ፡በታላቅ፡ድምፅ፡በአይሁድ፡ቋንቋ፡እንዲህ፡ብሎ፡ጮኸ፦የታላቁን፡የአሶር፡ንጉሥ፡ ቃል፡ስሙ፤ንጉሡ፡እንዲህ፡ይላል፦
29ከእጄ፡ያድናችኹ፡ዘንድ፡አይችልምና፡ሕዝቅያስ፡አያታላ፟ችኹ፤
30ሕዝቅያስም፦እግዚአብሔር፡በርግጥ፡ያድነናል፥ይህችም፡ከተማ፡በአሶር፡ንጉሥ፡እጅ፡አትሰጥም፡ብሎ፡ በእግዚአብሔር፡እንድትታመኑ፡አያድርጋችኹ።
31ሕዝቅያስንም፡አትስሙ፤የአሶር፡ንጉሥ፡እንዲህ፡ይላል፦ከእኔ፡ጋራ፡ታረቁ፡ወደ፡እኔም፡ ውጡ፥እያንዳንዳችኹም፡ከወይናችኹና፡ከበለሳችኹ፡ብሉ፡ከጕድጓዳችኹም፡ውሃ፡ጠጡ፤
32ይህም፡መጥቼ፡ምድራችኹን፡ወደምትመስለው፡ምድር፥እኽልና፡የወይን፡ጠጅ፥እንጀራና፡ ወይን፥ወይራና፡ማር፡ወዳለባት፡ምድር፡እስካፈልሳችኹ፡ድረስ፡በሕይወት፡እንድትኖሩ፡እንዳትሞቱም፡ ነው።ሕዝቅያስም፦እግዚአብሔር፡ያድነናል፡ብሎ፡ቢያታልላችኹ፡አትስሙት።
33በእውኑ፡የአሕዛብ፡አማልክት፡አገሮቻቸውን፡ከአሶር፡ንጉሥ፡እጅ፡አድነዋቸዋልን፧
34የሐማትና፡የአርፋድ፡አማልክት፡ወዴት፡አሉ፧የሴፈርዋይምና፡የሄና፡የዒዋም፡አማልክት፡ወዴት፡አሉ፧
35ሰማርያን፡ከእጄ፡አድነዋታልን፧እግዚአብሔር፡ኢየሩሳሌምን፡ከእጄ፡ያድን፡ዘንድ፡ከአገሮቹ፡አማልክት፡ ዅሉ፡አገሩን፡ከእጄ፡ያዳነ፡ማን፡ነው፧
36ሕዝቡም፡ዝም፡አሉ፥አንዳችም፡አልመለሱለትም፤ንጉሡ፡እንዳይመልሱለት፡አዞ፟፡ነበርና።
37የቤቱ፡አዛዥ፡የኬልቅያስ፡ልጅ፡ኤልያቄም፡ጸሓፊውም፡ሳምናስ፡ታሪክ፡ጸሓፊም፡የአሣፍ፡ልጅ፡ዮአስ፡ ልብሳቸውን፡ቀደ፟ው፡ወደ፡ሕዝቅያስ፡መጡ፥የራፋስቂስንም፡ቃል፡ነገሩት።