Skip to content
← 2 Kings

Chapter 2 · Amharic

2 Kings

1እንዲህም፡ኾነ፤እግዚአብሔር፡ኤልያስን፡በዐውሎ፡ነፋስ፡ወደ፡ሰማይ፡ሊያወጣው፡በወደደ፡ጊዜ፡ኤልያስ፡ ከኤልሳዕ፡ጋራ፡ከገልገላ፡ተነሣ።

2ኤልያስም፡ኤልሳዕን፦እግዚአብሔር፡ወደ፡ቤቴል፡ልኮኛልና፥በዚህ፡ቈይ፡አለው።ኤልሳዕም፦ሕያው፡ እግዚአብሔርን! በሕያው፡ነፍስኽም፡እምላለኹ፥አልለይኽም፡አለ።ወደ፡ቤቴልም፡ወረዱ።

3በቤቴልም፡የነበሩ፡የነቢያት፡ልጆች፡ወደ፡ኤልሳዕ፡ወጥተው፦እግዚአብሔር፡ጌታኽን፡ከራስኽ፡ላይ፡ዛሬ፡ እንዲወስደው፡ዐውቀኻልን፧አሉት።ርሱም፦አዎን፥ዐውቄያለኹ፤ዝም፡በሉ፡አላቸው።

4ኤልያስም፦ኤልሳዕ፡ሆይ፥እግዚአብሔር፡ወደ፡ኢያሪኮ፡ልኮኛልና፥እባክኽ፥በዚህ፡ቈይ፡ አለው።ርሱም፦ሕያው፡እግዚአብሔርን! በሕያው፡ነፍስኽም፡እምላለኹ፥አልለይኽም፡አለ።

5ወደ፡ኢያሪኮም፡መጡ።በኢያሪኮም፡የነበሩ፡የነቢያት፡ልጆች፡ወደ፡ኤልሳዕ፡ቀርበው፦እግዚአብሔር፡ ጌታኽን፡ከራስኽ፡ላይ፡ዛሬ፡እንዲወስደው፡ዐውቀኻልን፧አሉት።ርሱም፦አዎን፡ዐውቄያለኹ፤ዝም፡በሉ፡ ብሎ፡መለሰ።

6ኤልያስም፦እግዚአብሔር፡ወደ፡ዮርዳኖስ፡ልኮኛልና፥እባክኽ፥በዚህ፡ቈይ፡አለው።ርሱም፦ሕያው፡ እግዚአብሔርን! በሕያው፡ነፍስኽም፡እምላለኹ፥አልለይኽም፡አለ።ኹለቱም፡ኼዱ።

7ከነቢያትም፡ልጆች፡ዐምሳ፡ሰዎች፡ኼዱ፥በፊታቸውም፡ርቀው፡ቆሙ፤እነዚህም፡ኹለቱ፡በዮርዳኖስ፡ዳር፡ ቆመው፡ነበር።

8ኤልያስም፡መጐናጸፊያውን፡ወስዶ፡ጠቀለለው፥ውሃውንም፡መታ፥ወዲህና፡ወዲያም፡ተከፈለ፤ኹለቱም፡ በደረቅ፡ተሻገሩ።

9ከተሻገሩም፡በዃላ፡ኤልያስ፡ኤልሳዕን፦ከአንተ፡ሳልወሰድ፡አደርግልኽ፡ዘንድ፡የምትሻውን፡ለምን፡ አለው፤ኤልሳዕም፦መንፈስኽ፡በእኔ፡ላይ፡ኹለት፡ዕጥፍ፡ይኾን፡ዘንድ፡እለምንኻለኹ፡አለ።

10ርሱም፦አስቸጋሪ፡ነገር፡ለምነኻል፤ነገር፡ግን፥ከአንተ፡ዘንድ፡በተወሰድኹ፡ጊዜ፡ብታየኝ፡ ይኾንልኻል፤አለዚያ፡ግን፡አይኾንልኽም፡አለ።

11ሲኼዱም፦እያዘገሙም፡ሲጫወቱ፥እንሆ፥የእሳት፡ሠረገላና፡የእሳት፡ፈረሶች፡በመካከላቸው፡ገብተው፡ ከፈሏቸው፤ኤልያስም፡በዐውሎ፡ነፋስ፡ወደ፡ሰማይ፡ወጣ።

12ኤልሳዕም፡አይቶ፦አባቴ፡አባቴ፡ሆይ፥የእስራኤል፡ሠረገላና፡ፈረሰኛዎች፥ብሎ፡ጮኸ።ከዚያም፡ወዲያ፡ አላየውም፤ልብሱንም፡ይዞ፡ከኹለት፡ተረተረው።

13ከኤልያስም፡የወደቀውን፡መጐናጸፊያ፡አነሣ፥ተመልሶም፡በዮርዳኖስ፡ዳር፡ቆመ።

14ከኤልያስም፡የወደቀውን፡መጐናጸፊያ፡ወስዶ፡ውሃውን፡መታና።የኤልያስ፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ወዴት፡ ነው፧አለ፤ውሃውንም፡በመታ፡ጊዜ፡ወዲህና፡ወዲያ፡ተከፈለ፤ኤልሳዕም፡ተሻገረ።

15ከኢያሪኮም፡መጥተው፡በአንጻሩ፡የነበሩት፡የነቢያት፡ልጆች፡ባዩት፡ጊዜ፦የኤልያስ፡መንፈስ፡በኤልሳዕ፡ ላይ፡ዐርፏል፡አሉ።ሊገናኙትም፡መጥተው፡በፊቱ፡ወደ፡ምድር፡ተደፉ።

16እነርሱም፦እንሆ፥ከባሪያዎችኽ፡ጋራ፡ዐምሳ፡ኀያላን፡ሰዎች፡አሉ፤የእግዚአብሔር፡መንፈስ፡አንሥቶ፡ ወደ፡አንድ፡ተራራ፡ወይም፡ወደ፡አንድ፡ሸለቆ፡ጥሎት፡እንደ፡ኾነ፥ኼደው፡ጌታኽን፡ይፈልጉት፡ዘንድ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org እንለምንኻለን፡አሉት።ርሱም፦አትስደዱ፡አላቸው።

17እስኪያፍርም፡ድረስ፡ግድ፡ባሉት፡ጊዜ፦ስደዱ፡አለ፤ዐምሳም፡ሰዎች፡ሰደዱ፤ሦስት፡ቀንም፡ፈልገው፡ አላገኙትም።

18በኢያሪኮም፡ተቀምጦ፡ሳለ፡ወደ፡ርሱ፡ተመለሱ፤ርሱም፦አትኺዱ፡አላልዃችኹምን፧አላቸው።

19የከተማዪቱም፡ሰዎች፡ኤልሳዕን፦እንሆ፥ጌታችን፡እንደምታይ፡የዚች፡ከተማ፡ኑሮ፡መልካም፡ ነው፤ውሃው፡ግን፡ክፉ፡ነው፥ምድሪቱም፡ፍሬዋን፡ትጨነግፋለች፡አሉት።

20ርሱም፦ዐዲስ፡ማሰሮ፡አምጡልኝ፥ጨውም፡ጨምሩበት፡አለ፤ያንንም፡አመጡለት።

21ውሃው፡ወዳለበቱም፡ምንጭ፡ወጥቶ፡ጨው፡ጣለበትና፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ይህን፡ውሃ፡ ፈውሼዋለኹ፤ከዚህም፡በዃላ፡ሞትና፡ጭንገፋ፡አይኾንበትም፡አለ።

22ኤልሳዕም፡እንደተናገረው፡ነገር፡ውሃው፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ተፈውሷል።

23ከዚያም፡ወደ፡ቤቴል፡ወጣ፤በመንገድም፡ሲወጣ፡ብላቴናዎች፡ከከተማዪቱ፡ወጥተው።አንተ፡ መላጣ፥ውጣ፤አንተ፡መላጣ፥ውጣ፡ብለው፡አፌዙበት።

24ዘወርም፡ብሎ፡አያቸው፥በእግዚአብሔርም፡ስም፡ረገማቸው፤ከዱርም፡ኹለት፡ድቦች፡ወጥተው፡ ከብላቴናዎች፡አርባ፡ኹለቱን፡ሰባበሯቸው።

25ከዚያም፡ወደቀርሜሎስ፡ተራራ፡ኼደ፥ከዚያም፡ወደ፡ሰማርያ፡ተመለሰ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source