Skip to content
← 2 Kings

Chapter 20 · Amharic

2 Kings

1በዚያም፡ወራት፡ሕዝቅያስ፡እስከ፡ሞት፡ድረስ፡ታመመ።ነቢዩም፡የዓሞጽ፡ልጅ፡ኢሳይያስ፡ወደ፡ርሱ፡ መጥቶ፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ትሞታለኽ፡እንጂ፡በሕይወት፡አትኖርምና፡ቤትኽን፡አስተካክል፡ አለው።

2ፊቱንም፡ወደ፡ግድግዳው፡መልሶ፡እንዲህ፡ሲል፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጸለየ።

3አቤቱ፥በፊትኽ፡በእውነትና፡በፍጹም፡ልብ፡እንደ፡ኼድኹ፥ደስ፡የሚያሠኝኽንም፡እንዳደረግኹ፡ታስብ፡ ዘንድ፡እለምንኻለኹ።ሕዝቅያስም፡እጅግ፡አድርጎ፡አለቀሰ።

4ኢሳይያስም፡ወደመካከለኛው፡ከተማ፡አደባባይ፡ሳይደርስ፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡እንዲህ፡ሲል፡መጣለት።

5ተመልሰኽ፡የሕዝቤን፡አለቃ፡ሕዝቅያስን፡እንዲህ፡በለው፦የአባትኽ፡የዳዊት፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ እንዲህ፡ይላል፦ጸሎትኽን፡ሰምቻለኹ፥እንባኽንም፡አይቻለኹ፤እንሆ፥እፈውስኻለኹ፤በሦስተኛውም፡ቀን፡ ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ትወጣለኽ።

6በዕድሜኽም፡ላይ፡ዐሥራ፡ዐምስት፡ዓመት፡እጨምራለኹ፤አንተንና፡ይህችን፡ከተማ፡ከአሶር፡ንጉሥ፡እጅ፡ እታደጋለኹ፤ስለ፡እኔም፡ስለ፡ባሪያዬም፡ስለ፡ዳዊት፡ይህችን፡ከተማ፡እጋርዳታለኹ።

7ኢሳይያስም፥የበለስ፡ጥፍጥፍ፡አምጡልኝ፡አለ፤አምጥተውም፡በዕባጩ፡ላይ፡አደረጉለት፥ርሱም፡ተፈወሰ።

8ሕዝቅያስም፡ኢሳይያስን፥እግዚአብሔር፡እንዲፈውሰኝ፥እኔስ፡በሦስተኛው፡ቀን፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ እንድወጣ፡ምልክቱ፡ምንድር፡ነው፧አለው።

9ኢሳይያስም፥እግዚአብሔር፡የተናገረውን፡ነገር፡እንዲፈጽመው፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ምልክቱ፡ይህ፡ 180 ዕብ.፥ኤሣርሐዶን። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ይኾንልኻል፤ጥላው፡ዐሥር፡ደረጃ፡ወደ፡ፊት፡ይኼድ፡ዘንድ፡ወይም፡ዐሥር፡ደረጃ፡ወደ፡ዃላ፡ይመለስ፡ ዘንድ፡ትወዳ፟ለኽን፧አለ።

10ሕዝቅያስም፥ጥላው፡ዐሥር፡ደረጃ፡ቢጨምር፡ቀላል፡ነገር፡ነው፤እንዲህ፡አይኹን፤ነገር፡ግን፥ጥላው፡ ዐሥር፡ደረጃ፡ወደ፡ዃላ፡ይመለስ፡አለው።

11ነቢዩም፡ኢሳይያስ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጮኸ፤ጥላውንም፡በአካዝ፡የጥላ፡ስፍራ፡ሰዓት፡ላይ፡በወረደበት፡ መንገድ፡ዐሥር፡ደረጃ፡ወደ፡ዃላ፡መለሰው።

12በዚያም፡ወራት፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡የባልዳን፡ልጅ፡መሮዳክ፡ባልዳን፡ሕዝቅያስ፡እንደ፡ታመመ፡ሰምቶ፡ ነበርና፥ደብዳቤና፡እጅ፡መንሻ፡ወደ፡ሕዝቅያስ፡ላከ።

13ሕዝቅያስም፡ደስ፡አለው፥ግምጃ፡ቤቱንም፡ዅሉ፥ብሩንና፡ወርቁንም፥ቅመሙንና፡የከበረውንም፡ ዘይት፥መሣሪያም፡ያለበትን፡ቤት፡በቤተ፡መዛግብቱም፡የተገኘውን፡ዅሉ፡አሳያቸው፡በቤቱና፡በግዛቱ፡ዅሉ፡ ካለው፡ሕዝቅያስ፡ያላሳያቸው፡የለም።

14ነቢዩም፡ኢሳይያስ፡ወደ፡ንጉሡ፡ወደ፡ሕዝቅያስ፡መጥቶ፦እነዚህ፡ሰዎች፡ምን፡አሉ፧ከወዴትስ፡ መጡልኽ፧አለው።ሕዝቅያስም፦ከሩቅ፡አገር፡ከባቢሎን፡መጡ፡አለው።

15ርሱም፦በቤትኽ፡ያዩት፡ምንድር፡ነው፧አለው፤ሕዝቅያስም፦በቤቴ፡ያለውን፡ዅሉ፡አይተዋል፤በቤተ፡ መዛግብቴ፡ካለው፡ያላሳየዃቸው፡የለም፡አለው።

16ኢሳይያስም፡ሕዝቅያስን፦የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስማ።

17እንሆ፥በቤትኽ፡ያለው፡ዅሉ፥አባቶችኽም፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ያከማቹት፡ዅሉ፡ወደ፡ባቢሎን፡ የሚፈልስበት፡ወራት፡ይመጣል፤ምንም፡አይቀርም፥ይላል፡እግዚአብሔር።

18ከአንተም፡ከሚወጡት፡ከምትወልዳቸው፡ልጆችኽ፡ማርከው፡ይወስዳሉ፤በባቢሎንም፡ንጉሥ፡ቤት፡ውስጥ፡ ጃን፡ደረባዎች፡ይኾናሉ፡አለው።

19ሕዝቅያስም፡ኢሳይያስን፦የተናገርኸው፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡መልካም፡ነው፡አለው።ደግሞም፦በዘመኔ፡ ሰላምና፡እውነት፡የኾነ፡እንደ፡ኾነ፡መልካም፡አይደለምን፧አለ።

20የቀረውም፡የሕዝቅያስ፡ነገር፥ጭከናውም፡ዅሉ፥ኵሬውንና፡መስኖውንም፡እንደ፡ሠራ፥ውሃውንም፡ወደ፡ ከተማዪቱ፡እንዳመጣ፥በይሁዳ፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡አይደለምን፧

21ሕዝቅያስም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፤ልጁም፡ምናሴ፡በርሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source