Skip to content
← 2 Kings

Chapter 21 · Amharic

2 Kings

1ምናሴም፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የዐሥራ፡ኹለት፡ዓመት፡ልጅ፡ነበረ፤በኢየሩሳሌምም፡ዐምሳ፡ዐምስት፡ ዓመት፡ነገሠ፤የእናቱ፡ስም፡ሐፍሴባ፡ነበረ።

2እግዚአብሔርም፡ከእስራኤል፡ልጆች፡ፊት፡እንዳወጣቸው፡እንደ፡አሕዛብ፡ርኵሰት፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ ክፉ፡ነገር፡አደረገ።

3አባቱም፡ሕዝቅያስ፡ያፈረሳቸውን፡የኰረብታውን፡መስገጃዎች፡መልሶ፡ሠራ፤የእስራኤልም፡ንጉሥ፡አክአብ፡ እንዳደረገው፡ለበዓል፡መሠዊያ፡ሠራ፥የማምለኪያ፡ዐጸድንም፡ተከለ፥ለሰማይም፡ሰራዊት፡ዅሉ፡ሰገደ፡ አመለካቸውም።

4እግዚአብሔርም፦ስሜን፡በኢየሩሳሌም፡አኖራለኹ፡ባለው፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡መሠዊያዎችን፡ሠራ።

5በእግዚአብሔርም፡ቤት፡በኹለቱ፡ወለሎች፡ላይ፡ለሰማይ፡ሰራዊት፡ዅሉ፡መሠዊያዎችን፡ሠራ።

6ልጁንም፡በእሳት፡አሳለፈ፥ሞራ፡ገላጭም፡ኾነ፥አስማትም፡አደረገ፥መናፍስት፡ጠሪዎችንና፡ጠንቋዮችንም፡ ሰበሰበ፤ያስቈጣውም፡ዘንድ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡እጅግ፡ክፉ፡ነገር፡አደረገ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

7እግዚአብሔርም፡ለዳዊትና፡ለልጁ፡ለሰሎሞን፦በዚህ፡ቤት፡ከእስራኤልም፡ነገድ፡ዅሉ፡በመረጥዃት፡ በኢየሩሳሌም፡ስሜን፡ለዘለዓለም፡አኖራለኹ፤

8ያዘዝዃቸውንም፡ዅሉ፥ባሪያዬም፡ሙሴ፡ያዘዛቸውን፡ሕግ፡ዅሉ፡ቢያደርጉ፡ቢጠብቁም፡ለአባቶቻቸው፡ ከሰጠዃት፡ምድር፡የእስራኤልን፡እግር፡እንደ፡ገና፡አላቅበዘብዝም፡ባለው፡ቤት፡የሠራውን፡የማምለኪያ፡ ዐጸድን፡የተቀረጸውን፡ምስል፡አቆመ።

9ነገር፡ግን፥አልሰሙም፤እግዚአብሔርም፡ከእስራኤል፡ልጆች፡ፊት፡ካጠፋቸው፡ከአሕዛብ፡ይልቅ፡ክፉ፡ ይሠሩ፡ዘንድ፡ምናሴ፡አሳታቸው።

10እግዚአብሔርም፡በባሪያዎቹ፡በነቢያት፡እጅ፡እንዲህ፡ሲል፡ተናገረ፦

11የይሁዳ፡ንጉሥ፡ምናሴ፡ይህን፡ርኵሰት፡አድርጓልና፥ከፊቱም፡የነበሩ፡አሞራውያን፡ከሠሩት፡ዅሉ፡ይልቅ፡ ክፉ፡ሥራ፡ሠርቷልና፥ይሁዳንም፡ደግሞ፡በጣዖታቱ፡አስቷልና፥

12ስለዚህ፥የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥የሚሰማውን፡ዅሉ፡ኹለቱን፡ ዦሮዎቹን፡ጭው፡የሚያደርግ፡ክፉ፡ነገርን፡በኢየሩሳሌምና፡በይሁዳ፡ላይ፡አመጣለኹ።

13የሰማርያንም፡ገመድ፡የአክአብንም፡ቤት፡ቱንቢ፡በኢየሩሳሌም፡ላይ፡እዘረጋለኹ፡ሰውም፡ወጭቱን፡ እንዲወለውል፡ኢየሩሳሌምን፡ወልውዬ፡እገለብጣታለኹ።

14የርስቴንም፡ቅሬታ፡እጥላለኹ፥በጠላቶቻቸውም፡እጅ፡አሳልፌ፡እሰጣቸዋለኹ፥ለጠላቶቻቸውም፡ዅሉ፡ ምርኮና፡ብዝበዛ፡ይኾናሉ፤

15አባቶቻቸው፡ከግብጽ፡ከወጡ፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡በፊቴ፡ክፉ፡ሠርተዋልና፥አስቈጥተውኝማልና።

16ደግሞም፡ምናሴ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡ይሠራ፡ዘንድ፡ይሁዳን፡ካሳተበት፡ኀጢአት፡ሌላ፡ከዳር፡ እስከ፡ዳር፡ኢየሩሳሌምን፡እስኪሞላት፡ድረስ፡እጅግ፡ብዙ፡ንጹሕ፡ደም፡አፈሰሰ።

17የምናሴም፡የቀረው፡ነገርና፡የሠራው፡ሥራ፡ዅሉ፥ያደረገውም፡ኀጢአት፥በይሁዳ፡ነገሥታት፡ታሪክ፡ መጽሐፍ፡የተጻፈ፡አይደለምን፧

18ምናሴም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በቤቱም፡አጠገብ፡ባለው፡በዖዛ፡አትክልት፡ተቀበረ፤ልጁም፡ዓሞጽ፡ በርሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።

19ዓሞጽም፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የኻያ፡ኹለት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፤በኢየሩሳሌምም፡ኹለት፡ ዓመት፡ነገሠ፤እናቱም፡የዮጥባ፡ሰው፡የሐሩስ፡ልጅ፡ሜሶላም፡ነበረች።

20አባቱም፡ምናሴ፡እንዳደረገ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡ሠራ።

21አባቱም፡በኼደበት፡መንገድ፡ዅሉ፡ኼደ፥አባቱም፡ያመለካቸውን፡ጣዖታት፡አመለከ፡ሰገደላቸውም።

22የአባቶቹንም፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡ተወ፥በእግዚአብሔርም፡መንገድ፡አልኼደም።

23የዓሞጽም፡ባሪያዎች፡አሤሩበት፥ንጉሡንም፡በቤቱ፡ውስጥ፡ገደሉት፥

24የአገሩ፡ሕዝብ፡ግን፡በንጉሡ፡በዓሞጽ፡ላይ፡ያሴሩበትን፡ዅሉ፡ገደሉ፤የአገሩም፡ሕዝብ፡ልጁን፡ ኢዮስያስን፡በርሱ፡ፋንታ፡አነገሡት።

25የዓሞጽም፡የቀረው፡ነገርና፡የሠራው፡ሥራ፥በይሁዳ፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡አይደለምን፧

26በዖዛም፡አትክልት፡ባለው፡በመቃብሩ፡ተቀበረ፤ልጁም፡ኢዮስያስ፡በርሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source