1ኢዮስያስም፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፥የስምንት፡ዓመት፡ልጅ፡ነበረ፤በኢየሩሳሌምም፡ሠላሳ፡አንድ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ዓመት፡ነገሠ፤እናቱም፡ከባሱሮት፡የኾነ፡የአዳያ፡ልጅ፡ይዲዳ ፡ነበረች።
2በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ቅን፡ነገርን፡አደረገ፥በአባቱም፡በዳዊት፡መንገድ፡ዅሉ፡ኼደ፥ቀኝም፡ግራም፡ አላለም።
3በንጉሡም፡በኢዮስያስ፡በዐሥራ፡ስምንተኛው፡ዓመት፡በስምንተኛው፡ወር፡ንጉሡ፡ጸሓፊውን፡የሜሶላምን፡ ልጅ፡የኤዜልያስን፡ልጅ፡ሳፋንን፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡ላከው፥እንዲህም፡አለው፦
4የመቅደሱ፡በረኛዎች፡ከሕዝቡ፡የሰበሰቡትን፡ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡የገባውን፡ገንዘብ፡ይደምር፡ዘንድ፡ ወደካህናቱ፡አለቃ፡ወደ፡ኬልቅያስ፡ኺድ።
5በእግዚአብሔርም፡ቤት፡ላሉት፡ሠራተኛዎች፡አለቃዎች፡ይስጡት፤እነርሱም፡የተናደውን፡የእግዚአብሔርን፡ ቤት፡ለሚጠግኑት፡ሠራተኛዎች፥
6ለዐናጢዎችና፡ለጠራቢዎች፥ለድንጋይም፡ወቃሪዎች፥መቅደሱንም፡ለመጠገን፡ዕንጨትንና፡የተወቀረውን፡ ድንጋይ፡ለሚገዙ፡ይክፈሉት።
7ነገር፡ግን፥እነርሱ፡የታመኑ፡ነበሩና፥በእጃቸው፡ስለ፡ተሰጠ፡አይቈጣጠሯቸውም፡ነበር።
8ካህኑም፡ኬልቅያስ፡ጸሓፊውን፡ሳፋንን፥የሕጉን፡መጽሐፍ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡አግኝቻለኹ፡ አለው፤ኬልቅያስም፡መጽሐፉን፡ለሳፋን፡ሰጠው፥ርሱም፡አነበበው።
9ጸሓፊውም፡ሳፋን፡ወደ፡ንጉሡ፡መጣ፥ለንጉሡም፦በመቅደሱ፡የተገኘውን፡ገንዘብ፡ባሪያዎችኽ፡ አፈሰሱት፥በእግዚአብሔርም፡ቤት፡ሠራተኛዎች፡ላይ፡ለተሾሙት፡አለቃዎች፡ሰጡት፡ብሎ፡አወራለት።
10ጸሓፊውም፡ሳፋን፡ለንጉሡ፦ካህኑ፡ኬልቅያስ፡መጽሐፍ፡ሰጥቶኛል፡ብሎ፡ነገረው።ሳፋንም፡በንጉሡ፡ ፊት፡አነበበው።
11ንጉሡም፡የሕጉን፡መጽሐፍ፡ቃል፡በሰማ፡ጊዜ፥ልብሱን፡ቀደደ።
12ንጉሡም፡ካህኑን፡ኬልቅያስን፥የሳፋንንም፡ልጅ፡አኪቃም ን፥የሚክያስንም፡ልጅ፡ዓክቦርን፥ጸሓፊውንም፡ ሳፋንን፥የንጉሡንም፡ብላቴና፡ዐሳያ ን፦
13አባቶቻችን፡በርሷ፡የተጻፈውን፡ዅሉ፡ይሠሩ፡ዘንድ፡የዚችን፡መጽሐፍ፡ቃል፡ስላልሰሙ፡በላያችን፡ የነደደ፡የእግዚአብሔር፡ቍጣ፡እጅግ፡ነውና፥ኼዳችኹ፡ስለ፡እኔና፡ስለ፡ሕዝቡ፡ስለ፡ይሁዳም፡ዅሉ፡የዚችን፡ የተገኘችውን፡መጽሐፍ፡ቃል፡እግዚአብሔርን፡ጠይቁ፡ብሎ፡አዘዛቸው።
14እንዲሁም፡ካህኑ፡ኬልቅያስና፡አኪቃም፡ዓክቦርም፡ሳፋንና፡ዐሳያም፡ወደ፡ልብስ፡ጠባቂው፡ወደሐስራ፡ ልጅ፡ወደ፡ቲቁዋ፡ልጅ፡ወደሴሌም፡ሚስት፡ወደ፡ነቢያቱ፡ወደ፡ሕልዳና፡ኼዱ፤ርሷም፡በኢየሩሳሌም፡ በኹለተኛው፡ክፍል፡ተቀምጣ፡ነበር፤ከርሷም፡ጋራ፡ተነጋገሩ።
15ርሷም፡አለቻቸው፦የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ወደ፡እኔ፡ለላካችኹ፡ሰው፡ እንዲህ፡ብላችኹ፡ንገሩት፦
16እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥የይሁዳ፡ንጉሥ፡እንዳነበበው፡እንደ፡መጽሐፉ፡ቃል፡ዅሉ፡በዚህ፡ ስፍራና፡በሚኖሩበት፡ላይ፡ክፉ፡ነገር፡አመጣለኹ።
17በእጃቸው፡ሥራ፡ዅሉ፡ያስቈጡኝ፡ዘንድ፡ትተውኛልና፥ለሌላዎችም፡አማልክት፡ዐጥነዋልና፥ቍጣዬ፡ በዚህ፡ስፍራ፡ላይ፡ይነዳ፟ል፥አይጠፋምም።
18እግዚአብሔርን፡ለመጠየቅ፡ለላካችኹ፡ለይሁዳ፡ንጉሥ፡ግን፡እንዲህ፡በሉት፦የእስራኤል፡አምላክ፡ እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ስለሰማኸው፡ቃል፥ልብኽ፡ገር፡ኾኗልና፥
19እነርሱም፡ለድንቅና፡ለመርገም፡እንዲኾኑ፡በዚህ፡ስፍራና፡በሚኖሩበት፡ላይ፡የተናገርኹትን፡ሰምተኽ፡ 181 ዕብ.፥የዲይዳህ፡(የተወደደች)። 182 ዕብ.፥አኂቃም፡(እኅውየ፡ቆመ፥ወንድሜ፡ቆመ)። 183 ዕብ.፥ዐሳያህ፡(ጌታ፡ሠራ)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org በእግዚአብሔር፡ፊት፡ተዋርደኻልና፥ልብስኽን፡ቀደ፟ኻልና፥በፊቴም፡አልቅሰኻልና፥እኔ፡ደግሞ፡ሰምቼኻለኹ፡ ይላል፡እግዚአብሔር።
20ስለዚህም፡ደግሞ፡ወደ፡አባቶችኽ፡እሰበስብኻለኹ፥በሰላምም፡ወደ፡መቃብርኽ፡ትሰበሰባለኽ፤በዚህም፡ ስፍራ፡ላይ፡የማመጣውን፡ክፉ፡ነገር፡ዐይኖችኽ፡አያዩም፦ይህንም፡ለንጉሡ፡አወሩለት።