1የሶርያ፡ንጉሥ፡ሰራዊት፡አለቃ፡ንዕማንም፡እግዚአብሔር፡በርሱ፡እጅ፡ለሶርያ፡ደኅንነትን፡ስለ፡ሰጠ፡ በጌታው፡ዘንድ፡ታላቅ፡ክቡር፡ሰው፡ነበረ፤ደግሞም፡ጽኑዕ፡ኀያል፡ነበረ፥ነገር፡ግን፥ለምጻም፡ነበረ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
2ከሶርያውያንም፡አገር፡አደጋ፡ጣዮች፡ወጥተው፡ነበር፥ከእስራኤልም፡ምድር፡ታናሽ፡ብላቴና፡ሴት፡ ማርከው፡ነበር፤የንዕማንንም፡ሚስት፡ታገለግል፡ነበር።
3እመቤቷንም፦ጌታዬ፡በሰማርያ፡ካለው፡ከነቢዩ፡ፊት፡ቢደርስ፡ኖሮ፡ከለምጹ፡በፈወሰው፡ነበር፡አለቻት።
4ንዕማንም፡ገብቶ፡ለጌታው።ከእስራኤል፡አገር፡የኾነች፡አንዲት፡ብላቴና፡እንዲህና፡እንዲህ፡ብላለች፡ ብሎ፡ነገረው።
5የሶርያም፡ንጉሥ፡ንዕማንን፦ኺድ፥ለእስራኤል፡ንጉሥ፡ደብዳቤ፡እልካለኹ፡አለው።ርሱም፡ ኼደ፥ዐሥርም፡መክሊት፡ብር፥ስድስት፡ሺሕም፡ወርቅ፥ዐሥርም፡መለወጫ፡ልብስ፡በእጁ፡ወሰደ።
6ለእስራኤልም፡ንጉሥ፦ይህች፡ደብዳቤ፡ወዳንተ፡ስትደርስ፡ባሪያዬን፡ንዕማንን፡ከለምጹ፡ትፈውሰው፡ዘንድ፡ እንደ፡ሰደድኹልኽ፡ዕወቅ፡የሚል፡ደብዳቤ፡ወሰደ።
7የእስራኤልም፡ንጉሥ፡ደብዳቤውን፡ባነበበ፡ጊዜ፡ልብሱን፡ቀዶ፟፦ሰውን፡ከለምጹ፡እፈውስ፡ዘንድ፡ይህ፡ ሰው፡ወደ፡እኔ፡መስደዱ፡እኔ፡በእውኑ፡ለመግደልና፡ለማዳን፡የምችል፡አምላክ፡ኾኜ፡ ነውን፧ተመልከቱ፥የጠብ፡ምክንያትም፡እንደሚፈልግብኝ፡እዩ፡አለ።
8የእግዚአብሔርም፡ሰው፡ኤልሳዕ፡የእስራኤል፡ንጉሥ፡ልብሱን፡እንደ፡ቀደደ፡በሰማ፡ጊዜ፦ልብስኽን፡ ለምን፡ቀደድኽ፧ወደ፡እኔ፡ይምጣ፥በእስራኤልም፡ዘንድ፡ነቢይ፡እንዳለ፡ያውቃል፡ብሎ፡ወደ፡ንጉሡ፡ላከ።
9ንዕማንም፡በፈረሱና፡በሠረገላው፡መጣ፥በኤልሳዕም፡ቤት፡ደጃፍ፡ውጭ፡ቆመ።
10ኤልሳዕም፦ኺድ፥በዮርዳኖስም፡ሰባት፡ጊዜ፡ታጠብ፤ሥጋኽም፡ይፈወሳል፥አንተም፡ንጹሕ፡ትኾናለኽ፡ ብሎ፡ወደ፡ርሱ፡መልእክተኛ፡ላከ።
11ንዕማን፡ግን፡ተቈጥቶ፡ኼደ፥እንዲህም፡አለ፦እንሆ፥ወደ፡እኔ፡የሚመጣ፥ቆሞም፡የአምላኩን፡ የእግዚአብሔርን፡ስም፡የሚጠራ፥የለምጹንም፡ስፍራ፡በእጁ፡ዳሶ፟፡የሚፈውሰኝ፡መስሎኝ፡ነበር።
12የደማስቆ፡ወንዞች፡አባና ና፡ፋርፋ ፡ከእስራኤል፡ውሃዎች፡ዅሉ፡አይሻሉምን፧በእነርሱስ፡ውስጥ፡ መታጠብና፡መንጻት፡አይቻለኝም፡ኖሯልን፧ዘወርም፡ብሎ፡ተቈጥቶ፡ኼደ።
13ባሪያዎቹም፡ቀርበው።አባት፡ሆይ፥ነቢዩ፡ታላቅ፡ነገርስ፡እንኳ፡ቢነግርኽ፡ኖሮ፡ባደረግኸው፡ ነበር፤ይልቁንስ።ታጠብና፡ንጹሕ፡ኹን፡ቢልኽ፡እንዴት፡ነዋ! ብለው፡ተናገሩት።
14ወረደም፥የእግዚአብሔርም፡ሰው፡እንደ፡ተናገረው፡በዮርዳኖስ፡ሰባት፡ጊዜ፡ብቅ፡ጥልቅ፡አለ፤ሥጋውም፡ እንደ፡ገና፡እንደ፡ትንሽ፡ብላቴና፡ሥጋ፡ኾኖ፡ተመለሰ፥ንጹሕም፡ኾነ።
15ርሱም፡ከጭፍራው፡ዅሉ፡ጋራ፡ወደእግዚአብሔር፡ሰው፡ተመለሰ፥ወጥቶም፡በፊቱ፡ ቆመና፦እንሆ፥ከእስራኤል፡ዘንድ፡በቀር፡በምድር፡ዅሉ፡አምላክ፡እንደሌለ፡ዐወቅኹ፤አኹንም፡ከባሪያኽ፡ በረከት፡ትቀበል፡ዘንድ፡እለምንኻለኹ፡አለ።
16ርሱም፦በፊቱ፡የቆምኹት፡ሕያው፡እግዚአብሔርን! አልቀበልም፡አለ።ይቀበለውም፡ዘንድ፡ግድ፡ አለው፤ርሱ፡ግን፡እንቢ፡አለ።
17ንዕማንም፦እኔ፡ባሪያኽ፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡ከእግዚአብሔር፡በቀር፡ለሌላዎች፡አማልክት፡የሚቃጠል፡ መሥዋዕት፡ወይም፡ሌላ፡መሥዋዕት፡አላቀርብምና፡ኹለት፡የበቅሎ፡ጭነት፡ዐፈር፡እንድወስድ፡ዕሺ፡ትለኝ፡ ዘንድ፡እለምንኻለኹ።
18እግዚአብሔርም፡ለእኔ፡ለባሪያኽ፡በዚህ፡ነገር፡ብቻ፡ይቅር፡ይበለኝ፤ጌታዬ፡በዚያ፡ይሰግድ፡ዘንድ፡ እጄን፡ተደግፎ፡ወደሬሞን፡ቤት፡በገባ፡ጊዜ፥እኔም፡በሬሞን፡ቤት፡በሰገድኹ፡ጊዜ፥እግዚአብሔር፡በዚህ፡ ነገር፡ለእኔ፡ለባሪያኽ፡ይቅር፡ይበለኝ፡አለ።
19ርሱም፦በደኅና፡ኺድ፡አለው።አንድ፡አግድመትም፡ያኽል፡ከርሱ፡ራቀ። 169 ዕብ.፥አባናህ። 170 ዕብ.፥ፋርፋር፡(የተፈረፈረ)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
20የእግዚአብሔርም፡ሰው፡ሎሌ፡ግያዝ፦ጌታዬ፡ሶርያዊውን፡ይህን፡ንዕማንን፡ማረው፥ካመጣለትም፡ነገር፡ ምንም፡አልተቀበለም፤ሕያው፡እግዚአብሔርን! በስተዃላው፡እሮጣለኹ፥ከርሱም፡አንዳች፡እወስዳለኹ፡አለ።
21ግያዝም፡ንዕማንን፡ተከተለው፤ንዕማንም፡ወደ፡ርሱ፡ሲሮጥ፡ባየው፡ጊዜ፡ሊገናኘው፡ከሠረገላው፡ ወርዶ፦ዅሉ፡ደኅና፡ነውን፧አለው።
22ርሱም፦ደኅና፡ነው።አኹን፡ከነቢያት፡ወገን፡የኾኑት፡ኹለት፡ጕልማሳዎች፡ከተራራማው፡ከኤፍሬም፡ አገር፡ወደ፡እኔ፡መጥተዋል፤አንድ፡መክሊት፡ብርና፡ኹለት፡መለወጫ፡ልብስ፡ትሰጣቸው፡ዘንድ፡ እለምንኻለኹ፡ብሎ፡ጌታዬ፡ላከኝ፡አለ።
23ንዕማንም፦ኹለት፡መክሊት፡ትወስድ፡ዘንድ፡ይፈቀድልኽ፡አለ፤ግድ፡አለውም፤ኹለቱንም፡መክሊት፡ ብር፡በኹለት፡ከረጢት፡ውስጥ፡አሰረና፡ከኹለት፡መለወጫ፡ልብስ፡ጋራ፡ለኹለት፡ሎሌዎቹ፡ አስያዘ፤እነርሱም፡ተሸክመው፡በፊቱ፡ኼዱ።
24ወደ፡ኰረብታውም፡በመጣ፡ጊዜ፡ከእጃቸው፡ወስዶ፡በቤቱ፡ውስጥ፡አኖራቸው፤ሰዎቹንም፡ አሰናበተ፥እነርሱም፡ኼዱ።
25ርሱ፡ግን፡ገብቶ፡በጌታው፡ፊት፡ቆመ፤ኤልሳዕም፦ግያዝ፡ሆይ፥ከወዴት፡ መጣኽ፧አለው።ርሱም፦እኔ፡ባሪያኽ፡ወዴትም፡አልኼድኹም፡አለ።
26ርሱም፦ያ፡ሰው፡ከሠረገላው፡ወርዶ፡ሊቀበልኽ፡በተመለሰ፡ጊዜ፡ልቤ፡ከአንተ፡ጋራ፡ አልኼደምን፧ብሩንና፡ልብሱን፥የወይራውንና፡የወይኑን፡ቦታ፥በጎችንና፡በሬዎችን፥ወንዶችንና፡ሴቶችን፡ ባሪያዎች፡ትቀበል፡ዘንድ፡ይህ፡ጊዜው፡ነውን፧
27እንግዲህስ፡የንዕማን፡ለምጽ፡ባንተ፡ላይ፥ለዘለዓለምም፡በዘርኽ፡ላይ፡ይጣበቃል፡አለው።እንደ፡በረዶም፡ ለምጻም፡ኾኖ፡ከርሱ፡ዘንድ፡ወጣ።