Skip to content
← 2 Kings

Chapter 6 · Amharic

2 Kings

1የነቢያትም፡ልጆች፡ኤልሳዕን፦እንሆ፥በፊትኽ፡የምንቀመጥበት፡ስፍራ፡ጠቦ፟ናል።

2ወደ፡ዮርዳኖስም፡እንኺድ፥ከእኛም፡እያንዳንዱ፡ከዚያ፡ምሰሶ፡ያምጣ፥የምንቀመጥበትንም፡ስፍራ፡በዚያ፡ እንሥራ፡አሉት፤ርሱም፦ኺዱ፡አለ።

3ከነርሱም፡አንዱ፦አንተ፡ደግሞ፡ከእኛ፡ከባሪያዎችኽ፡ጋራ፡ለመኼድ፡ፍቀድ፡አለ።ርሱም፦እኼዳለኹ፡ አለ።

4ከነርሱም፡ጋራ፡ኼደ፤ወደ፡ዮርዳኖስም፡በደረሱ፡ጊዜ፡ዕንጨት፡ቈረጡ።

5ከነርሱም፡አንዱ፡ምሰሶውን፡ሲቈርጥ፡የምሣሩ፡ብረት፡ወደ፡ውሃው፡ውስጥ፡ወደቀ፤ርሱም፦ጌታዬ፡ ሆይ፥ወየው! ወየው! የተዋስኹት፡ነበረ፡ብሎ፡ጮኸ።

6የእግዚአብሔርም፡ሰው፦የወደቀው፡ወዴት፡ነው፧አለ፡ስፍራውንም፡አሳየው፤ዕንጨትም፡ቈርጦ፡በዚያ፡ ጣለው፥ብረቱም፡ተንሳፈፈ።

7ርሱም፦ውሰደው፡አለ፤እጁንም፡ዘርግቶ፡ወሰደው።

8የሶርያም፡ንጉሥ፡ከእስራኤል፡ጋራ፡ይዋጋ፡ነበር፤ከባሪያዎቹም፡ጋራ፡ተማክሮ፦በዚህ፡ተደብቀን፡ እንሰፍራለን፡አለ።

9የእግዚአብሔርም፡ሰው፦ሶርያውያን፡በዚያ፡ተደብቀዋልና፥በዚያ፡ስፍራ፡እንዳታልፍ፡ተጠንቀቅ፡ብሎ፡ ወደእስራኤል፡ንጉሥ፡ላከ።

10የእስራኤልም፡ንጉሥ፡የእግዚአብሔር፡ሰው፡ወደነገረው፡ስፍራ፡ሰደደ፤አንድ፡ጊዜም፡ሳይኾን፥ኹለት፡ ጊዜም፡ሳይኾን፡በዚያ፡ራሱን፡አዳነ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

11የሶርያም፡ንጉሥ፡ልብ፡ስለዚህ፡እጅግ፡ታወከ፤ባሪያዎቹንም፡ጠርቶ፦ከእኛ፡ዘንድ፡ከእስራኤል፡ንጉሥ፡ ጋራ፡የተወዳጀ፡እንዳለ፡አትነግሩኝምን፧አላቸው።

12ከባሪያዎቹም፡አንዱ፦ጌታዬ፡ሆይ፥እንዲህ፡እኮ፡አይደለም፤ነገር፡ግን፥በዕልፍኝኽ፡ውስጥ፡ኾነኽ፡ የምትናገረውን፡በእስራኤል፡ዘንድ፡ያለ፡ነቢይ፡ኤልሳዕ፡ለእስራኤል፡ንጉሥ፡ይነግረዋል፡አለ።

13ርሱም፦ልኬ፡አስይዘው፡ዘንድ፡ኼዳችኹ፡ወዴት፡እንደ፡ኾነ፡እዩ፡አለ።እነርሱም፦እንሆ፥በዶታይን፡ አለ፡ብለው፡ነገሩት።

14ወደዚያም፡ፈረሶችንና፡ሠረገላዎችን፡እጅግም፡ጭፍራ፡ሰደደ፤በሌሊትም፡መጥተው፡ከተማዪቱን፡ከበቡ።

15የእግዚአብሔር፡ሰው፡ሎሌ፡ማለዳ፡ተነሥቶ፡በወጣ፡ጊዜ፥እንሆ፥በከተማዪቱ፡ዙሪያ፡ጭፍራና፡ፈረሶች፡ ሠረገላዎችም፡ነበሩ።ሎሌውም፦ጌታዬ፡ሆይ፥ወዮ! ምን፡እናደርጋለን፧አለው።

16ርሱም፦ከእኛ፡ጋራ፡ያሉት፡ከነርሱ፡ጋራ፡ካሉት፡ይበልጣሉና፡አትፍራ፡አለው።

17ኤልሳዕም፦አቤቱ፥ያይ፡ዘንድ፡ዐይኖቹን፥እባክኽ፥ግለጥ፡ብሎ፡ጸለየ።እግዚአብሔርም፡የብላቴናውን፡ ዐይኖች፡ገለጠ፥አየም፤እንሆም፥በኤልሳዕ፡ዙሪያ፡ያሉት፡የእሳት፡ፈረሶችና፡ሠረገላዎች፡ተራራውን፡ ሞልተውት፡ነበር።

18ወደ፡ርሱም፡በወረዱ፡ጊዜ፡ኤልሳዕ፦ይህን፡ሕዝብ፡ዕውር፡ታደርገው፡ዘንድ፡እለምንኻለኹ፡ብሎ፡ወደ፡ እግዚአብሔር፡ጸለየ።ኤልሳዕም፡እንደተናገረው፡ቃል፡ዕውር፡አደረጋቸው።

19ኤልሳዕም፦መንገዱ፡በዚህ፡አይደለም፥ከተማዪቱም፡ይህች፡አይደለችም፤የምትሹትን፡ሰው፡አሳያችኹ፡ ዘንድ፡ተከተሉኝ፡አላቸው፤ወደ፡ሰማርያም፡መራቸው።

20ወደ፡ሰማርያም፡በገቡ፡ጊዜ፥ኤልሳዕ፦አቤቱ፥ያዩ፡ዘንድ፡የእነዚህን፡ሰዎች፡ዐይኖች፡ግለጥ፡ አለ፤እግዚአብሔርም፡ዐይኖቻቸውን፡ገለጠ፥እነርሱም፡አዩ።እንሆም፥በሰማርያ፡መካከል፡ነበሩ።

21የእስራኤልም፡ንጉሥ፡ባያቸው፡ጊዜ፡ኤልሳዕን፦አባቴ፡ሆይ፥ልግደላቸውን፧ልግደላቸውን፧አለው።

22ርሱም፦አትግደላቸው፤በሰይፍኽና፡በቀስትኽ፡የማረክኸውን፡ትገድል፡ዘንድ፡ይገ፟ባኻ ፟ ልን፧እንጀራና፡ውሃ፡ በፊታቸው፡አኑርላቸው፥በልተውና፡ጠጥተውም፡ወደ፡ጌታቸው፡ይኺዱ፡አለው።

23ብዙም፡መብል፡አዘጋጀላቸው፤በበሉና፡በጠጡ፡ጊዜም፡አሰናበታቸው፥እነርሱም፡ወደ፡ጌታቸው፡ ኼዱ።ከዚያም፡በዃላ፡የሶርያ፡አደጋ፡ጣዮች፡ወደእስራኤል፡አገር፡አልመጡም።

24ከዚያም፡በዃላ፡የሶርያ፡ንጉሥ፡ወልደ፡አዴር፡ሰራዊቱን፡ዅሉ፡ሰበሰበ፥ወጥቶም፡ሰማርያን፡ከበባት።

25በሰማርያም፡ታላቅ፡ራብ፡ኾኖ፡ነበር፤እንሆም፥የአህያ፡ራስ፡በዐምሳ፡ብር፥የርግብም፡ኩስ፡የጎሞር፡ ስምንተኛ፡የሚኾን፡በዐምስት፡ብር፡እስኪሸጥ፡ድረስ፡ከበቧት።

26የእስራኤልም፡ንጉሥ፡በቅጥር፡ላይ፡በተመላለሰ፡ጊዜ፡አንዲት፡ሴት፡ጌታዬ፡ንጉሥ፡ሆይ፥ርዳኝ፡ብላ፡ ወደ፡ርሱ፡ጮኸች።

27ርሱም፦እግዚአብሔር፡ያልረዳሽን፡እኔ፡እንዴት፡እረዳሻለኹ፧ከዐውድማው፡ወይስ፡ከመጥመቂያው፡ ነውን፧አለ።

28ንጉሡም፦ምን፡ኾነሻል፧አላት፤ርሷም፦ይህች፡ሴት።ዛሬ፡እንድንበላው፡ልጅሽን፡አምጪ፤ነገም፡ ልጄን፡እንበላለን፡አለችኝ።

29ልጄንም፡ቀቅለን፡በላነው፤በማግስቱም፦እንድንበላው፡ልጅሽን፡አምጪ፡አልዃት፤ልጇንም፡ሸሸገችው፡ ብላ፡መለሰችለት።

30ንጉሡም፡የሴቲቱን፡ቃል፡ሰምቶ፡ልብሱን፡ቀደደ፤በቅጥርም፡ይመላለስ፡ነበር፤ሕዝቡም፡በስተውስጥ፡ በሥጋው፡ላይ፡ለብሶት፡የነበረውን፡ማቅ፡አዩ።

31ንጉሡም፦የሣፋጥ፡ልጅ፡የኤልሳዕ፡ራስ፡ዛሬ፡በላዩ፡ያደረ፡እንደ፡ኾነ፡እግዚአብሔር፡ይህን፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ያድርግብኝ፥ይህንም፡ይጨምርብኝ፡አለ።

32ኤልሳዕ፡ግን፡በቤቱ፡ተቀምጦ፡ነበር፥ሽማግሌዎችም፡ከርሱ፡ጋራ፡ተቀምጠው፡ነበር፤ንጉሡ፡ሰው፡ ላካ፤መልእክተኛውም፡ገና፡ሳይደርስ፡ለሽማግሌዎች፦ይህ፡የነፍሰ፡ገዳይ፡ልጅ፡ራሴን፡ይቈርጥ፡ዘንድ፡ እንደ፡ላከ፡እዩ፤መልእከተኛውም፡በመጣ፡ጊዜ፡ደጁን፡ዘግታችኹ፡ከልክሉት፤የጌታው፡የእግሩ፡ኰቴ፡ በዃላው፡ነው፡አላቸው።

33ሲናገራቸውም፡መልእክተኛው፡ወደ፡ርሱ፡ደረሰ፤ርሱም፦እንሆ፥ይህ፡ክፉ፡ነገር፡ከእግዚአብሔር፡ ዘንድ፡ነው፥እግዚአብሔርን፡ገና፡እጠብቅ፡ዘንድ፡ምንድር፡ነኝ፧አለ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source