Skip to content
← 2 Kings

Chapter 7 · Amharic

2 Kings

1ኤልሳዕም፦የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ነገ፡በዚህ፡ጊዜ፡በሰማርያ፡በር፡ አንድ፡መስፈሪያ፡መልካም፡ዱቄት፡ባንድ፡ሰቅል፥ኹለትም፡መስፈሪያ፡ገብስ፡ባንድ፡ሰቅል፡ይሸመታል፡አለ።

2ንጉሡም፡በእጁ፡ተደግፎ፡የነበረ፡አለቃ፡ለእግዚአብሔር፡ሰው፡መልሶ፦እንሆ፥እግዚአብሔር፡በሰማይ፡ መስኮቶች፡ቢያደርግ፡ይህ፡ነገር፡ይኾናልን፧አለው።ርሱም፦እንሆ፥በዐይኖችኽ፡ታየዋለኽ፥ከዚያም፡ አትቀምስም፡አለ።

3በበሩም፡መግቢያ፡አራት፡ለምጻም፡ሰዎች፡ነበሩ፤ርስ፡በርሳቸውም፦እስክንሞት፡ድረስ፡በዚህ፡ለምን፡ እንቀመጣለን፧

4ወደ፡ከተማ፡እንገባ፡ዘንድ፡ብንወድ፟፡ራብ፡በከተማ፡አለ፥በዚያም፡እንሞታለን፤በዚህም፡ብንቀመጥ፡ እንሞታለን።እንግዲህ፡ኑ፥ወደሶርያውያን፡ሰፈር፡እንሽሽ፤በሕይወት፡ቢያኖሩን፡እንኖራለን፤ቢገድሉንም፡ እንሞታለን፡ተባባሉ።

5ጨለምለም፡ባለ፡ጊዜ፡ወደሶርያውያን፡ሰፈር፡ይኼዱ፡ዘንድ፡ተነሡ፤ወደሶርያውያንም፡ሰፈር፡መዠመሪያ፡ ዳርቻ፡በመጡ፡ጊዜ፥እንሆ፥ማንም፡አልነበረም።

6እግዚአብሔር፡ለሶርያውያን፡የሠረገላና፡የፈረስ፡የብዙም፡ጭፍራ፡ድምፅ፡አሰምቶ፡ነበር፤ርስ፡ በርሳቸውም፦እንሆ፥የእስራኤል፡ንጉሥ፡የኬጢያውያንና፡የግብጻውያንን፡ነገሥት፡ቀጥሮ፡አምጥቶብናል፡ ይባባሉ፡ነበር።

7ስለዚህም፡ተነሥተው፡በጨለማ፡ሸሹ፤ድንኳኖቻቸውንና፡ፈረሶቻቸውን፡አህያዎቻቸውንና፡ሰፈሩን፡እንዳለ፡ ትተው፡ነፍሳቸውን፡ያድኑ፡ዘንድ፡ሸሹ።

8እነዚህም፡ለምጻሞች፡ወደሰፈሩ፡መዠመሪያ፡ዳርቻ፡በመጡ፡ጊዜ፡ወደ፡አንድ፡ድንኳን፡ገብተው፡በሉ፡ ጠጡም፥ከዚያም፡ወርቅና፡ብር፡ልብስም፡ወሰዱ፥ኼደውም፡ሸሸጉት፤ተመልሰውም፡ወደ፡ሌላ፡ድንኳን፡ ገቡ፥ከዚያም፡ደግሞ፡ወስደው፡ሸሸጉ።

9ከዚያም፡ወዲያ፡ርስ፡በርሳቸው።መልካም፡አላደረግንም፤ዛሬ፡የመልካም፡ምሥራች፡ቀን፡ነው፥እኛም፡ ዝም፡ብለናል፤እስኪነጋም፡ድረስ፡ብንቈይ፡በደለኛዎች፡እንኾናለን፤ኑ፥እንኺድ፤ለንጉሥ፡ቤተ፡ሰብ፡ እንናገር፡ተባባሉ።

10መጥተውም፦ወደሶርያውያን፡ሰፈር፡መጣን፥እንሆም፥ፈረሶችና፡አህያዎች፡ታስረው፥ድንኳኖችም፡ ተተክለው፡ነበር፡እንጂ፡ሰው፡አልነበረም፥የሰውም፡ድምፅ፡አልነበረም፡ብለው፡ወደከተማዪቱ፡ደጅ፡ጠባቂ፡ ጮኹ።

11የደጁም፡ጠባቂዎች፡ጠሩ፥ለንጉሡም፡ቤት፡ውስጥ፡አወሩ።

12ንጉሡም፡በሌሊት፡ተነሥቶ፡ባሪያዎቹን፦ሶርያውያን፡ያደረጉብንን፡እነግራችዃለኹ፤እንደ፡ተራብን፡ ያውቃሉ፤ስለዚህ፦ከከተማዪቱ፡በወጡ፡ጊዜ፡በሕይወታቸው፡እንይዛቸዋለን፥ወደ፡ከተማም፡እንገባለን፡ ብለው፡በሜዳ፡ይሸሸጉ፡ዘንድ፡ከሰፈሩ፡ወጥተዋል፡አላቸው። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

13ከባሪያዎቹም፡አንዱ፡መልሶ፦በከተማ፡ከቀሩት፡ፈረሶች፡ዐምስት፡ይውሰዱ፤እንሆ፥እንደ፡ቀሩት፡እንደ፡ እስራኤል፡ወገን፡ዅሉ፡ናቸው፤እንሆ፥እንዳለቁ፡እንደ፡እስራኤል፡ወገን፡ዅሉ፡ናቸው፤እንስደድም፥እንይም፡ አለ።

14ኹለትም፡ሠረገላዎች፡ከፈረሶች፡ጋራ፡ወሰዱ፤ንጉሡም፦ኼዳችኹ፡እዩ፡ብሎ፡ከሶርያውያን፡ሰራዊት፡ በዃላ፡ላከ።

15በዃላቸው፡እስከ፡ዮርዳኖስ፡ድረስ፡ኼዱ፤እንሆም፥ሶርያውያን፡ሲሸሹ፡የጣሉት፡ልብስና፡ዕቃ፡ መንገዱን፡ዅሉ፡ሞልቶ፡ነበር።መልእክተኛዎችም፡ተመልሰው፡ለንጉሡ፡ነገሩት።

16ሕዝቡም፡ወጥቶ፡የሶርያውያንን፡ሰፈር፡በዘበዘ፤እንደእግዚአብሔርም፡ቃል፡አንድ፡መስፈሪያ፡መልካም፡ ዱቄት፡ባንድ፡ሰቅል፥ኹለትም፡መስፈሪያ፡ገብስ፡ባንድ፡ሰቅል፡ተሸመተ።

17ንጉሡም፡ያን፡እጁን፡ይደግፈው፡የነበረውን፡አለቃ፡በሩን፡ይጠብቅ፡ዘንድ፡አቆመው።ሕዝቡም፡በበሩ፡ ረገጠው፥ንጉሡም፡ወደ፡ርሱ፡በወረደ፡ጊዜ፡የእግዚአብሔር፡ሰው፡እንደ፡ተናገረው፡ሞተ።

18የእግዚአብሔርም፡ሰው፡ለንጉሡ፦ነገ፡በዚህ፡ጊዜ፡በሰማርያ፡በር፡ኹለት፡መስፈሪያ፡ገብስ፡ባንድ፡ ሰቅል፥አንድም፡መስፈሪያ፡መልካም፡ዱቄት፡ባንድ፡ሰቅል፡ይሸመታል፡ብሎ፡እንደተናገረው፡ነገር፡እንዲሁ፡ ኾነ።

19ያም፡አለቃ፡ለእግዚአብሔር፡ሰው፡መልሶ፦እንሆ፥እግዚአብሔር፡በሰማይ፡መስኮቶች፡ቢያደርግ፡ይህ፡ ነገር፡ይኾናልን፧ብሎ፡ነበር፤ርሱም፦እንሆ፥በዐይኖችኽ፡ታየዋለኽ፥ከዚያም፡አትቀምስም፡ብሎት፡ነበር።

20እንዲሁም፡ደረሰበት፤ሕዝቡም፡በበሩ፡ረገጠውና፡ሞተ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source