Skip to content
← 2 Kings

Chapter 8 · Amharic

2 Kings

1ኤልሳዕም፡ልጇን፡ያስነሣላትን፡ሴት፦አንቺ፡ከቤተ፡ሰብሽ፡ጋራ፡ተነሥተሽ፡ኺጂ፥በምታገኚውም፡ስፍራ፡ ተቀመጪ፤እግዚአብሔር፡ራብ፡ጠርቷል፤ሰባት፡ዓመትም፡በምድር፡ላይ፡ይመጣል፡ብሎ፡ተናገራት።

2ሴቲቱም፡ተነሥታ፡እንደእግዚአብሔር፡ሰው፡ቃል፡አደረገች፤ከቤተ፡ሰቧም፡ጋራ፡ኼዳ፡በፍልስጥኤም፡ አገር፡ሰባት፡ዓመት፡ተቀመጠች።

3ሰባቱም፡ዓመት፡በተፈጸመ፡ጊዜ፡ሴቲቱ፡ከፍልስጥኤም፡አገር፡ተመለሰች፤ስለ፡ቤቷና፡ስለ፡መሬቷ፡ ልትጮኽ፡ወደ፡ንጉሡ፡ወጣች።

4ንጉሡም፡ከእግዚአብሔር፡ሰው፡ሎሌ፡ከግያዝ፡ጋራ።ኤልሳዕ፡ያደረገውን፡ተኣምራት፡ዅሉ፡ንገረኝ፡ እያለ፡ይጫወት፡ነበር።

5ርሱም፡የሞተውን፡እንደ፡አስነሣ፡ለንጉሡ፡ሲናገር፥እንሆ፥ልጇን፡ያስነሣላት፡ሴት፡ስለ፡ቤቷና፡ስለ፡ መሬቷ፡ወደ፡ንጉሥ፡ጮኸች፤ግያዝም፦ጌታዬ፡ንጉሥ፡ሆይ፥ሴቲቱ፡ይህች፡ናት፥ኤልሳዕም፡ያስነሣው፡ ልጇ፡ይህ፡ነው፡አለ።

6ንጉሡም፡ሴቲቱን፡ጠየቀ፥ነገረችውም።ንጉሡም፦የነበረላትን፡ዅሉ፥መሬቷንም፡ከተወች፡ዠምራ፡ እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ያለውን፡የዕርሻዋን፡ፍሬ፡ዅሉ፡መልስላት፡ብሎ፡ስለ፡ርሷ፡ጃን፡ደረባውን፡አዘዘ።

7ኤልሳዕም፡ወደ፡ደማስቆ፡መጣ፤የሶርያም፡ንጉሥ፡ወልደ፡አዴር፡ታሞ፟፡ ነበር፤ወሬኛዎችም፦የእግዚአብሔር፡ሰው፡ወደዚህ፡መጥቷል፡ብለው፡ነገሩት።

8ንጉሡም፡አዛሄልን፦ገጸ፡በረከት፡በእጅኽ፡ወስደኽ፡የእግዚአብሔርን፡ሰው፡ልትገናኝ፡ኺድ፤በርሱም፡ አፍ።ከዚህ፡በሽታ፡እድናለኹን፧ብለኽ፡እግዚአብሔርን፡ጠይቅ፡አለው።

9አዛሄልም፡ሊገናኘው፡ኼደ፥ከርሱም፡ጋራ፡ከደማስቆ፡መልካሙን፡ነገር፡ዅሉ፡የአርባ፡ግመል፡ጭነት፡ ገጸ፡በረከት፡ወሰደ፤መጥቶም፡በፊቱ፡ቆመና፦ልጅኽ፡የሶርያ፡ንጉሥ፡ወልደ፡አዴር።ከዚህ፡በሽታ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org እድናለኹን፧ሲል፡ወዳንተ፡ልኮኛል፡አለ።

10ኤልሳዕም፦ኺድ፥መዳንስ፡ትድናለኽ፡በለው፤ነገር፡ግን፥እንዲሞት፡እግዚአብሔር፡አሳይቶኛል፡አለው።

11እስኪያፍርም፡ድረስ፡ትኵር፡ብሎ፡ተመለከተው፤የእግዚአብሔርም፡ሰው፡አነባ።

12አዛሄልም፦ጌታዬ፡ለምን፡ያነባል፧አለ።ርሱም፦በእስራኤል፡ልጆች፡ላይ፡የምታደርገውን፡ክፋት፡ ስለማውቅ፡ነው፤ምሽጎቻቸውን፡በእሳት፡ታቃጥላለኽ፥ጕልማሳዎቻቸውንም፡በሰይፍ፡ ትገድላለኽ፥ሕፃናታቸውንም፡ትፈጠፍጣለኽ፥እርጕዞቻቸውንም፡ትቀዳ፟ለኽ፡አለው።

13አዛሄልም፦ይህን፡ታላቅ፡ነገር፡ኣደርግ፡ዘንድ፡እኔ፡ውሻ፡ባሪያኽ፡ምንድር፡ ነኝ፧አለ።ኤልሳዕም፦አንተ፡በሶርያ፡ላይ፡ንጉሥ፡እንድትኾን፡እግዚአብሔር፡አሳይቶኛል፡አለው።

14ከኤልሳዕም፡ርቆ፡ወደ፡ጌታው፡መጣ፤ርሱም፦ኤልሳዕ፡ምን፡አለኽ፧አለው።

15ርሱም፦እንድትፈወስ፡ነገረኝ፡አለው።በነጋውም፡ለሐፍ፡ወስዶ፡በውሃ፡ነከረው፡በፊቱም፡ላይ፡ ሸፈነው፥ሞተም።አዛሄልም፡በፋንታው፡ነገሠ።

16በእስራኤልም፡ንጉሥ፡በአክአብ፡ልጅ፡በኢዮራም፡በዐምስተኛው፡ዓመት፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡የኢዮሳፍጥ፡ ልጅ፡ኢዮራም፡ነገሠ።

17መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የሠላሳ፡ኹለት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፤በኢየሩሳሌምም፡ስምንት፡ዓመት፡ ነገሠ።

18የአክአብንም፡ልጅ፡አግብቶ፡ነበርና፥የአክአብ፡ቤት፡እንዳደረገ፡በእስራኤል፡ነገሥታት፡መንገድ፡ ኼደ፤በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ክፉ፡አደረገ።

19ነገር፡ግን፥ለርሱና፡ለልጆቹ፡ለዘመኑ፡ዅሉ፡መብራት፡ይሰጠው፡ዘንድ፡ተስፋ፡እንደ፡ሰጠ፥ስለ፡ ባሪያው፡ስለ፡ዳዊት፡እግዚአብሔር፡ይሁዳን፡ያጠፋ፡ዘንድ፡አልወደደም።

20በርሱም፡ዘመን፡ኤዶምያስ፡ለይሁዳ፡እንዳይገብር፡ሸፈተ፥በላያቸውም፡ንጉሥ፡አነገሡ።

21ኢዮራምም፡ከሠረገላዎቹ፡ዅሉ፡ጋራ፡ወደ፡ጸዒር፡ዐለፈ፤በሌሊትም፡ተነሥቶ፡ርሱንና፡የሠረገላዎቹን፡ አለቃዎች፡ከበ፟ው፡የነበሩትን፡የኤዶምያስን፡ሰዎች፡መታ፤ሕዝቡ፡ግን፡ወደ፡ድንኳኑ፡ሸሸ።

22ኤዶምያስ፡ግን፡ለይሁዳ፡እንዳይገብር፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ሸፈተ።በዚያም፡ዘመን፡ደግሞ፡ልብና፡ሸፈተ።

23የተረፈውም፡የኢዮራም፡ነገር፥ያደረገውም፡ዅሉ፥በይሁዳ፡ነገሥታት፡ታሪክ፡መጽሐፍ፡የተጻፈ፡ አይደለምን፧

24ኢዮራምም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በዳዊትም፡ከተማ፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡ተቀበረ፤በፋንታውም፡ልጁ፡ አካዝያስ፡ነገሠ።

25በእስራኤል፡ንጉሥ፡በአክአብ፡ልጅ፡በኢዮራም፡በዐሥራ፡ኹለተኛው፡ዓመት፡የይሁዳ፡ንጉሥ፡የኢዮራም፡ ልጅ፡አካዝያስ፡ነገሠ።

26መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡አካዝያስ፡የኻያ፡ኹለት፡ዓመት፡ጕልማሳ፡ነበረ፤በኢየሩሳሌምም፡አንድ፡ ዓመት፡ነገሠ።እናቱም፡ጎቶልያ፡የተባለች፡የእስራኤል፡ንጉሥ፡የዘንበሪ፡ልጅ፡ነበረች።

27በአክአብም፡ቤት፡መንገድ፡ኼደ፥እንደ፡አክአብም፡ቤት፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡አደረገ፤ለአክአብ፡ ቤት፡ዐማች፡ነበረና።

28ከአክአብም፡ልጅ፡ከኢዮራም፡ጋራ፡የሶርያን፡ንጉሥ፡አዛሄልን፡በሬማት፡ዘገለዓድ፡ሊጋጠም፡ ኼደ፤ሶርያውንም፡ኢዮራምን፡አቈሰሉት።

29ንጉሡም፡ኢዮራም፡ከሶርያ፡ንጉሥ፡ከአዛሄል፡ጋራ፡በተዋጋ፡ጊዜ፡ሶርያውያን፡በሬማት፡ያቈሰሉትን፡ ቍስል፡ይታከም፡ዘንድ፡ወደ፡ኢይዝራኤል፡ተመለሰ።የአክአብም፡ልጅ፡ኢዮራም፡ታሞ፟፡ነበርና፥የይሁዳ፡ ንጉሥ፡የኢዮራም፡ልጅ፡አካዝያስ፡ሊያየው፡ወደ፡ኢይዝራኤል፡ወረደ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source