Skip to content
← 2 Samuel

Chapter 10 · Amharic

2 Samuel

1ከዚህ፡በዃላ፡የዐሞን፡ልጆች፡ንጉሥ፡ሞተ፥ልጁም፡ሐኖን፡በፋንታው፡ነገሠ።

2ዳዊትም፦አባቱ፡ወረታ፡እንዳደረገልኝ፡እኔ፡ለናዖስ፡ልጅ፡ለሐኖን፡ቸርነት፡አደርጋለኹ፡አለ።ዳዊትም፡ አባቱ፡ስለ፡ሞተ፡ሊያጽናናው፡ባሪያዎቹን፡ላከ፤የዳዊትም፡ባሪያዎች፡ወደዐሞን፡ልጆች፡አገር፡መጡ።

3የዐሞንም፡ልጆች፡አለቃዎች፡ጌታቸውን፡ሐኖንን፦ዳዊት፡አባትኽን፡አክብሮ፡ሊያጽናናኽ፡ባሪያዎቹን፡ ወዳንተ፡የላከ፡ይመስልኻልን፧ዳዊትስ፡ከተማዪቱን፡ለመመርመርና፡ለመሰለል፡ለማጥፋትም፡ባሪያዎቹን፡የላከ፡ አይደለምን፧አሉት።

4ሐኖንም፡የዳዊትን፡ባሪያዎች፡ወስዶ፡የጢማቸውን፡ገሚስ፡ላጨ፥ልብሳቸውንም፡እስከ፡ወገባቸው፡ድረስ፡ ከኹለት፡ቀዶ፟፡ሰደዳቸው።

5ዳዊትም፡ያን፡በሰማ፡ጊዜ፥ሰዎቹ፡እጅግ፡ዐፍረው፡ነበርና፥ተቀባዮች፡ላከ።ንጉሡም፦ጢማችኹ፡ እስኪያድግ፡ድረስ፡በኢያሪኮ፡ተቀመጡ፥ከዚያም፡በዃላ፡ተመለሱ፡አላቸው።

6የዐሞን፡ልጆች፡በዳዊት፡ዘንድ፡አንደ፡ተጠሉ፡ባዩ፡ጊዜ፥የዐሞን፡ልጆች፡ልከው፡ከሶርያውያን፡ ከቤትሮዖብና፡ከሱባ፡ኻያ፡ሺሕ፡እግረኛዎች፥ከመዓካ፡ንጉሥም፡አንድ፡ሺሕ፡ሰዎች፥ከጦብም፡ዐሥራ፡ ኹለት፡ሺሕ፡ሰዎች፡ቀጠሩ።

7ዳዊትም፡በሰማ፡ጊዜ፡ኢዮአብንና፡የኀያላኑን፡ሰራዊት፡ዅሉ፡ላከ።

8የዐሞንም፡ልጆች፡ወጥተው፡በበሩ፡መግቢያ፡ፊት፡ለፊት፡ተሰለፉ፤የሱባና፡የረአብ፡ሶርያውያን፥የጦብና፡ የመዓካም፡ሰዎች፡ለብቻቸው፡በሰፊ፡ሜዳ፡ላይ፡ነበሩ።

9ኢዮአብም፡በፊትና፡በዃላ፡ሰልፍ፡እንደ፡ከበበው፡ባየ፡ጊዜ፡ከእስራኤል፡ምርጥ፡ምርጦቹን፡ዅሉ፡ መረጠ፥በሶርያውያንም፡ፊት፡ለሰልፍ፡አኖራቸው።

10የቀረውንም፡ሕዝብ፡በወንድሙ፡በአቢሳ፡እጅ፡አድርጎ፡በዐሞን፡ልጆች፡ፊት፡ለሰልፍ፡አኖራቸው።

11ሶርያውያን፡ቢበረቱብኝ፡ትረዳኛለኽ፤የዐሞን፡ልጆች፡ቢበረቱብኽ፡እኔ፡መጥቼ፡እረዳኻለኹ።

12አይዞኽ፤ስለ፡ሕዝባችንና፡ስለ፡አምላካችንም፡ከተማዎች፡እንበርታ፤እግዚአብሔርም፡ደስ፡ያሠኘውን፡ ያድርግ፡አለ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

13ኢዮአብና፡ከርሱም፡ጋራ፡የነበረው፡ሕዝብ፡ከሶርያውያን፡ጋራ፡ሊዋጉ፡ቀረቡ፥እነርሱም፡ከፊቱ፡ሸሹ።

14የዐሞንም፡ልጆች፡ሶርያውያን፡እንደ፡ሸሹ፡ባዩ፡ጊዜ፡እነርሱ፡ደግሞ፡ከአቢሳ፡ፊት፡ሸሹ፥ወደ፡ ከተማዪቱም፡ገቡ፤ኢዮአብም፡ከዐሞን፡ልጆች፡ዘንድ፡ተመልሶ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡መጣ።

15ሶርያውያንም፡በእስራኤል፡ፊት፡እንደ፡ተሸነፉ፡ባዩ፡ጊዜ፡በአንድነት፡ተሰበሰቡ።

16አድርዐዛርም፡ልኮ፡በወንዝ፡ማዶ፡የነበሩትን፡ሶርያውያን፥አመጣ፤ወደ፡ዔላምም፡መጡ፥የአድርዐዛርም፡ ሰራዊት፡አለቃ፡ሶባክ፡በፊታቸው፡ነበረ።

17ዳዊትም፡በሰማ፡ጊዜ፡እስራኤልን፡ዅሉ፡ሰበሰበ፥ዮርዳኖስንም፡ተሻግሮ፡ወደዔላም፡መጣ፤ሶርያውያንም፡ በዳዊት፡ፊት፡ተሰልፈው፡ከርሱ፡ጋራ፡ተዋጉ።

18ሶርያውያንም፡ከእስራኤል፡ፊት፡ሸሹ፤ዳዊትም፡ከሶርያውያን፡ሰባት፡መቶ፡ሠረገለኛዎች፡አርባ፡ሺሕም፡ ፈረሰኛዎች፡ገደለ፤የሰራዊቱንም፡አለቃ፡ሶባክን፡መታ፥ርሱም፡በዚያ፡ሞተ።

19ለአድርዐዛርም፡የሚገብሩ፡ነገሥታት፡ዅሉ፡በእስራኤል፡ፊት፡እንደ፡ተሸነፉ፡ባዩ፡ጊዜ፡ከእስራኤል፡ጋራ፡ ታረቁ፥ገበሩላቸውም፦ሶርያውያንም፡ከዚያ፡ወዲያ፡የዐሞንን፡ልጆች፡ይረዱ፡ዘንድ፡ፈሩ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source