Skip to content
← 2 Samuel

Chapter 11 · Amharic

2 Samuel

1እንዲህም፡ኾነ፤በዓመቱ፡መለወጫ፡ነገሥታት፡ወደ፡ሰልፍ፡በሚወጡበት፡ጊዜ፥ዳዊት፡ኢዮአብን፡ ከርሱም፡ጋራ፡ባሪያዎቹን፡እስራኤልንም፡ዅሉ፡ሰደደ።የዐሞንም፡ልጆች፡አገር፡አጠፉ፥ረባትንም፡ ከበቡ፤ዳዊት፡ግን፡በኢየሩሳሌም፡ቀርቶ፡ነበር።

2እንዲህም፡ኾነ፤ወደ፡ማታ፡ጊዜ፡ዳዊት፡ከምንጣፉ፡ተነሣ፥በንጉሥም፡ቤት፡በሰገነት፡ላይ፡ ተመላለሰ፤በሰገነቱ፡ሳለ፡አንዲት፡ሴት፡ስትታጠብ፡አየ፤ሴቲቱም፡መልከ፡መልካም፡ነበረች።

3ዳዊትም፡ልኮ፡ስለ፡ሴቲቱ፡ጠየቀ፤አንድ፡ሰውም፦ይህች፡የኤልያብ፡ልጅ፡የኬጢያዊው፡የኦርዮ ፡ ሚስት፡ቤርሳቤሕ፡አይደለችምን፧አለ።

4ዳዊትም፡መልእክተኛዎች፡ልኮ፡አስመጣት፤ወደ፡ርሱም፡ገባች፥ከርኵሰቷም፡ነጽታ፡ነበርና፥ከርሷ፡ጋራ፡ ተኛ፤ወደ፡ቤቷም፡ተመለሰች።

5ሴቲቱም፡አረገዘች፥ወደ፡ዳዊትም፦አርግዤያለኹ፡ብላ፡ላከችበት።

6ዳዊትም፡ወደ፡ኢዮአብ፦ኬጢያዊውን፡ኦርዮን፡ስደድልኝ፡ብሎ፡ላከ።ኢዮአብም፡ኦርዮን፡ወደ፡ዳዊት፡ ሰደደው።

7ኦርዮም፡ወደ፡ርሱ፡በመጣ፡ጊዜ፡ዳዊት፡የኢዮአብንና፡የሕዝቡን፡ደኅንነት፥ሰልፉም፡እንዴት፡እንደ፡ኾነ፡ ጠየቀው።

8ዳዊትም፡ኦርዮን፦ወደ፡ቤትኽ፡ኺድ፥እግርኽንም፡ታጠብ፡አለው።ኦርዮም፡ከንጉሡ፡ቤት፡ሲወጣ፡ ማለፊያ፡የንጉሥ፡መብል፡ተከትሎት፡ኼደ።

9ኦርዮ፡ግን፡ከጌታው፡ባሪያዎች፡ዅሉ፡ጋራ፡በንጉሥ፡ቤት፡ደጅ፡ተኛ፥ወደ፡ቤቱም፡አልወረደም።

10ኦርዮ፡ወደ፡ቤቱ፡አልኼደም፡ብለው፡ለዳዊት፡ነገሩት፤ዳዊትም፡ኦርዮን፦አንተ፡ከመንገድ፡የመጣኽ፡ አይደለምን፧ስለ፡ምን፡ወደ፡ቤትኽ፡አልወረድኽም፧አለው።

11ኦርዮም፡ዳዊትን፦ታቦቱና፡እስራኤል፡ይሁዳም፡በጐዦ፡ተቀምጠዋል፤ጌታዬ፡ኢዮአብና፡የጌታዬም፡ ባሪያዎች፡በሰፊ፡ሜዳ፡ሰፍረዋል፤እኔ፡ልበላና፡ልጠጣ፡ወይስ፡ከሚስቴ፡ጋራ፡ልተኛ፡ወደ፡ቤቴ፡ እኼዳለኹን፧በሕይወትኽና፡በሕያው፡ነፍስኽ፡እምላለኹ! ይህን፡ነገር፡አላደርገውም፡አለው። 152 ዕብ.፥ኡሪያህ፡(የጌታ፡ነበልባል)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

12ዳዊትም፡ኦርዮን፦ዛሬ፡ደግሞ፡በዚህ፡ተቀመጥ፥ነገም፡አሰናብትኻለኹ፡አለው።ኦርዮም፡በዚያ፡ቀንና፡ በነጋው፡በኢየሩሳሌም፡ተቀመጠ።

13ዳዊትም፡ጠራው፥በፊቱም፡በላና፡ጠጣ፥አሰከረውም፤ነገር፡ግን፥በመሸ፡ጊዜ፡ወጥቶ፡ከጌታው፡ ባሪያዎች፡ጋራ፡በምንጣፉ፡ላይ፡ተኛ፥ወደ፡ቤቱም፡አልወረደም።

14በነጋም፡ጊዜ፥ዳዊት፡ለኢዮአብ፡ደብዳቤ፡ጻፈ፥በኦርዮም፡እጅ፡ላከው።

15በደብዳቤውም፦ኦርዮን፡ጽኑ፡ሰልፍ፡ባለበት፡በፊተኛው፡ስፍራ፡አቁሙት፥ተመቶ፟ም፡ይሞት፡ዘንድ፡ ከዃላው፡ሽሹ፡ብሎ፡ጻፈ።

16ኢዮአብም፡ከተማዪቱን፡በከበበ፡ጊዜ፥ዠግናዎች፡እንዳሉበት፡በሚያውቀው፡ስፍራ፡ኦርዮን፡አቆመው።

17የከተማዪቱም፡ሰዎች፡ወጥተው፡ከኢዮአብ፡ጋራ፡ተዋጉ፤ከዳዊትም፡ባሪያዎች፡ከሕዝቡ፡አንዳንዱ፡ ወደቁ፤ኬጢያዊው፡ኦርዮም፡ደግሞ፡ሞተ።

18ኢዮአብም፡ልኮ፡በሰልፍ፡የኾነውን፡ዅሉ፡ለዳዊት፡ነገረው።

19ለመልእክተኛውም፡እንዲህ፡ብሎ፡አዘዘው።የሰልፉን፡ነገር፡ዅሉ፡ለንጉሡ፡ነግረኽ፡በፈጸምኽ፡ጊዜ፦

20ስትዋጉ፡ወደ፡ከተማዪቱ፡ለምን፡ቀረባችኹ፧ከቅጥሩ፡በላይ፡ፍላጻ፡እንዲወረወር፡አታውቁምን፧

21የሩቤሼትን፡ልጅ፡አቢሜሌክን፡ማን፡ገደለው፧ከቅጥር፡ላይ፡የወፍጮ፡መጅ፡ጥላ፡በቴቤስ፡ላይ፡ የገደለችው፡አንዲት፡ሴት፡አይደለችምን፧ስለ፡ምን፡ወደ፡ቅጥሩ፡እንደዚህ፡ቀርባችኹ፧ብሎ፡ንጉሡ፡ሲቈጣ፡ ብታይ፥አንተ፦ባሪያኽ፡ኬጢያዊው፡ኦርዮ፡ደግሞ፡ሞተ፡በለው።

22መልእክተኛውም፡ተነሥቶ፡ኼደ፥ኢዮአብም፡ያዘዘውን፡ዅሉ፡ለዳዊት፡ነገረው።

23መልእክተኛውም፡ዳዊትን፦ሰዎቹ፡በረቱብን፥ወደ፡ሜዳም፡ወጡብን፤እኛም፡ ወደቅንባቸው፥እስከከተማዪቱም፡በር፡ድረስ፡ተከተልናቸው።

24ፍላጻ፡የሚወረውሩም፡በቅጥሩ፡ላይ፡ኾነው፡በባሪያዎችኽ፡ላይ፡ወረወሩ፤ከንጉሡም፡ባሪያዎች፡አንዳንድ፡ ሞቱ፥ባሪያኽም፡ኬጢያዊው፡ኦርዮ፡ደግሞ፡ሞተ፡አለው።

25ዳዊትም፡መልእክተኛውን፦ሰይፍ፡አንድ፡ጊዜ፡ይህን፡አንድ፡ጊዜም፡ያን፡ያጠፋልና፡ይህ፡ነገር፡ በዐይንኽ፡አይክፋ፤ከተማዪቱን፡የሚወጉትን፡አበርታ፥አፍርሳትም፡ብለኽ፡ለኢዮአብ፡ንገረው፤አንተም፡ አጽናው፡አለው።

26የኦርዮም፡ሚስት፡ባሏ፡ኦርዮ፡እንደ፡ሞተ፡በሰማች፡ጊዜ፥ለባሏ፡አለቀሰች።

27የልቅሶዋም፡ወራት፡ሲፈጸም፡ዳዊት፡ልኮ፡ወደ፡ቤቱ፡አስመጣት፥ሚስትም፡ኾነችው፥ወንድ፡ልጅም፡ ወለደችለት፤ነገር፡ግን፥ዳዊት፡ያደረገው፡ነገር፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡ኾነ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source