Skip to content
← 2 Samuel

Chapter 12 · Amharic

2 Samuel

1እግዚአብሔርም፡ናታንን፡ወደ፡ዳዊት፡ላከ፥ወደ፡ርሱም፡መጥቶ፡አለው፦ባንድ፡ከተማ፡አንዱ፡ባለጠጋ፡ አንዱም፡ድኻ፡የኾኑ፡ኹለት፡ሰዎች፡ነበሩ።

2ባለጠጋውም፡እጅግ፡ብዙ፡በግና፡ላም፡ነበረው።

3ለድኻው፡ግን፡ከገዛት፡አንዲት፡ታናሽ፡በግ፡በቀር፡አንዳች፡አልነበረውም፤አሳደጋትም፥ከልጆቹም፡ጋራ፡ በርሱ፡ዘንድ፡አደገች፤እንጀራውንም፡ትበላ፥ከዋንጫውም፡ትጠጣ፥በብብቱም፡ትተኛ፡ነበር፥እንደ፡ልጁም፡ ነበረች።

4ወደ፡ባለጠጋውም፡እንግዳ፡በመጣ፡ጊዜ፡ከበጉና፡ከላሙ፡ወስዶ፡ለዚያ፡ወደ፡ርሱ፡ለመጣው፡እንግዳ፡ ያዘጋጅለት፡ዘንድ፡ሣሣ፤የዚያንም፡የድኻውን፡ሰው፡በግ፡ወስዶ፡ለዚያ፡ለመጣው፡ሰው፡አዘጋጀ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

5ዳዊትም፡በዚያ፡ሰው፡ላይ፡እጅግ፡ተቈጥቶ፡ናታንን፦ሕያው፡እግዚአብሔርን! ይህን፡ያደረገ፡ሰው፡ የሞት፡ልጅ፡ነው።

6ይህን፡አድርጓልና፥አላዘነምና፡ስለ፡አንዲቱ፡በግ፡አራት፡ይመልስ፡አለው።

7ናታንም፡ዳዊትን፡አለው፦ያ፡ሰው፡አንተ፡ነኽ።የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ ይላል፦በእስራኤል፡ላይ፡ንጉሥ፡ልትኾን፡ቀባኹኽ፥ከሳኦልም፡እጅ፡አዳንኹኽ፤

8የጌታኽንም፡ቤት፡ሰጠኹኽ፥የጌታኽንም፡ሚስቶች፡በብብትኽ፡ጣልኹልኽ፤የእስራኤልንና፡የይሁዳን፡ቤት፡ ሰጠኹኽ፤ይህም፡አንሶ፡ቢኾን፡ኖሮ፡ከዚህ፡የበለጠ፡እጨምርልኽ፡ነበር።

9አኹንስ፡በፊቱ፡ክፉ፡ትሠራ፡ዘንድ፡የእግዚአብሔርን፡ነገር፡ለምን፡አቃለልኽ፧ኬጢያዊውን፡ኦርዮን፡ በሰይፍ፡መትተኻል፥ሚስቱንም፡ለአንተ፡ሚስት፡ትኾን፡ዘንድ፡ወስደኻል፤ርሱንም፡በዐሞን፡ልጆች፡ሰይፍ፡ ገድለኻል።

10ስለዚህም፡አቃለ፟ኸኛልና፥የኬጢያዊውንም፡የኦርዮን፡ሚስት፡ለአንተ፡ሚስት፡ትኾን፡ዘንድ፡ወስደኻልና፡ ለዘለዓለም፡ከቤትኽ፡ሰይፍ፡አይርቅም።

11እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ከቤትኽ፡ክፉ፡ነገር፡አስነሣብኻለኹ፤ሚስቶችኽንም፡በዐይንኽ፡ ፊት፡እወስዳለኹ፥ለዘመድኽም፡እሰጣቸዋለኹ፥በዚችም፡ፀሓይ፡ዐይን፡ፊት፡ከሚስቶችኽ፡ጋራ፡ይተኛል።

12አንተ፡ይህን፡በስውር፡አድርገኸዋል፤እኔ፡ግን፡ይህን፡በእስራኤል፡ዅሉ፡ፊትና፡በፀሓይ፡ፊት፡ አደርገዋለኹ።

13ዳዊትም፡ናታንን፦እግዚአብሔርን፡በድያለኹ፡አለው።ናታንም፡ዳዊትን፦እግዚአብሔር፡ደግሞ፡ ኀጢአትኽን፡አርቆልኻል፤አትሞትም።

14ነገር፡ግን፥በዚህ፡ነገር፡ለእግዚአብሔር፡ጠላቶች፡ታላቅ፡የስድብ፡ምክንያት፡አድርገኻልና፡ስለዚህ፡ ደግሞ፡የተወለደልኽ፡ልጅ፡ፈጽሞ፡ይሞታል፡አለው።

15ናታንም፡ወደ፡ቤቱ፡ተመለሰ።እግዚአብሔርም፡የኦርዮ፡ሚስት፡ለዳዊት፡የወለደችውን፡ሕፃን፡ ቀሠፈ፥እጅግም፡ታሞ፟፡ነበር።

16ዳዊትም፡ስለ፡ሕፃኑ፡እግዚአብሔርን፡ለመነ፤ዳዊትም፡ጾመ፥ገብቶም፡በመሬት፡ላይ፡ተኛ።

17የቤቱም፡ሽማግሌዎች፡ተነሥተው፡ከምድር፡ያነሡት፡ዘንድ፡በአጠገቡ፡ቆሙ፤ርሱ፡ግን፡እንቢ፡ አለ፥ከነርሱም፡ጋራ፡እንጀራ፡አልበላም።

18በሰባተኛውም፡ቀን፡ሕፃኑ፡ሞተ።የዳዊትም፡ባሪያዎች።ሕፃኑ፡በሕይወት፡ሳለ፡ብንነግረው፡ አልሰማንም፤ይልቁንስ፡ሕፃኑ፡እንደ፡ሞተ፡ብንነግረው፡እንዴት፡ይኾን፧በነፍሱ፡ክፉ፡ያደርጋል፡ብለው፡ ሕፃኑ፡እንደ፡ሞተ፡ይነግሩት፡ዘንድ፡ፈሩ።

19ዳዊትም፡ባሪያዎቹ፡በሹክሹክታ፡ሲነጋገሩ፡ባየ፡ጊዜ፡ዳዊት፡ሕፃኑ፡እንደ፡ሞተ፡ዐወቀ፤ዳዊትም፡ ባሪያዎቹን፦ሕፃኑ፡ሞቷል፧አላቸው።እነርሱም፦ሞቷል፡አሉት።

20ዳዊትም፡ከምድር፡ተነሥቶ፡ታጠበ፥ተቀባም፥ልብሱንም፡ለወጠ፤ወደእግዚአብሔርም፡ቤት፡ገብቶ፡ ሰገደ።ወደ፡ቤቱም፡መጣ፦እንጀራ፡አምጡልኝ፡አለ፤በፊቱም፡አቀረቡለት፥በላም።

21ባሪያዎቹም፦ይህ፡ያደረግኸው፡ነገር፡ምንድር፡ነው፧በሕይወት፡ሳለ፡ስለ፡ሕፃኑ፡ጾምኽና፡ አለቀስኽ፤ከሞተ፡በዃላ፡ግን፡ተነሥተኽ፡እንጀራ፡በላኽ፡አሉት።

22ርሱም፦ሕፃኑ፡ሕያው፡ሳለ።እግዚአብሔር፡ይምረኝ፥ሕፃኑም፡በሕይወት፡ይኖር፡እንደ፡ኾነ፡ማን፡ ያውቃል፧ብዬ፡ጾምኹ፡አለቀስኹም።

23አኹን፡ግን፡ሞቷል፤የምጾመው፡ስለ፡ምንድር፡ነው፧በእውኑ፡እንግዲህ፡እመልሰው፡ዘንድ፡ ይቻለኛልን፧እኔ፡ወደ፡ርሱ፡እኼዳለኹ፡እንጂ፡ርሱ፡ወደ፡እኔ፡አይመለስም፡አለ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

24ዳዊትም፡ሚስቱን፡ቤርሳቤሕን፡አጽናናት፥ወደ፡ርሷም፡ገባ፥ከርሷም፡ጋራ፡ተኛ፤ወንድ፡ልጅም፡ ወለደች፥ስሙንም፡ሰሎሞን፡ብሎ፡ጠራው።እግዚአብሔርም፡ወደደው፤

25ደግሞም፡በነቢዩ፡በናታን፡እጅ፡ልኮ፡ስሙን፡ስለ፡እግዚአብሔር፡ይዲድያ፡ብሎ፡ጠራው።

26ኢዮአብም፡የዐሞንን፡ልጆች፡ከተማ፡ረባትን፡ወጋ፥የውሃውንም፡ከተማ፡ያዘ።

27ኢዮአብም፡ወደ፡ዳዊት፦ረባትን፡ወግቻለኹ፥የውሃውንም፡ከተማ፡ይዣለኹ።

28አኹንም፡ከተማዪቱን፡እንዳልይዝ፥በስሜም፡እንዳትጠራ፥የቀረውን፡ሕዝብ፡ሰብስብ፥ከተማዪቱንም፡ ከበ፟ኽ፡ያዝ፡ብሎ፡መልእክተኛዎችን፡ላከ።

29ዳዊትም፡ሕዝቡን፡ዅሉ፡ሰብስቦ፡ወደ፡ረባት፡ኼደ፥ወግቶም፡ያዛት።

30የንጉሣቸውንም፡ዘውድ፡ከራሱ፡ላይ፡ወሰደ።ክብደቱም፡አንድ፡መክሊት፡ወርቅ፡ያኽል፡ነበር፥ክቡር፡ ዕንቍም፡ነበረበት፤ዳዊትም፡በራሱ፡ላይ፡አደረገው።ከከተማዪቱም፡እጅግ፡ብዙ፡ምርኮ፡አወጣ።

31በውስጧም፡የነበሩትን፡ሕዝብ፡አውጥቶ፡በመጋዝና፡በብረት፡መቈፈሪያና፡በብረት፡መጥረቢያ፡እንዲሠሩ፡ አደረጋቸው፤የሸክላ፡ጡብም፡እንዲያቃጥሉ፡አደረጋቸው፤በዐሞን፡ልጆች፡ከተማዎች፡ዅሉ፡እንዲህ፡ አደረገ።ዳዊትም፡ሕዝቡም፡ዅሉ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ተመለሱ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source