1ዳዊትም፦ስለ፡ዮናታን፡ቸርነት፡አደርግለት፡ዘንድ፡ከሳኦል፡ቤት፡አንድ፡ሰው፡ቀርቷልን፧አለ።
2ከሳኦልም፡ቤት፡ሲባ፡የሚባል፡አንድ፡ባሪያ፡ነበረ፥ወደ፡ዳዊትም፡ጠሩት፤ንጉሡም፦አንተ፡ሲባ፡ ነኽን፧አለው።ርሱም፦እኔ፡ባሪያኽ፡ነኝ፡አለ።
3ንጉሡም፦የእግዚአብሔርን፡ቸርነት፡አደርግለት፡ዘንድ፡ከሳኦል፡ቤት፡አንድ፡ሰው፡ አልቀረምን፧አለ።ሲባም፡ንጉሡን፦እግሩ፡ሽባ፡የኾነ፡አንድ፡የዮናታን፡ልጅ፡አለ፡አለው።
4ንጉሡም፦ወዴት፡ነው፧አለው፤ሲባም፡ንጉሡን፦እንሆ፥ርሱ፡በሎዶባር፡በዓሚኤል፡ልጅ፡በማኪር፡ ቤት፡አለ፡አለው።
5ንጉሡም፡ዳዊት፡ልኮ፡ከሎዶባር፡ከዓሚኤል፡ልጅ፡ከማኪር፡ቤት፡አስመጣው።
6የሳኦልም፡ልጅ፡የዮናታን፡ልጅ፡ሜምፊቦስቴ፡ወደ፡ዳዊት፡መጣ፥በግንባሩም፡ወድቆ፡እጅ፡ ነሣ፤ዳዊትም፦ሜምፊቦስቴ፡ሆይ፥አለ፤ርሱም፦እንሆኝ፡ባሪያኽ፡አለ።
7ዳዊትም፦ስለ፡አባትኽ፡ስለ፡ዮናታን፡ቸርነት፡ፈጽሜ፡አደርግልኻለኹና፡አትፍራ፤የአባትኽንም፡የሳኦልን፡ 151 ዕብ.፥የሆሻፋጥ፡(አምላክ፡ፈረደለት)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ምድር፡ዅሉ፡እመልስልኻለኹ፥አንተም፡ዅልጊዜ፡ከገበታዬ፡እንጀራ፡ትበላለኽ፡አለው።
8ርሱም፦የሞተ፡ውሻ፡ወደምመስል፡ወደ፡እኔ፡የተመለከትኽ፥እኔ፡ባሪያኽ፡ምንድር፡ነኝ፧ብሎ፡እጅ፡ ነሣ።
9ንጉሡም፡የሳኦልን፡ባሪያ፣ሲባን፡ጠርቶ፦ለሳኦልና፡ለቤቱ፡ዅሉ፡የነበረውን፡ዅሉ፡ለጌታኽ፡ልጅ፡ ሰጥቻለኹ።
10አንተና፡ልጆችኽ፡ሎሌዎችኽም፡ምድሩን፡ዕረሱለት፤ለጌታኽም፡ልጅ፡እንጀራ፡ይኾነው፡ዘንድ፡ፍሬውን፡ አግባ፤የጌታኽ፡ልጅ፡ሜምፊቦስቴ፡ግን፡ዅልጊዜ፡ከገበታዬ፡ይበላል፡አለው።ለሲባም፡ዐሥራ፡ዐምስት፡ ልጆችና፡ኻያ፡ባሪያዎች፡ነበሩት።
11ሲባም፡ንጉሡን፦ጌታዬ፡ንጉሡ፡ባሪያውን፡እንዳዘዘ፡እንዲሁ፡ባሪያኽ፡ያደርጋል፡አለው።ሜምፊቦስቴም፡ ከንጉሡ፡ልጆች፡እንደ፡አንዱ፡ከዳዊት፡ገበታ፡ይበላ፡ነበር።
12ለሜምፊቦስቴም፡ሚካ፡የተባለ፡ታናሽ፡ልጅ፡ነበረው።በሲባም፡ቤት፡ያሉ፡ዅሉ፡ለሜምፊቦስቴ፡ያገለግሉ፡ ነበር።
13ሜምፊቦስቴም፡ከንጉሥ፡ገበታ፡ዅልጊዜ፡እየበላ፡በኢየሩሳሌም፡ተቀምጦ፡ነበር፤ኹለት፡እግሩም፡ሽባ፡ ነበረ።