1ከዚህም፡በዃላ፡ዳዊት፡ፍልስጥኤማውያንን፡መታ፥አዋረዳቸውም፤ከፍልስጥኤማውያንም፡እጅ፡ሜቴግ፡ አማ፡የተባለችውን፡ከተማ፡ወሰደ።
2ሞዐብን፡መታ፥ሞዐባውያንንም፡በምድር፡ጥሎ፡በገመድ፡ሰፈራቸው፤በኹለትም፡ገመድ፡ ለሞት፥በአንድም፡ገመድ፡ሙሉ፡ለሕይወት፡ሰፈራቸው፤ሞዐባውያንም፡ለዳዊት፡ገባሮች፡ኾኑ፥ግብርም፡ አመጡለት።
3ዳዊትም፡ደግሞ፡በኤፍራጥስ፡ወንዝ፡አጠገብ፡የነበረውን፡ግዛት፡መልሶ፡ለመያዝ፡በኼደ፡ጊዜ፡የረአብን፡ ልጅ፡የሱባን፡ንጉሥ፡አድርዐዛርን፡መታ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
4ዳዊትም፡ከርሱ፡ሺሕ፡ሰባት፡መቶ፡ፈረሰኛዎች፥ኻያ፡ሺሕም፡እግረኛዎች፡ያዘ፤ዳዊትም፡የሠረገለኛውን፡ ፈረስ፡ዅሉ፡ቋንዣ፡ቈረጠ፤ለመቶ፡ሠረገላ፡ብቻ፡አስቀረ።
5ከደማስቆም፡ሶርያውያን፡የሱባን፡ንጉሥ፡አድርዐዛርን፡ሊረዱ፡በመጡ፡ጊዜ፡ዳዊት፡ከሶርያውያን፡ኻያ፡ ኹለት፡ሺሕ፡ሰዎች፡ገደለ።
6ዳዊትም፡በደማስቆ፡ሶርያ፡ጭፍራዎች፡አኖረ፥ሶርያውያንም፡ለዳዊት፡ገባሮች፡ኾኑ፥ግብርም፡ አመጡለት፤እግዚአብሔርም፡ዳዊት፡በኼደበት፡ዅሉ፡ድልን፡ሰጠው።
7ዳዊትም፡ለአድርዐዛር፡ባሪያዎች፡የነበሩትን፡የወርቅ፡ጋሻዎች፡ወሰደ፥ወደ፡ኢየሩሳሌምም፡ይዟቸው፡መጣ።
8ንጉሡም፡ዳዊት፡ከአድርዐዛር፡ከተማዎች፡ከቤጣሕና፡ከቤሮታይ፡እጅግ፡ብዙ፡ናስ፡ወሰደ።
9የሐማትም፡ንጉሥ፡ቶዑ፡ዳዊት፡የአድርዐዛርን፡ጭፍራ፡ዅሉ፡እንደ፡መታ፡ሰማ።
10ቶዑም፡ከአድርዐዛር፡ጋራ፡ዅልጊዜ፡ይዋጋ፡ነበርና፥ዳዊት፡አድርዐዛርን፡ድል፡ስለ፡መታ፡ቶዑ፡ልጁን፡ አዶራምን፡ደኅንነቱን፡ይጠይቅ፡ዘንድ፥ይመርቀውም፡ዘንድ፡ወደ፡ንጉሥ፡ዳዊት፡ላከው፤ርሱም፡የብርና፡ የወርቅ፡የናስም፡ዕቃ፡ይዞ፡መጣ።
12ንጉሥ፡ዳዊትም፡ካሸነፋቸው፡ከአሕዛብ፡ዅሉ፡ከሶርያ፡ከሞዐብም፡ከዐሞንም፡ልጆች፡ ከፍልስጥኤማውያንም፡ከዐማሌቅም፡ከረአብም፡ልጅ፡ከሱባ፡ንጉሥ፡ከአድርዐዛር፡ምርኮ፡ከቀደሰው፡ብርና፡ ወርቅ፡ጋራ፡እነዚህን፡ደግሞ፡ለእግዚአብሔር፡ቀደሰ።
13ዳዊትም፡በተመለሰ፡ጊዜ፡ከኤዶምያስ፡ዐሥራ፡ስምንት፡ሺሕ፡ሰዎች፡በጨው፡ሸለቆ፡ውስጥ፡በመምታቱ፡ ስሙ፡ተጠራ።
14በኤዶምያስ፡ዅሉ፡ጭፍራዎች፡አኖረ፥ኤዶማውያንም፡ዅሉ፡ለዳዊት፡ገባሮች፡ኾኑ፤እግዚአብሔርም፡ ዳዊት፡በሚኼድበት፡ዅሉ፡ድልን፡ሰጠው።
15ዳዊትም፡በእስራኤል፡ዅሉ፡ላይ፡ነገሠ፤ዳዊትም፡ለሕዝቡ፡ዅሉ፡ፍርድንና፡ጽድቅን፡አደረገላቸው።
16የጽሩያ፡ልጅ፡ኢዮአብም፡የሰራዊት፡አለቃ፡ነበረ፤የአኂሉድም፡ልጅ፡ኢዮሳፍጥ ፡ታሪክ፡ጸሓፊ፡ነበረ፤
17የአኪጦብም፡ልጅ፡ሳዶቅ፥የአቢሜሌክም፡ልጅ፡አብያታር፡ካህናት፡ነበሩ፤ሰራያም፡ጸሓፊ፡ነበረ፤
18የዮዳዔ፡ልጅ፡በናያስ፡በከሊታውያንና፡በፈሊታውያን፡ላይ፡ነበረ፤የዳዊትም፡ልጆች፡አማካሪዎች፡ነበሩ።