Skip to content
← 2 Samuel

Chapter 7 · Amharic

2 Samuel

1እንዲህም፡ኾነ፤ንጉሡ፡በቤቱ፡በተቀመጠ፡ጊዜ፡እግዚአብሔርም፡በዙሪያው፡ካሉት፡ጠላቶቹ፡ዅሉ፡ ባሳረፈው፡ጊዜ፥

2ንጉሡ፡ነቢዩን፡ናታንን፦እኔ፡ከዝግባ፡በተሠራ፡ቤት፡ተቀምጫለኹ፥የእግዚአብሔር፡ታቦት፡ግን፡ በመጋረጃዎች፡ውስጥ፡እንደ፡ተቀመጠ፡እይ፡አለው።

3ናታንም፡ንጉሡን፦እግዚአብሔር፡ከአንተ፡ጋራ፡ነውና፥ኺድ፥በልብኽም፡ያለውን፡ዅሉ፡አድርግ፡ አለው።

4በዚያም፡ሌሊት፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡ናታን፡መጣ፥እንዲህም፡አለው፦

6ኺድ፥ለባሪያዬ፡ለዳዊት፡ንገረው፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የእስራኤልን፡ልጆች፡ከግብጽ፡ ምድር፡ካወጣኹበት፡ቀን፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡በድንኳንና፡በማደሪያ፡እኼድ፡ነበር፡እንጂ፡በቤት፡ አልተቀመጥኹምና፡አንተ፡የምኖርበትን፡ቤት፡አትሠራልኝም።

7ከእስራኤል፡ልጆች፡ዅሉ፡ጋራ፡ባለፍኹበት፡ስፍራ፡ዅሉ፦ስለ፡ምን፡ቤትን፡ከዝግባ፡ዕንጨት፡ አልሠራችኹልኝም፧ብዬ፡ሕዝቤን፡እስራኤልን፡ይጠብቅ፡ዘንድ፡ከእስራኤል፡ነገድ፡ላዘዝኹት፡ለአንዱ፡ በእውኑ፡ተናግሬያለኹን፧

8አኹንም፡ዳዊትን፡ባሪያዬን፡እንዲህ፡በለው፦የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦አንተ፡ መንጋውን፡ስትከተል፡በሕዝቤ፡በእስራኤል፡ላይ፡አለቃ፡ትኾን፡ዘንድ፡ከበግ፡ጥበቃ፡ወሰድኹኽ፤

9በኼድኽበትም፡ዅሉ፡ከአንተ፡ጋራ፡ነበርኹ፥ጠላቶችኽንም፡ዅሉ፡ከፊትኽ፡አጠፋኹ፤በምድርም፡ላይ፡ እንዳሉ፡እንደ፡ታላላቆቹ፡ስም፡ታላቅ፡ስም፡አደርግልኻለኹ።

11ለሕዝቤም፡ለእስራኤል፡ስፍራ፡አደርግለታለኹ፥እተክለውማለኹ፤በስፍራውም፡ይቀመጣል፥ከዚያም፡ በዃላ፡አይናወጥ፤እንደ፡ቀድሞው፡ዘመንና፡በሕዝቤ፡በእስራኤል፡ላይ፡ፈራጆች፡እንዳስነሣኹበት፡ጊዜ፡ ግፈኛዎች፡ተመልሰው፡አያስጨንቁትም፤ከጠላቶችኽም፡አሳርፍኻለኹ።እግዚአብሔርም፡ደግሞ፦ቤት፡ እሠራልኻለኹ፡ብሎ፡ይነግርኻል።

12ዕድሜኽም፡በተፈጸመ፡ጊዜ፡ከአባቶችኽም፡ጋራ፡ባንቀላፋኽ፡ጊዜ፥ከወገብኽ፡የሚወጣውን፡ዘርኽን፡ ከአንተ፡በዃላ፡አስነሣለኹ፥መንግሥቱንም፡አጸናለኹ።

13ርሱ፡ለስሜ፡ቤት፡ይሠራል፤የመንግሥቱንም፡ዙፋን፡ለዘለዓለም፡አጸናለኹ።

14እኔም፡አባት፡እኾነዋለኹ፥ርሱም፡ልጅ፡ይኾነኛል፤ክፉ፡ነገርም፡ቢያደርግ፥ሰው፡በሚቀጣበት፡በትርና፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org በሰው፡ልጆች፡መቀጫ፡እገሥጸዋለኹ፤

15ከፊቴም፡ከጣልኹት፡ከሳኦል፡እንዳራቅኹ፡ምሕረቴን፡ከርሱ፡አላርቅም።

16ቤትኽና፡መንግሥትኽም፡በፊቴ፡ለዘለዓለም፡ይጠነክራል፥ዙፋንኽም፡ለዘለዓለም፡ይጸናል።

17እንደዚህ፡ቃል፡ዅሉ፡እንደዚህም፡ራእይ፡ዅሉ፡ናታን፡ለዳዊት፡ነገረው።

18ንጉሡ፡ዳዊትም፡ገባ፥በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ተቀምጦ፡እንዲህ፡አለ፦ጌታዬ፡እግዚአብሔር፡ ሆይ፥እስከዚህ፡ያደረስኸኝ፡እኔ፡ማን፡ነኝ፧

19ቤቴስ፡ምንድር፡ነው፧ጌታዬ፡እግዚአብሔር፡ሆይ፥ይህ፡በፊትኽ፡ጥቂት፡ነበረ፤ስለ፡ባሪያኽም፡ቤት፡ ደግሞ፡ለሩቅ፡ዘመን፡ተናገርኽ፤ጌታዬ፡እግዚአብሔር፡ሆይ፥ይህ፡የሰው፡ሕግ፡ነው።

20ጌታዬ፡እግዚአብሔር፡ሆይ፥አንተ፡ባሪያኽን፡ታውቃለኽና፡ዳዊትስ፡ይናገርኽ፡ዘንድ፡የሚጨምረው፡ ምንድር፡ነው፧

21ለባሪያኽም፡ታስታውቀው፡ዘንድ፡ስለ፡ቃልኽ፡ምክንያትና፡እንደ፡ልብኽ፡ዐሳብ፡ይህን፡ታላቅ፡ነገር፡ ዅሉ፡አደረግኽ።

22ስለዚህም፥አቤቱ፡አምላኬ፡ሆይ፥እንደ፡አንተ፡ያለ፡የለምና፥በዦሯችንም፡እንደ፡ሰማን፡ዅሉ፡ከአንተ፡ በቀር፡አምላክ፡የለምና፡አንተ፡ታላቅ፡ነኽ።

23ለርሱ፡ለራሱ፡እንዲኾን፡ሕዝብን፡ይቤዥ፡ዘንድ፡ለርሱ፡ለራሱም፡ስም፡ያደርግ፡ዘንድ፥በአሕዛብና፡ በአምላኮቻቸውም፡ፊት፡ከግብጽ፡በተቤዠው፡ሕዝብ፡ፊት፡ተኣምራትንና፡ድንቅን፡ያደርግ፡ዘንድ፡ እግዚአብሔር፡እንደ፡ኼደለት፡እንደ፡ሕዝብኽ፡እንደ፡እስራኤል፡ያለ፡በምድር፡ላይ፡ምን፡ሕዝብ፡አለ፧

24ሕዝብኽንም፡እስራኤልን፡ለዘለዓለም፡ሕዝብ፡አድርገኽ፡አጽንተኸዋል፤አንተም፥አቤቱ፥አምላክ፡ ኾነኻቸዋል።

25አቤቱ፡አምላክ፡ሆይ፥አኹንም፡ለባሪያኽና፡ለቤቱ፡የተናገርኸውን፡ለዘለዓለም፡አጽናው፥እንደ፡ ተናገርኽም፡አድርግ።

26የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡የእስራኤል፡አምላክ፡ነው፡ይባል፡ዘንድ፡ስምኽ፡ለዘለዓለም፡ታላቅ፡ ይኹን፤የባሪያኽም፡የዳዊት፡ቤት፡በፊትኽ፡የጸና፡ይኹን።

27አቤቱ፡የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡ሆይ፥አንተ፦እኔ፡ቤት፡እሠራልኻለኹ፡ብለኽ፡ለባሪያኽ፡ ገልጠኻልና፥ስለዚህ፡ባሪያኽ፡ይህችን፡ጸሎት፡ወዳንተ፡ይጸልይ፡ዘንድ፡በልቡ፡ደፈረ።

28ጌታዬ፡እግዚአብሔር፡ሆይ፥አኹንም፡አንተ፡አምላክ፡ነኽ፥ቃልኽም፡እውነት፡ነው፥ይህንም፡መልካም፡ ነገር፡ለባሪያኽ፡ተናግረኻል።

29ጌታዬ፡እግዚአብሔር፡ሆይ፥አንተ፡ተናግረኻልና፥አኹን፡እንግዲህ፡ለዘለዓለም፡በፊትኽ፡ይኾን፡ዘንድ፡ የባሪያኽን፡ቤት፥እባክኽ፥ባርክ፤በበረከትኽም፡የባሪያኽ፡ቤት፡ለዘለዓለም፡ይባረክ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source