Skip to content
← 2 Samuel

Chapter 6 · Amharic

2 Samuel

1ዳዊትም፡ዳግም፡ከእስራኤል፡የተመረጡትን፡ሠላሳ፡ሺሕ፡ያኽል፡ሰው፡ሰበሰበ።

2ዳዊትና፡ከርሱ፡ጋራ፡የነበሩት፡ሕዝብ፡ዅሉ፡በይሁዳ፡ካለች፡ከበዓል፡ተነሥተው፡በኪሩቤል፡ላይ፡ በተቀመጠ፡በሰራዊት፡ጌታ፡በእግዚአብሔር፡ስም፡የተጠራውን፡የእግዚአብሔርን፡ታቦት፡ከዚያ፡ያመጡ፡ዘንድ፡ ኼዱ።

3የእግዚአብሔርንም፡ታቦት፡በዐዲስ፡ሠረገላ፡ላይ፡ጫኑ፥በኰረብታውም፡ላይ፡ከነበረው፡ከዐሚናዳብ፡ቤት፡ አመጡት፤የዐሚናዳብ፡ልጆችም፡ዖዛ፡እና፡አኂዮ፡ዐዲሱን፡ሠረገላ፡ይነዱ፡ነበር።

4በኰረብታውም፡ላይ፡ከነበረው፡ከዐሚናዳብ፡ቤት፡የእግዚአብሔርን፡ታቦት፡ባመጡ፡ጊዜ፡አኂዮ፡በታቦቱ፡ ፊት፡ይኼድ፡ነበር።

5ዳዊትና፡የእስራኤልም፡ቤት፡ዅሉ፡በቅኔና፡በበገና፡በመሰንቆም፡በከበሮም፡በነጋሪትና፡በጸናጽል፡ በእግዚአብሔር፡ፊት፡በሙሉ፡ኀይላቸው፡ይጫወቱ፡ነበር።

6ወደናኮንም፡ዐውድማ፡በደረሱ፡ጊዜ፡በሬዎቹ፡ይፋንኑ፡ነበርና፥ዖዛ፡እጁን፡ዘርግቶ፡የእግዚአብሔርን፡ ታቦት፡ያዘ።

7የእግዚአብሔርም፡ቍጣ፡በዖዛ፡ላይ፡ነደደ፥እግዚአብሔርም፡ስለ፡ድፍረቱ፡በዚያው፡ ቀሠፈው፤በእግዚአብሔርም፡ታቦት፡አጠገብ፡በዚያው፡ሞተ።

8እግዚአብሔርም፡ዖዛን፡ስለ፡ሰበረው፡ዳዊት፡ዐዘነ፤እስከ፡ዛሬም፡ድረስ፡የዚያ፡ስፍራ፡ስም፡የዖዛ፡ ስብራት፡ተብሎ፡ተጠራ።

9በዚያም፡ቀን፡ዳዊት፡እግዚአብሔርን፡ፈራና፦የእግዚአብሔር፡ታቦት፡ወደ፡እኔ፡እንዴት፡ይመጣል፧አለ።

10ዳዊትም፡የእግዚአብሔርን፡ታቦት፡ወደ፡ርሱ፡ወደዳዊት፡ከተማ፡ያመጣው፡ዘንድ፡አልወደደም፤ዳዊትም፡ በጌት፡ሰው፡በዐቢዳራ ፡ቤት፡አገባው።

11የእግዚአብሔርም፡ታቦት፡በጌት፡ሰው፡በአቢዳራ፡ቤት፡ሦስት፡ወር፡ያኽል፡ተቀመጠ፤እግዚአብሔርም፡ አቢዳራንና፡ቤቱን፡ዅሉ፡ባረከ።

12ንጉሡ፡ዳዊትም፡እግዚአብሔር፡የአቢዳራን፡ቤትና፡የነበረውን፡ዅሉ፡ስለእግዚአብሔር፡ታቦት፡እንደ፡ ባረከ፡ሰማ።ዳዊትም፡ኼዶ፡የእግዚአብሔርን፡ታቦት፡ከአቢዳራ፡ቤት፡ወደዳዊት፡ከተማ፡በደስታ፡አመጣው።

13የእግዚአብሔርንም፡ታቦት፡የተሸከሙ፡ስድስት፡ርምጃ፡በኼዱ፡ጊዜ፡አንድ፡በሬና፡አንድ፡ፍሪዳ፡ሠዋ።

14ዳዊትም፡በሙሉ፡ኀይሉ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ይዘፍን፡ነበር፤ዳዊትም፡የበፍታ፡ኤፉድ፡ለብሶ፡ነበር።

15ዳዊትና፡የእስራኤልም፡ቤት፡ዅሉ፡ሆ፡እያሉ፡ቀንደ፡መለከትም፡እየነፉ፡የእግዚአብሔርን፡ታቦት፡ አመጡ።

16የእግዚአብሔርም፡ታቦት፡ወደዳዊት፡ከተማ፡በገባ፡ጊዜ፡የሳኦል፡ልጅ፡ሜልኮል፡በመስኮት፡ኾና፡ ተመለከተች፥ንጉሡም፡ዳዊት፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ሲዘል፟ና፡ሲዘፍን፡አየች፤በልቧም፡ናቀችው።

17የእግዚአብሔርንም፡ታቦት፡አገቡ፥ዳዊትም፡በተከለለት፡ድንኳን፡ውስጥ፡በስፍራው፡አኖሩት፤ዳዊትም፡ የሚቃጠልና፡የደኅንነት፡መሥዋዕትን፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡አሳረገ።

18ዳዊትም፡የሚቃጠልና፡የደኅንነት፡መሥዋዕት፡ማሳረግ፡ከፈጸመ፡በዃላ፡ሕዝቡን፡በሰራዊት፡ጌታ፡ በእግዚአብሔር፡ስም፡መረቀ። 150 ዕብ.፥ዖበድ፡ኤዶም፡(የኤዶም፡አገልጋይ)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

19ለሕዝቡም፡ዅሉ፡ለእስራኤል፡ወገን፡ለወንዱም፡ለሴቱም፡ለያንዳንዱ፡አንዳንድ፡እንጀራ፡አንዳንድም፡ የሥጋ፡ቍራጭ፡አንዳንድም፡የዘቢብ፡ጥፍጥፍ፡አከፋፈለ።ሕዝቡም፡ዅሉ፡እያንዳንዱ፡ወደ፡ቤቱ፡ኼደ።

20ዳዊትም፡ቤተ፡ሰቡን፡ሊመርቅ፡ተመለሰ።የሳኦልም፡ልጅ፡ሜልኮል፡ዳዊትን፡ለመቀበል፡ ወጣችና።ምናምንቴዎች፡ዕርቃናቸውን፡እንደሚገልጡ፡የእስራኤል፡ንጉሥ፡በባሪያዎቹ፡ቈነዣዥት፡ፊት፡ ዕርቃኑን፡በመግለጡ፡ምንኛ፡የተከበረ፡ነው! አለችው።

21ዳዊትም፡ሜልኮልን፦በእግዚአብሔር፡ፊት፡ዘፍኛለኹ፤በእግዚአብሔር፡ሕዝብ፡በእስራኤል፡ላይ፡አለቃ፡ እኾን፡ዘንድ፡ከአባትሽና፡ከቤቱ፡ዅሉ፡ይልቅ፡የመረጠኝ፡እግዚአብሔር፡የተባረከ፡ይኹን፡ስለዚህም፡ በእግዚአብሔር፡ፊት፡እጫወታለኹ።

22አኹንም፡ከኾንኹት፡ይልቅ፡የተናቅኹ፡እኾናለኹ፥በዐይንሽም፡እዋረዳለኹ፤ነገር፡ግን፥በተናገርሽው፡ ቈነዣዥት፡ዘንድ፡እከብራለኹ፡አላት።

23የሳኦልም፡ልጅ፡ሜልኮል፡እስከሞተችበት፡ቀን፡ድረስ፡ልጅ፡አልወለደችም።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source