Skip to content
← 2 Samuel

Chapter 5 · Amharic

2 Samuel

1የእስራኤልም፡ነገድ፡ዅሉ፡ወደ፡ኬብሮን፡ወደ፡ዳዊት፡መጥተው፦እንሆ፥እኛ፡የዐጥንትኽ፡ፍላጭ፡ የሥጋኽ፡ቍራጭ፡ነን።

2አስቀድሞ፡ሳኦል፡በእኛ፡ላይ፡ንጉሥ፡ኾኖ፡ሳለ፡እስራኤልን፡የምታወጣና፡የምታገባ፡አንተ፡ ነበርኽ፤እግዚአብሔርም፦አንተ፡ሕዝቤን፡እስራኤልን፡ትጠብቃለኽ፥በእስራኤልም፡ላይ፡አለቃ፡ትኾናለኽ፡ ብሎኽ፡ነበር፡አሉት።

3የእስራኤልም፡ሽማግሌዎች፡ዅሉ፡ወደ፡ንጉሡ፡ወደ፡ኬብሮን፡መጡ፤ንጉሡ፡ዳዊትም፡በኬብሮን፡ በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቃል፡ኪዳን፡ከነርሱ፡ጋራ፡አደረገ፤በእስራኤልም፡ንጉሥ፡ይኾን፡ዘንድ፡ዳዊትን፡ቀቡት። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

4ዳዊትም፡መንገሥ፡በዠመረ፡ጊዜ፡የሠላሳ፡ዓመት፡ልጅ፡ነበረ፥አርባ፡ዓመትም፡ነገሠ።

5በኬብሮን፡በይሁዳ፡ላይ፡ሰባት፡ዓመት፡ከስድስት፡ወር፡ነገሠ፤በኢየሩሳሌምም፡በእስራኤል፡ዅሉና፡ በይሁዳ፡ላይ፡ሠላሳ፡ሦስት፡ዓመት፡ነገሠ።

6ንጉሡና፡ሰዎቹም፡በአገሩ፡ውስጥ፡ከተቀመጡት፡ከኢያቡሳውያን፡ጋራ፡ለመዋጋት፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ ኼዱ፤እነርሱም፦ዳዊት፡ወደዚህ፡ሊገባ፡አይችልም፡ብለው፡ዐስበው፡ነበርና፥ዳዊትን፦ዕውሮችንና፡ ዐንካሳዎችን፡ካላወጣኽ፡በቀር፡ወደዚህ፡አትገባም፡አሉት።

7ነገር፡ግን፥ዳዊት፡ዐምባዪቱን፡ጽዮንን፡ያዘ፥ርሷም፡የዳዊት፡ከተማ፡ናት።

8በዚያም፡ቀን፡ዳዊት፦ኢያቡሳውያንን፡የሚመታ፡በውሃ፡መኼጃው፡ይውጣ፤የዳዊትም፡ነፍስ፡ የምትጠላቸውን፡ዕውሮችንና፡ዐንካሳዎችን፡ያውጣ፡አለ።ስለዚህም፡በምሳሌ፦ዕውርና፡ዐንካሳ፡ወደ፡ቤት፡ አይግቡ፡ተባለ።

9ዳዊትም፡በዐምባዪቱ፡ውስጥ፡ተቀመጠ፥የዳዊትም፡ከተማ፡ብሎ፡ጠራት።ዳዊትም፡ዙሪያዋን፡ከሚሎ፡ ዠምሮ፡ወደ፡ውስጥ፡ቀጠራት።

10ዳዊትም፡እየበረታ፡ኼደ፤የሰራዊት፡አምላክ፡እግዚአብሔርም፡ከርሱ፡ጋራ፡ነበረ።

11የጢሮስም፡ንጉሥ፡ኪራም፡ወደ፡ዳዊት፡መልእክተኛዎችን፡የዝግባ፡ዕንጨትንም፡ዐናጢዎችንም፡ ጠራቢዎችንም፡ላከ፤ለዳዊትም፡ቤት፡ሠሩለት።

12ዳዊትም፡እግዚአብሔር፡በእስራኤል፡ላይ፡ንጉሥ፡አድርጎ፡እንዳጸናው፥ስለ፡ሕዝቡ፡ስለ፡እስራኤልም፡ መንግሥቱን፡ከፍ፡እንዳደረገ፡ዐወቀ።

13ዳዊትም፡ከኬብሮን፡ከመጣ፡በዃላ፡ሌላዎቹን፡ቁባቶቹንና፡ሚስቶቹን፡ከኢየሩሳሌም፡ወሰደ፤ለዳዊትም፡ ደግሞ፡ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆች፡ተወለዱለት።

14በኢየሩሳሌምም፡የተወለዱለት፡ስማቸው፡ይህ፡ነው፤ሳሙስ፥

15ሶባብ፥ናታን፥ሰሎሞን ፥ኢያቤሐር፥ኤሊሱዔ፥

16ናፌቅ፥ያፍያ፥ኤሊሳማ፥ኤሊዳሄ፥ኤሊፋላት።

17ፍልስጥኤማውያንም፡ዳዊት፡በእስራኤል፡ላይ፡ንጉሥ፡ኾኖ፡እንደ፡ተቀባ፡ሰሙ፥ፍልስጥኤማውያንም፡ ዅሉ፡ዳዊትን፡ሊፈልጉ፡ወጡ፤ዳዊትም፡በሰማ፡ጊዜ፡ወደ፡ምሽጉ፡ወረደ።

18ፍልስጥኤማውያንም፡መጥተው፡በራፋይም፡ሸለቆ፡ተበትነው፡ሰፈሩ።

19ዳዊትም፦ወደ፡ፍልስጥኤማውያን፡ልውጣን፧በእጄስ፡አሳልፈኽ፡ትሰጣቸዋለኽን፧ብሎ፡እግዚአብሔርን፡ ጠየቀ።እግዚአብሔርም፡ዳዊትን፦ፍልስጥኤማውያንን፡በርግጥ፡በእጅኽ፡አሳልፌ፡እሰጣቸዋለኹና፡ውጣ፡ አለው።

20ዳዊትም፡ወደ፡በዓልፐራሲም፡መጣ፥በዚያም፡መታቸውና፦ውሃ፡እንዲያፈርስ፡እግዚአብሔር፡ጠላቶቼን፡ በፊቴ፡አፈረሳቸው፡አለ።ስለዚህም፡የዚያን፡ስፍራ፡ስም፡በዓልፐራሲም፡ብሎ፡ጠራው።

21ጣዖቶቻቸውንም፡በዚያ፡ተዉ፥ዳዊትና፡ሰዎቹም፡ወሰዷቸው።

22ፍልስጥኤማውያንም፡ደግሞ፡መጡ፥በራፋይምም፡ሸለቆ፡ተበትነው፡ሰፈሩ።

23ዳዊትም፡እግዚአብሔርን፡ጠየቀ፤ርሱም፦በዃላቸው፡ዞረኽ፡በሾላው፡ዛፍ፡ፊት፡ለፊት፡ግጠማቸው፡ እንጂ፡አትውጣ።

24በሾላውም፡ዛፍ፡ራስ፡ውስጥ፡የሽውሽውታ፡ድምፅ፡ስትሰማ፥በዚያን፡ጊዜ፡እግዚአብሔር፡ የፍልስጥኤማውያንን፡ጭፍራ፡ለመምታት፡በፊትኽ፡ወጥቶ፡ይኾናልና፥በዚያን፡ጊዜ፡ቸኵል፡አለው። 149 ዕብ.፥ሸሎሞህ፡(ሰላማዊ)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

25ዳዊትም፡እግዚአብሔር፡እንዳዘዘው፡አደረገ፤ከገባዖንም፡እስከ፡ጌዝር፡ድረስ፡ፍልስጥኤማውያንን፡መታ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source