Skip to content
← 2 Samuel

Chapter 17 · Amharic

2 Samuel

1አኪጦፌልም፡አቤሴሎምን፦ዐሥራ፡ኹለት፡ሺሕ፡ሰዎች፡ልምረጥና፡ አኪጦፌልም፡በዚች፡ሌሊት፡ተነሥቼ፡ዳዊትን፡ላሳድ፟።

2ደክሞና፡እጁ፡ዝሎ፡ሳለ፡እወድቅበታለኹ፥አስፈራውማለኹ፤ከርሱም፡ጋራ፡ያለው፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ ይሸሻል፥ንጉሡንም፡ብቻውን፡እመታዋለኹ፤

3ሙሽራ፡ወደ፡ባሏ፡እንደምትመለስ፡ሕዝቡን፡ዅሉ፡ወዳንተ፡እመልሰዋለኹ፤ሕዝቡ፡ዅሉ፡ደኅና፡ ይኾናል፤የምትፈልገው፡አንድ፡ሰው፡ብቻ፡ነው።

4ነገሩም፡አቤሴሎምንና፡የእስራኤልን፡ሽማግሌዎች፡ዅሉ፡ደስ፡አሠኘ።

5አቤሴሎምም፦አርካዊውን፡ኩሲን፡ጥሩ፥ደግሞም፡ርሱ፡የሚለውን፡እንስማ፡አለ።

6ኩሲም፡ወደ፡አቤሴሎም፡በመጣ፡ጊዜ፡አቤሴሎም፦አኪጦፌል፡ያለው፡ይህ፡ነው፤ነገሩን፡እናደርገው፡ ዘንድ፡ይገ፟ባ፟ልን፧ባይኾን፡ግን፡አንተ፡ንገረን፡ብሎ፡ተናገረው።

7ኩሲም፡አቤሴሎምን፦አኪጦፌል፡በዚህ፡ጊዜ፡የመከራት፡ምክር፡መልካም፡አይደለችም፡አለው።

8ኩሲ፡ደግሞ፡አለ፦ግልገሎቿ፡በዱር፡በተነጠቁ፡ጊዜ፡ድብ፡መራራ፡እንደ፡ኾነች፡በልባቸው፡መራሮች፡ እጅግም፡ኀያላን፡መኾናቸውን፡አባትኽንና፡ሰዎቹን፡ታውቃለኽ፤አባትኽ፡ዐርበኛ፡ነው፥ከሕዝብም፡ጋራ፡ አያድርም።

9አኹንም፡ምናልባት፡ባንድ፡ጕድጓድ፡ወይም፡በማናቸውም፡ስፍራ፡ተሸሽጎ፡ይኾናል፤በመዠመሪያም፡ ከነርሱ፡ዐያሌዎች፡ቢወድቁ፥የሚሰማው፡ዅሉ፦አቤሴሎምን፡የተከተለው፡ሕዝብ፡ተመታ፡ይላል።

10እስራኤልም፡ዅሉ፡አባትኽ፡ኀያል፡እንደ፡ኾነ፥ከርሱም፡ጋራ፡ያሉት፡ሰዎች፡ጽኑዓን፡እንደ፡ኾኑ፡ ያውቃልና፥ጽኑዕ፡ልቡም፡እንደ፡አንበሳ፡ልብ፡የኾነው፡ፈጽሞ፡ይቀልጣል።

11ነገር፡ግን፥የምመክርኽ፡ይህ፡ነው፤ከዳን፡እስከ፡ቤርሳቤሕ፡ያለ፡እስራኤል፡ዅሉ፡በብዛቱ፡እንደ፡ባሕር፡ አሸዋ፡ኾኖ፡ወዳንተ፡ይሰብሰብ፥አንተም፡በመካከላቸው፡ወደ፡ሰልፍ፡ውጣ።

12ርሱንም፡ወደምናገኝበት፡ወደ፡አንድ፡ስፍራ፡እንደርስበታለን፥ጠልም፡በምድር፡ላይ፡እንደሚወድቅ፡ እንወርድበታለን፤ርሱና፡ከርሱም፡ጋራ፡ያሉ፡ሰዎች፡ዅሉ፡አንድ፡ስንኳ፡አናስቀርም።

13ወደ፡ከተማም፡ቢገባ፡እስራኤል፡ዅሉ፡ወደዚያች፡ከተማ፡ገመድ፡ይወስዳል፥እኛም፡አንድ፡ድንጋይ፡ እንኳ፡እስከማይገኝባት፡ድረስ፡ወደ፡ወንዙ፡ውስጥ፡እንስባታለን።

14አቤሴሎምና፡የእስራኤልም፡ሰዎች፡ዅሉ፦የአርካዊው፡የኩሲ፡ምክር፡ከአኪጦፌል፡ምክር፡ይሻላል፡ አሉ።እግዚአብሔርም፡በአቤሴሎም፡ላይ፡ክፉ፡ያመጣ፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡መልካሚቱን፡የአኪጦፌልን፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ምክር፡እንዲበትን፡አዘዘ።

15ኩሲም፡ለካህናቱ፡ለሳዶቅና፡ለአብያታር፦አኪጦፌል፡ለአቤሴሎምና፡ለእስራኤል፡ሽማግሌዎች፡እንዲህና፡ እንዲህ፡መክሯል፤እኔ፡ግን፡እንዲህና፡እንዲህ፡መክሬያለኹ።

16አኹን፡እንግዲህ፡ንጉሡና፡ከርሱ፡ጋራ፡ያለው፡ሕዝብ፡ዅሉ፡እንዳይዋጡ፥ፈጥናችኹ።ሳትዘገይ፡ ተሻገር፡እንጂ፡በዚች፡ሌሊት፡በምድረ፡በዳ፡መሻገሪያ፡አትደር፡ብላችኹ፡ለዳዊት፡ንገሩት፡አላቸው።

17ዮናታንና፡አኪማዐስ፡ተገልጠው፡ወደ፡ከተማ፡ይገቡ፡ዘንድ፡አልቻሉም፡ነበርና፥በዐይንሮጌል፡ተቀምጠው፡ ነበር፤አንዲትም፡ባሪያ፡ኼዳ፡ትነግራቸው፡ነበር፤እነርሱም፡ኼደው፡ለንጉሡ፡ለዳዊት፡ይነግሩት፡ነበር።

18አንድ፡ብላቴናም፡አይቶ፡ለአቤሴሎም፡ነገረው፤እነርሱ፡ግን፡ፈጥነው፡ኼዱ፤ወደ፡ብራቂምም፡ወዳንድ፡ ሰው፡ቤት፡መጡ፤በግቢውም፡ውስጥ፡ጕድጓድ፡ነበረ፥ወደዚያም፡ውስጥ፡ወረዱ።

19ሴቲቱም፡በጕድጓድ፡አፍ፡ላይ፡ዳውጃ፡ዘረጋችበት፥የተከካ፡እኽልም፡በላዩ፡አሰጣችበት፤ነገሩም፡ እንዲህ፡ተሰወረ።

20የአቤሴሎም፡ባሪያዎች፡ወደ፡ሴቲቱ፡ወደ፡ቤት፡መጥተው፦አኪማዐስና፡ዮናታን፡የት፡ አሉ፧አሉ፤ሴቲቱም፦ፈፋውን፡ተሻግረው፡ኼዱ፡አለቻቸው።እነርሱም፡ፈልገው፡ባላገኟቸው፡ጊዜ፡ወደ፡ ኢየሩሳሌም፡ተመለሱ።

21ከኼዱም፡በዃላ፡እነርሱ፡ከጕድጓድ፡ወጥተው፡ኼዱ፥ለንጉሡም፡ለዳዊት፡ ነገሩት፥ዳዊትንም፦አኪጦፌል፡በእናንተ፡ላይ፡እንዲህ፡መክሯልና፥ተነሡ፥ፈጥናችኹም፡ውሃውን፡ተሻገሩ፡ አሉት።

22ዳዊትና፡ከርሱም፡ጋራ፡የነበሩት፡ዅሉ፡ተነሥተው፡ዮርዳኖስን፡ተሻገሩ፤እስኪነጋም፡ድረስ፡ዮርዳኖስን፡ ሳይሻገር፡አንድ፡ሰው፡እንኳ፡አልቀረም።

23አኪጦፌልም፡ምክሩን፡እንዳልተከተሉ፡ባየ፡ጊዜ፡አህያውን፡ጫነ፥ተነሥቶም፡ወደ፡ቤቱ፡ወደ፡ከተማው፡ ኼደ፤ቤቱንም፡አደራጅቶ፡በገዛ፡እጁ፡ታንቆ፡ሞተ፥በአባቱም፡መቃብር፡ተቀበረ።

24ዳዊትም፡ወደ፡መሃናይም፡መጣ፤አቤሴሎምም፡ከርሱም፡ጋራ፡የእስራኤል፡ሰዎች፡ዅሉ፡ዮርዳኖስን፡ ተሻገሩ።

25አቤሴሎምም፡በጭፍራው፡ላይ፡በኢዮአብ፡ስፍራ፡ዐማሳይን፡ሾመ፤ዐማሳይም፡የይስማኤላዊ፡ሰው፡ የዬቴር፡ልጅ፡ነበረ፤ርሱም፡የኢዮአብን፡እናት፡የጽሩያን፡እኅት፡የናዖስን፡ልጅ፡አቢግያን፡አግብቶ፡ነበር።

26እስራኤልና፡አቤሴሎምም፡በገለዓድ፡ምድር፡ሰፈሩ።

27ዳዊትም፡ወደ፡መሃናይም፡በመጣ፡ጊዜ፡በዐሞን፡ልጆች፡አገር፡በረባት፡የነበረ፡የናዖስ፡ልጅ፡ ኡኤስቢ፥የሎዶባርም፡ሰው፡የዓሚኤል፡ልጅ፡ማኪር፥የሮግሊምም፡ሰው፡ገለዓዳዊ፡ቤርዜሊ፥

29ሕዝቡ፡በምድረ፡በዳ፡ተርቧል፥ደክሟል፥ተጠምቷል፡ብለው፡ምንጣፍ፥ዳካ፥የሸክላም፡ ዕቃ፥ይበሉም፡ዘንድ፡ስንዴ፥ገብስ፥ዱቄት፥የተጠበሰ፡እሸት፥ባቄላ፥ምስር፥የተቈላ፡ ሽንብራ፥ማር፥ቅቤ፥በጎች፥የላምም፡ርጎ፡ለዳዊትና፡ከርሱ፡ጋራ፡ለነበሩት፡ሕዝብ፡አመጡላቸው።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source