Skip to content
← 2 Samuel

Chapter 18 · Amharic

2 Samuel

1ዳዊትም፡ከርሱ፡ጋራ፡የነበሩትን፡ሕዝብ፡ቈጠረ፥ሻለቃዎችንና፡የመቶ፡አለቃዎችንም፡ሾመላቸው።

2ዳዊትም፡ሕዝቡን፡ከኢዮአብ፡እጅ፡በታች፡ሢሶውን፥ከኢዮአብም፡ወንድም፡ከጽሩያ፡ልጅ፡ከአቢሳ፡እጅ፡ በታች፡ሢሶውን፥ከጌት፡ሰውም፡ከኢታይ፡እጅ፡በታች፡ሢሶውን፡ሰደደ።ንጉሡም፡ሕዝቡን፦እኔ፡ደግሞ፡ ከእናንተ፡ጋራ፡እወጣለኹ፡አላቸው።

3ሕዝቡ፡ግን፦አትወጣም፤ብንሸሽ፡ስለ፡እኛ፡አያስቡም፤ከእኛም፡እኩሌታው፡ቢሞት፡ስለ፡እኛ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org አያስቡም፤አንተ፡ግን፡ለብቻኽ፡ከእኛ፡ከዐሥሩ፡ሺሕ፡ይልቅ፡ትበልጣለኽ፤አኹንም፡በከተማ፡ተቀምጠኽ፡ ብትረዳን፡ይሻላል፡አሉ።

4ንጉሡም፦መልካም፡የሚመስላችኹን፡አደርጋለኹ፡አላቸው።ንጉሡም፡በበሩ፡አጠገብ፡ቆመ፥ሕዝቡም፡ ዅሉ፡መቶ፡በመቶ፡ሺሕ፡በሺሕ፡እየኾኑ፡ወጡ።

5ንጉሡም፡ኢዮአብንና፡አቢሳን፣ኢታይንም፦ለብላቴናው፡ለአቤሴሎም፡ስለ፡እኔ፡ራሩለት፡ብሎ፡ አዘዛቸው።ንጉሡም፥ስለ፡አቤሴሎም፥አለቃዎቹን፡ዅሉ፡ሲያዝ፟፥ሕዝቡ፡ዅሉ፡ሰማ።

6ሕዝቡም፡በእስራኤል፡ላይ፡ወደ፡ሜዳ፡ወጣ፤ሰልፉም፡በኤፍሬም፡ዅሉ፡ውስጥ፡ኾነ።

7በዚያም፡የእስራኤል፡ሕዝብ፡በዳዊት፡ባሪያዎች፡ፊት፡ተመቱ፥በዚያም፡ቀን፡ታላቅ፡ውጊያ፡በዚያ፡ ኾነ፥ኻያ፡ሺሕ፡ሰውም፡ሞተ።

8ከዚያም፡ሰልፉ፡በአገሩ፡ዅሉ፡ፊት፡ላይ፡ተበተነ፤በዚያም፡ቀን፡ሰይፍ፡ከዋጠው፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ይልቅ፡ ዱር፡ብዙ፡ዋጠ።

9አቤሴሎም፡ከዳዊት፡ባሪያዎች፡ጋራ፡በድንገት፡ተገናኘ፤አቤሴሎምም፡በበቅሎ፡ተቀምጦ፡ ነበር፥በቅሎውም፡ብዙ፡ቅርንጫፍ፡ባለው፡በታላቅ፡ዛፍ፡በታች፡ገባ፥ራሱም፡በዛፉ፡ተያዘ፤በሰማይና፡ በምድር፡መካከል፡ተንጠለጠለ፥ተቀምጦበትም፡የነበረ፡በቅሎ፡ዐለፈ።

10አንድ፡ሰውም፡አይቶ፦እንሆ፥አቤሴሎም፡በትልቅ፡ዛፍ፡ላይ፡ተንጠልጥሎ፡አየኹ፡ብሎ፡ለኢዮአብ፡ ነገረው።

11ኢዮአብም፡ለነገረው፡ሰው፦እንሆ፥ካየኸው፡ለምን፡ወደ፡ምድር፡አልመታኸውም፧አስር፡ብርና፡አንድ፡ ድግ፡እሰጥኽ፡ነበር፡አለው።

12ሰውዮውም፡ኢዮአብን፦እኛ፡ስንሰማ፡ንጉሡ፡አንተንና፡አቢሳን፡ኢታይንም፦ብላቴናውን፡አቤሴሎምን፡ ማንም፡እንዳይነካው፡ተጠንቀቁ፡ብሎ፡አዟ፟ልና፥ሺሕ፡ብር፡በእጄ፡ላይ፡ብትመዝን፡እጄን፡በንጉሡ፡ልጅ፡ ላይ፡ባልዘረጋኹም፡ነበር።

13እኔ፡ቅሉ፡በነፍሱ፡ላይ፡ብወነጅል፡ኖሮ፥ይህ፡ከንጉሥ፡ባልተሰወረም፥አንተም፡በተነሣኽብኝ፡ነበር፡ አለው።

14ኢዮአብም፦እኔ፡ከአንተ፡ጋራ፡እንዲህ፡እዘገይ፡ዘንድ፡አልችልም፡ብሎ፡ሦስት፡ጦሮች፡በእጁ፡ ወሰደ፥አቤሴሎምም፡ገና፡በዛፍ፡ላይ፡ተንጠልጥሎ፡ሕያው፡ሳለ፡በልቡ፡ላይ፡ተከላቸው።

15አስሩም፡የኢዮአብ፡ጋሻ፡ዣግሬዎች፡ከበቡት፥አቤሴሎምንም፡መትተው፡ገደሉት።

16ኢዮአብም፡ሕዝቡን፡ከልክሎ፡ነበርና፥ቀንደ፡መለከት፡ነፋ፥ሕዝቡም፡እስራኤልን፡ከማሳደድ፡ተመለሰ።

17አቤሴሎምንም፡ወስደው፡በዱር፡ባለ፡በታላቅ፡ጕድጓድ፡ውስጥ፡ጣሉት፥እጅግም፡ታላቅ፡የኾነ፡የድንጋይ፡ ክምር፡ከመሩበት፤እስራኤልም፡ዅሉ፡እያንዳንዱ፡ወደ፡ድንኳኑ፡ሸሸ።

18አቤሴሎምም፡ሕያው፡ሳለ፦ለስሜ፡መታሰቢያ፡የሚኾን፡ልጅ፡የለኝም፡ብሎ፥ሐውልት፡ወስዶ፥በንጉሥ፡ ሸለቆ፡ውስጥ፡ለራሱ፡አቁሞ፡ነበር፤ሐውልቱንም፡በስሙ፡ጠርቶት፡ነበር፤እስከ፡ዛሬም፡ድረስ፡የአቤሴሎም፡ መታሰቢያ፡ተብሎ፡ይጠራል።

19የሳዶቅ፡ልጅ፡አኪማዐስ፡ግን፦እግዚአብሔር፡ጠላቶቹን፡አንደ፡ተበቀለለት፡ሮጬ፡ለንጉሥ፡የምሥራች፡ ልንገር፡አለ።

20ኢዮአብም፦በሌላ፡ቀን፡እንጂ፡ዛሬ፡ወሬ፡አትናገርም፤የንጉሥ፡ልጅ፡ሞቷልና፥ዛሬ፡ወሬ፡አትናገርም፡ አለው።

21ኢዮአብም፡ኵሲ ን፦ኺድ፥ያየኸውንም፡ለንጉሡ፡ንገር፡አለው።ኵሲም፡ለኢዮአብ፡እጅ፡ነሥቶ፡ 154 ዕብ.፥ኵሺ፡(ኵሳይ•የኵሽ፡ሰው፥ኢትዮጵያዊ)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ሮጠ።

22ዳግመኛም፡የሳዶቅ፡ልጅ፡አኪማዐስ፡ኢዮአብን፦የኾነ፡ኾኖ፡ኵሲን፡ተከትዬ፥እባክኽ፥ልሩጥ፡ አለው።ኢዮአብም፦ልጄ፡ሆይ፥መልካም፡ወሬ፡የምትወስድ፡አይደለኽምና፡ትሮጥ፡ዘንድ፡ለምን፡ ትወዳ፟ለኽ፧አለ።

23ርሱም፦እኔ፡ብሮጥ፡ምን፡ይገዳ፟ል፧አለ።ርሱም፦ሩጥ፡አለው።አኪማዐስም፡በሜዳው፡መንደር፡በኩል፡ ሮጠ፥ኵሲንም፡ቀደመው።

24ዳዊትም፡በኹለት፡በር፡መካከል፡ተቀምጦ፡ነበር፤ዘበኛውም፡በቅጥሩ፡ላይ፡ወዳለው፡ወደ፡በሩ፡ሰገነት፡ ወጣ፥ዐይኑንም፡አቅንቶ፡ብቻውን፡የሚሮጥ፡ሰው፡አየ።

25ዘበኛውም፡ለንጉሡ፡ሊነግረው፡ጮኸ።ንጉሡም፦ብቻውን፡እንደ፡ኾነ፡በአፉ፡ወሬ፡ይኖራል፡አለ።

26ርሱም፡ፈጥኖ፡ቀረበ።ዘበኛውም፡ሌላ፡ሰው፡ሲሮጥ፡አየ፤ዘበኛውም፡ለደጅ፡ጠባቂው፡ ጮኾ፦እንሆ፥ብቻውን፡የሚሮጥ፡ሌላ፡ሰው፡አየኹ፡አለ።ንጉሡም፦ርሱ፡ደግሞ፡ወሬ፡ይዞ፡ይኾናል፡ አለ።

27ዘበኛውም፦የፊተኛው፡ሩጫ፡እንደ፡ሳዶቅ፡ልጅ፡እንደ፡አኪማዐስ፡ሩጫ፡ይመስላል፡ አለ፤ንጉሡም፦ርሱ፡መልካም፡ሰው፡ነው፥መልካምም፡ወሬ፡ያመጣል፡አለ።

28አኪማዐስም፡ጮኾ፡ንጉሡን፦ዅሉ፡ደኅና፡ኾኗል፡አለው።በንጉሡም፡ፊት፡በምድር፡ላይ፡በግንባሩ፡ ተደፍቶ፦በንጉሡ፡በጌታዬ፡ላይ፡እጃቸውን፡ያነሡትን፡ሰዎች፡አሳልፎ፡የሰጠ፡አምላክኽ፡እግዚአብሔር፡ ይመስገን፡አለ።

29ንጉሡም፦ብላቴናው፡አቤሴሎም፡ደኅና፡ነውን፧አለ።አኪማዐስም፦ኢዮአብ፡እኔን፡ባሪያኽንና፡ የንጉሡን፡ባሪያ፡በላከ፡ጊዜ፡ትልቅ፡ሽብር፡አይቻለኹ፥ምን፡እንደ፡ኾነ፡ግን፡አላወቅኹም፡ብሎ፡መለሰለት።

30ንጉሡም፦ፈቀቅ፡ብለኽ፡ቁም፡አለ፤ርሱም፡ፈቀቅ፡ብሎ፡ቆመ።

31እንሆም፥ኵሲ፡መጣ፤ኵሲም፦እግዚአብሔር፡በላይኽ፡የተነሡትን፡ዅሉ፡ዛሬ፡አንደ፡ተበቀለልኽ፡ ለጌታዬ፡ለንጉሡ፡ወሬ፡አምጥቻለኹ፡አለ።

32ንጉሡም፡ኵሲን፦ብላቴናው፡አቤሴሎም፡ደኅና፡ነውን፧አለው።ኵሲም፦የጌታዬ፡የንጉሡ፡ ጠላቶች፥በክፉም፡የተነሡብኽ፡ዅሉ፡እንደዚያ፡ብላቴና፡ይኹኑ፡ብሎ፡መለሰለት።

33ንጉሡም፡እጅግ፡ዐዘነ፥በበሩም፡ላይ፡ወዳለችው፡ቤት፡ወጥቶ፡አለቀሰ፤ሲኼድም፦ልጄ፡አቤሴሎም፡ ሆይ፥ልጄ፥ልጄ፡አቤሴሎም፡ሆይ፥ባንተ፡ፋንታ፡ሞቼ፡ኖሮ፡ቢኾን፥ልጄ፡አቤሴሎም፥ልጄ፡ሆይ፡ይል፡ ነበር።ች፡

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source