Skip to content
← 2 Samuel

Chapter 19 · Amharic

2 Samuel

1ኢዮአብም፡ንጉሡ፡ስለ፡አቤሴሎም፡እንዳለቀሰና፡ዋይ፡ዋይ፡እንዳለ፡ሰማ።

2በዚያም፡ቀን፦ንጉሡ፡ስለ፡ልጁ፡ዐዘነ፡ሲባል፡ሕዝቡ፡ሰምቷልና፥የዚያ፡ቀን፡ድል፡በሕዝቡ፡ዅሉ፡ ዘንድ፡ወደ፡ሐዘን፡ተለወጠ።

3ሕዝቡም፡ከሰልፍ፡የሸሸ፡ሕዝብ፡ዐፍሮ፡ወደ፡ዃላው፡እንዲል፡በዚያ፡ቀን፡ወደ፡ከተማ፡ተሰርቆ፡ገባ።

4ንጉሡም፡ፊቱን፡ሸፈነ፥ንጉሡም፡በታላቅ፡ድምፅ፦ልጄ፡አቤሴሎም፡ሆይ፥ልጄ፡አቤሴሎም፥ልጄ፡ ሆይ፡እያለ፡ይጮኽ፡ነበር።

5ኢዮአብም፡ወደ፡ንጉሡ፡ወደ፡ቤት፡ገብቶ፡እንዲህ፡አለ፦ዛሬ፡ነፍስኽንና፡የወንዶችና፡የሴቶች፡ ልጆችኽን፡ነፍስ፡የሚስቶችኽንና፡የቁባቶችኽን፡ነፍስ፡ያዳኑትን፡የባሪያዎችኽን፡ዅሉ፡ፊት፡ዛሬ፡አሳፍረኻል፤

6አንተ፡የሚጠሉኽን፡ትወዳ፟ለኽ፥የሚወዱኽንም፡ትጠላለኽ።መሳፍንትኽንና፡ባሪያዎችኽን፡እንዳታስብ፡ዛሬ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ገልጠኻል፤ዛሬ፡ዅላችን፡ሞተን፡ቢኾን፡ኖር፡አቤሴሎምም፡ድኖ፡ቢኾን፡ኖሮ፡ደስ፡ያሠኘኽ፡እንደ፡ነበረ፡ ዛሬ፡አያለኹ።

7አኹን፡እንግዲህ፡ተነሥተኽ፡ውጣ፥ለባሪያዎችኽም፡የሚያጽናናቸውን፡ነገር፡ተናገራቸው፤ያልወጣኽ፡ እንደ፡ኾነ፡ግን፡አንድ፡ሰው፡ከአንተ፡ጋራ፡በዚች፡ሌሊት፡እንዳይቀር፡በእግዚአብሔር፡እምላለኹ፤ይህም፡ ከብላቴናነትኽ፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ካገኘኽ፡ክፉ፡ነገር፡ዅሉ፡ይልቅ፡ታላቅ፡መከራ፡ይኾንብኻል።

8ንጉሡም፡ተነሥቶ፡በበሩ፡ተቀመጠ፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡ንጉሡ፡በበሩ፡እንደ፡ተቀመጠ፡ሰማ፤ሕዝቡም፡ ዅሉ፡ወደ፡ንጉሡ፡ፊት፡መጣ።እስራኤልም፡እያንዳንዱ፡ወደ፡ድንኳኑ፡ሸሽቶ፡ነበር።

9ሕዝቡም፡ዅሉ፡በእስራኤል፡ነገድ፡ዅሉ፡ውስጥ።ንጉሡ፡ከጠላቶቻችን፡እጅ፡ ታድጎናል፥ከፍልስጥኤማውያንም፡እጅ፡አድኖናል፤አኹንም፡ስለ፡አቤሴሎም፡ከአገር፡ሸሽቷል።

10በላያችን፡እንዲኾን፡የቀባነው፡አቤሴሎም፡በሰልፍ፡ሞቷል፤አኹንም፡እንግዲህ፡ንጉሡን፡ለመመለስ፡ስለ፡ ምን፡ዝም፡ትላላችኹ፧እያለ፡ርስ፡በርሱ፡ይከራከር፡ነበር።

11ንጉሡም፡ዳዊት፡ለካህናቱ፡ለሳዶቅና፡ለአብያታር፡ልኮ፡እንዲህ፡አላቸው፦ለይሁዳ፡ሽማግሌዎች፡እንዲህ፡ ብላችኹ፡ተናገሯቸው፦የእስራኤል፡ዅሉ፡ነገር፡ወደ፡ንጉሡ፡ደርሷልና፥ንጉሡን፡ወደ፡ቤቱ፡ከመመለስ፡ ስለ፡ምን፡ዘገያችኹ፧

12እናንተ፡ወንድሞቼ፥የዐጥንቴ፡ፍላጭና፡የሥጋዬ፡ቍራጭ፡ናችኹ፤እናንተ፡ንጉሡን፡ከመመለስ፡ስለ፡ ምን፡ዘገያችኹ፧

13ለዐማሳይም፦አንተ፡የዐጥንቴ፡ፍላጭና፡የሥጋዬ፡ቍራጭ፡አይደለኽምን፧በዘመንኽም፡ዅሉ፡በኢዮአብ፡ ፋንታ፡በፊቴ፡የሰራዊት፡አለቃ፡ሳትኾን፡ብትቀር፡እግዚአብሔር፡ይህን፡ያድርግብኝ፡ይህንም፡ይጨምርብኝ፡ በሉት።

14የይሁዳንም፡ሰዎች፡ዅሉ፡ልብ፡እንደ፡አንድ፡ሰው፡ልብ፡አድርጎ፡አዘነበለ፤ወደ፡ንጉሡም፡ ልከው፦አንተ፡ከባሪያዎችኽ፡ዅሉ፡ጋራ፡ተመለስ፡አሉት።

15ንጉሡም፡ተመልሶ፡እስከ፡ዮርዳኖስ፡ድረስ፡መጣ።የይሁዳ፡ሰዎች፡ንጉሡን፡ሊቀበሉ፡ንጉሡንም፡ ዮርዳኖስን፡ሊያሻግሩ፡ወደ፡ገልገላ፡መጡ።

16ከብራቂምም፡አገር፡የነበረው፡ብንያማዊው፡የጌራ፡ልጅ፡ሳሚ፡ከይሁዳ፡ሰዎች፡ጋራ፡ዳዊትን፡ሊቀበል፡ ፈጥኖ፡ወረደ።

17ከርሱም፡ጋራ፡ብንያማውያን፡የኾኑ፡ሺሕ፡ሰዎች፡ነበሩ፥የሳኦልም፡ቤት፡ባሪያ፡ሲባ፡ከርሱም፡ጋራ፡ ዐሥራ፡ዐምስቱ፡ልጆችና፡ኻያው፡ባሪያዎች፡ነበሩ፤በንጉሡም፡ፊት፡ፈጥነው፡ዮርዳኖስን፡ተሻገሩ።

18ታንኳውም፡የንጉሥን፡ቤተ፡ሰብ፡ያሻግር፡ዘንድ፡ንጉሡም፡ደስ፡ያሠኘውን፡ያደርግ፡ዘንድ፡ይሸጋገር፡ ነበር።ንጉሡም፡ዮርዳኖስን፡ከተሻገረ፡በዃላ፡የጌራ፡ልጅ፡ሳሚ፡በፊቱ፡ተደፋ።

19ንጉሡንም፦ጌታዬ፡ሆይ፥ኀጢአቴን፡አትቍጠርብኝ፤ጌታዬ፡ንጉሡ፥ከኢየሩሳሌም፡በወጣኽ፡ቀን፡ ባሪያኽ፡የበደልኹኽን፡አታስብብኝ፥ንጉሡም፡በልቡ፡አያኑረው።

20ባሪያኽ፡በደለኛ፡እንደ፡ኾንኹ፡ዐውቄያለኹና፥እንሆ፥ከዮሴፍ፡ቤት፡ዅሉ፡አስቀድሜ፡ዛሬ፡ መጣኹ፥ጌታዬንም፡ንጉሡን፡ልቀበል፡ወረድኹ፡አለው።

21የጽሩያ፡ልጅ፡አቢሳ፡ግን፦ሳሚ፡እግዚአብሔር፡የቀባውን፡ሰድቧልና፥ሞት፡የተገባው፡አይደለምን፧አለ።

22ዳዊትም፦እናንተ፡የጽሩያ፡ልጆች፥እኔ፡ከእናንተ፡ጋራ፡ምን፡አለኝ፧ዛሬ፡ስለ፡ምን፡ጠላቶች፡ ትኾኑብኛላችኹ፧ዛሬስ፡በእስራኤል፡ዘንድ፡ሰው፡ሊሞት፡ይገ፟ባ፟ልን፧ዛሬስ፡በእስራኤል፡ላይ፡እንደ፡ነገሥኹ፡ አላወቅኹምን፧አለ።

23ንጉሡም፡ሳሚን፦አትሞትም፡አለው።ንጉሡም፡ማለለት። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

24የሳኦልም፡ልጅ፡ሜምፊቦስቴ፡ንጉሡን፡ሊቀበል፡ወረደ፤ንጉሡም፡ከኼደ፡ዠምሮ፡በደኅና፡ እስከተመለሰበት፡ቀን፡ድረስ፡እግሩን፡አልጠገነም፥ጢሙንም፡አልቈረጠም፥ልብሱንም፡አላጠበም፡ነበር።

25ንጉሡም፡ሊቀበለው፡ከኢየሩሳሌም፡በመጣ፡ጊዜ፡ንጉሡ።ሜምፊቦስቴ፡ሆይ፥ከእኔ፡ጋራ፡ስለ፡ምን፡ አልወጣኽም፧አለው።

26ርሱም፡መልሶ፡አለ፦ጌታዬን፥ንጉሥ፡ሆይ፥ባሪያዬ፡አታለለኝ፤እኔ፡ባሪያኽ፡ዐንካሳ፡ነኝና።ከንጉሥ፡ ጋራ፡እኼድ፡ዘንድ፡የምቀመጥበትን፡አህያ፡ልጫን፡አልኹት።

27ርሱም፡እኔን፡ባሪያኽን፡ለጌታዬ፡ለንጉሡ፡አማ፤አንተ፡ጌታዬ፡ንጉሥ፡ግን፡እንደእግዚአብሔር፡መልአክ፡ ነኽ፤ደስም፡ያሠኘኽን፡አድርግ።

28የአባቴ፡ቤት፡ዅሉ፡በጌታዬ፡በንጉሡ፡ዘንድ፡ሞት፡የሚገ፟ባ፟ቸው፡ነበሩ፤አንተ፡ግን፡እኔን፡ባሪያኽን፡ በገበታኽ፡በሚበሉ፡መካከል፡አስቀመጥኸኝ፤ለንጉሥ፡ደግሞ፡ለመናገር፡ምን፡መብት፡አለኝ፧

29ንጉሡም፦ነገርኽን፡ለምን፡ታበዛለኽ፧አንተና፡ሲባ፡ዕርሻውን፡ትካፈሉ፡ዘንድ፡ብያለኹ፡አለው።

30ሜምፊቦስቴም፡ንጉሡን፦ጌታዬ፡ንጉሡ፡በደኅና፡ወደ፡ቤቱ፡ከተመለሰ፡ርሱ፡ዅሉን፡ይውሰደው፡ አለው።

31ገለዓዳዊውም፡ቤርዜሊ፡ከሮግሊም፡ወረደ፤ሊሸኘውም፡ከንጉሡ፡ጋራ፡ዮርዳኖስን፡ተሻገረ።

32ቤርዜሊም፡እጅግ፡ያረጀ፡የሰማንያ፡ዓመት፡ሽማግሌ፡ነበረ፤እጅግም፡ትልቅ፡ሰው፡ነበረና፡ንጉሡ፡ በመሃናይም፡ሳለ፡ይቀልበው፡ነበር።

33ንጉሡም፡ቤርዜሊን፦በኢየሩሳሌም፡እቀልብኽ፡ዘንድ፡ከእኔ፡ጋራ፡ዕለፍ፡አለው።

34ቤርዜሊም፡ንጉሡን፡አለው፦ከንጉሡ፡ጋራ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡እወጣ፡ዘንድ፡ከሕይወቴ፡ዘመን፡ምን፡ ያኽል፡ቀረኝ፧

35ዛሬ፡የሰማንያ፡ዓመት፡ሽማግሌ፡ነኝ፤መልካሙንና፡ክፉውን፡መለየት፡እችላለኹን፧እኔ፡ባሪያኽ፡ የምበላውንና፡የምጠጣውን፡ጣዕሙን፡መለየት፡እችላለኹን፧የወንዱንና፡የሴቲቱን፡ዘፈን፡ድምፅ፡መስማት፡ እችላለኹን፧እኔ፡ባሪያኽ፡በጌታዬ፡በንጉሡ፡ላይ፡ለምን፡እከብድብኻለኹ፧

36እኔ፡ባሪያኽ፡ዮርዳኖስን፡ተሻግሬ፡ከንጉሡ፡ጋራ፡ጥቂት፡ልኼድ፡ነበር፤ንጉሡ፡እንዲህ፡ያለ፡ወረታ፡ ለምን፡ይመልስልኛል፧

37እኔ፡ባሪያኽ፡ተመልሼ፡በከተማዬ፡በአባቴና፡በእናቴ፡መቃብር፡አጠገብ፥እባክኽ፥ልሙት።ነገር፡ ግን፥ባሪያኽን፡ከመዓምን፡እይ፤ርሱ፡ከጌታዬ፡ከንጉሡ፡ጋራ፡ይለፍ፥ደስ፡የሚያሠኝኽንም፡ለርሱ፡አድርግ።

38ንጉሡም፦ከመዓም፡ከእኔ፡ጋራ፡ይለፍ፥ደስ፡የሚያሠኝኽንም፡አደርግለታለኹ፤አንተም፡ከእኔ፡ የምትሻውን፡ዅሉ፡አደርግልኻለኹ፡አለው።

39ሕዝቡም፡ዅሉ፡ዮርዳኖስን፡ተሻገረ፥ንጉሡም፡ተሻገረ፤ንጉሡም፡ቤርዜሊን፡ሳመው፥መረቀውም፤ወደ፡ ስፍራውም፡ተመለሰ።

40ንጉሡም፡ወደ፡ገልገላ፡ተሻገረ፥ከመዓምም፡ከርሱ፡ጋራ፡ኼደ፤የይሁዳም፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ደግሞም፡ የእስራኤል፡ሕዝብ፡እኩሌታ፡ንጉሡን፡አሻገረው።

41እንሆም፥የእስራኤል፡ሰዎች፡ዅሉ፡ወደ፡ንጉሥ፡መጡ፥ንጉሡንም፦ወንድሞቻችን፡የይሁዳ፡ሰዎች፡ ለምን፡ሰረቁኽ፧ንጉሡንም፡ቤተ፡ሰቡንም፡ከርሱም፡ጋራ፡የዳዊትን፡ሰዎች፡ዅሉ፡ዮርዳኖስን፡አሻገሩ፧አሉት።

42የይሁዳም፡ሰዎች፡ዅሉ፡ለእስራኤል፡ሰዎች፡መልሰው፦ንጉሡ፡ለእኛ፡ቅርባችን፡ነው፤ስለ፡ምን፡በዚህ፡ ነገር፡ትቈጣላችኹ፧በእውኑ፡ከንጉሡ፡አንዳች፡በልተናልን፧ወይስ፡ርሱ፡በረከት፡ሰጥቶናልን፧አሉ።

43የእስራኤልም፡ሰዎች፡ለይሁዳ፡ሰዎች፡መልሰው፦በንጉሡ፡ዘንድ፡ለእኛ፡ዐሥር፡ክፍል፡ አለን፥በዳዊትም፡ዘንድ፡ደግሞ፡ከእናንተ፡ይልቅ፡መብት፡አለን፤ስለ፡ምን፡ናቃችኹን፧ስለ፡ምንስ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ንጉሣችንን፡ለመመለስ፡ቀድሞ፡ምክር፡አልጠየቃችኹንም፧አሉ።የይሁዳም፡ሰዎች፡ቃል፡ከእስራኤል፡ሰዎች፡ ቃል፡ይልቅ፡ጠነከረ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source