Skip to content
← Amos

Chapter 3 · Amharic

Amos

1የእስራኤል፡ልጆች፡ሆይ፥እግዚአብሔር፡በእናንተ፥ከግብጽ፡ምድር፡ባወጣኹት፡ወገን፡ዅሉ፡ላይ፡ የተናገረውን፡ይህን፡ቃል፡ስሙ፤

2እንዲህም፡ብሏል፦እኔ፡ከምድር፡ወገን፡ዅሉ፡እናንተን፡ብቻችኹን፡ዐውቄያችዃለኹ፤ስለዚህ፥ስለ፡ ኀጢአታችኹ፡ዅሉ፡እበቀላችዃለኹ።

3በእውኑ፡ኹለት፡ሰዎች፡ሳይስማሙ፡በአንድነት፡ይኼዳሉን፧

4ወይስ፡አንበሳ፡የሚነጥቀው፡ነገር፡ሳያገኝ፡በጫካ፡ውስጥ፡ያገሣልን፧ወይስ፡የአንበሳ፡ደቦል፡አንዳች፡ ሳይዝ፡በመደቡ፡ኾኖ፡ይጮኻልን፧

5ወይስ፡ወፍ፥አጥማጅ፡ከሌለው፥በምድር፡ላይ፡በወጥመድ፡ይያዛልን፧ወይስ፡ወስፈንጠር፡አንዳች፡ሳይዝ፡ ከምድር፡ይፈነጠራልን፧ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

6ወይስ፡በከተማ፡ውስጥ፡መለከት፡ሲነፋ፡ሕዝቡ፡አይፈራምን፧ወይስ፡ክፉ፡ነገር፡በከተማ፡ላይ፡የመጣ፡ እንደ፡ኾነ፡ያደረገው፡እግዚአብሔር፡አይደለምን፧

7በእውነት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ምስጢሩን፡ለባሪያዎቹ፡ለነቢያት፡ካልነገረ፡በቀር፡ምንም፡አያደርግም።

8አንበሳው፡አገሣ፤የማይፈራ፡ማን፡ነው፧ጌታ፡እግዚአብሔር፡ተናገረ፤ትንቢት፡የማይናገር፡ማን፡ነው፧

9በአዛጦን፡አዳራሾችና፡በግብጽ፡ምድር፡አዳራሾች፡አውሩና፦በሰማርያ፡ተራራዎች፡ላይ፡ ተሰብሰቡ፥በውስጧም፡የኾነውን፡ታላቁን፡ውካታ፥በመካከሏም፡ያለውን፡ግፍ፡ተመልከቱ፡በሉ።

10ግፍንና፡ቅሚያን፡በአዳራሾቻቸው፡የሚያከማቹት፡ቅን፡ነገርን፡ያደርጉ፡ዘንድ፡አያውቁም፥ይላል፡ እግዚአብሔር።

11ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በምድሪቱ፡ዙሪያ፡ጠላት፡ይመጣል፤ብርታትሽንም፡ከአንቺ፡ ያወርዳል፥አዳራሾችሽም፡ይበዘበዛሉ።

12እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እረኛ፡ከአንበሳ፡አፍ፡ኹለት፡እግርን፡ወይም፡የዦሮን፡ጫፍ፡ እንደሚያድን፥እንዲሁ፡በሰማርያ፡በዐልጋ፡ማእዘን፥በደማስቆም፡በምንጣፍ፡ላይ፡የተቀመጡት፡የእስራኤል፡ ልጆች፡ይድናሉ።

13ስሙ፥በያዕቆብም፡ቤት፡ላይ፡መስክሩ፥ይላል፡የሰራዊት፡አምላክ፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

14እስራኤልን፡ስለ፡ኀጢአቱ፡በምበቀልበት፡ቀን፡የቤቴልን፡መሠዊያዎች፡ደግሞ፡እበቀላለኹ፤የመሠዊያው፡ ቀንዶች፡ይሰበራሉ፥ወደ፡ምድርም፡ይወድቃሉ።

15የክረምቱንና፡የበጋውን፡ቤት፡እመታለኹ፤በዝኆንም፡ጥርስ፡የተለበጡት፡ቤቶች፡ይጠፋሉ፥ታላላቆችም፡ ቤቶች፡ይፈርሳሉ፥ይላል፡እግዚአብሔር።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source