Skip to content
← Amos

Chapter 5 · Amharic

Amos

1የእስራኤል፡ቤት፡ሆይ፥በእናንተ፡ላይ፡ለሙሾ፡የማነሣውን፡ይህን፡ቃል፡ስሙ።

2የእስራኤል፡ድንግል፡ወደቀች፥ከእንግዲህም፡ወዲህ፡አትነሣም፤በምድሯ፡ላይ፡ተጣለች፥የሚያስነሣትም፡ የለም።

3ጌታ፡እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡ይላልና፦ሺሕ፡ከሚወጣባት፡ከተማ፡መቶ፡ይቀርላታል፥መቶም፡ ከሚወጣባት፡ከተማ፡ለእስራኤል፡ቤት፡ዐሥር፡ይቀርላታል።

4እግዚአብሔርም፡ለእስራኤል፡ቤት፡እንዲህ፡ይላልና፦እኔን፡ፈልጉ፥በሕይወትም፡ትኖራላችኹ፤

5ነገር፡ግን፥ገልገላ፡ፈጽሞ፡ትማረካለችና፥ቤቴልም፡ከንቱ፡ትኾናለችና፡ቤቴልን፡አትፈልጉ፥ወደ፡ ገልገላም፡አትግቡ፥ወደ፡ቤርሳቤሕም፡አትለፉ።

6በዮሴፍ፡ቤት፡እሳት፡እንዳትቃጠል፥በቤቴል፡የሚያጠፋትም፡ሳይኖር፡እንዳትበላ፥እግዚአብሔርን፡ ፈልጉ፥በሕይወትም፡ትኖራላችኹ።

7ፍርድን፡ወደ፡ሬት፡የምትለውጡ፥ጽድቅንም፡በምድር፡ላይ፡የምትጥሉ፡እናንተ፡ሆይ፥

8ሰባቱን፡ከዋክብትና፡ኦሪዮን፡የተባለውን፡ኮከብ፡የፈጠረውን፥የሞትን፡ጥላ፡ወደ፡ንጋት፡ የሚለውጠውን፥ቀኑንም፡በሌሊት፡የሚያጨልመውን፥የባሕሩንም፡ውሃዎች፡ጠርቶ፡በምድር፡ፊት፡ላይ፡ የሚያፈሳ፟ቸውን፥

9ዐምባውም፡እንዲፈርስ፡በብርቱ፡ላይ፡የድንገት፡ጥፋት፡የሚያመጣውን፡ፈልጉ፤ስሙ፡እግዚአብሔር፡ነው።

10በበሩ፡አደባባይ፡የሚገሥጸውን፡ጠሉ፥እውነትም፡የሚናገረውን፡ተጸየፉ።

11ድኻውንም፡ደብድባችዃልና፥የስንዴውንም፡ቀረጥ፡ከርሱ፡ወስዳችዃልና፥ከተጠረበ፡ድንጋይ፡ቤቶችን፡ ሠርታችዃል፥ነገር፡ግን፥አትቀመጡባቸውም፤ያማሩ፡የወይን፡ቦታዎች፡ተክላችዃል፥ነገር፡ግን፥ከወይን፡ ጠጃቸው፡አትጠጡም።

12ጻድቁን፡የምታስጨንቁ፥ጕቦንም፡የምትቀበሉ፥በበሩም፡አደባባይ፡የችጋረኛውን፡ፍርድ፡የምታጣምሙ፡ እናንተ፡ሆይ፥በደላችኹ፡እንዴት፡እንደ፡በዛ፥ኀጢአታችኹም፡እንዴት፡እንደ፡ጸና፡እኔ፡ዐውቃለኹና።

13ስለዚህ፥ክፉ፡ዘመን፡ነውና፥በዚያ፡ዘመን፡አስተዋይ፡የሚኾን፡ዝም፡ይላል።

14በሕይወት፡ትኖሩ፡ዘንድ፡መልካሙን፡እንጂ፡ክፉውን፡አትፈልጉ፤እንዲህም፡እናንተ፡እንደ፡ተናገራችኹ፡ የሰራዊት፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ከእናንተ፡ጋራ፡ይኾናል።

15ክፉውን፡ጥሉ፥መልካሙንም፡ውደዱ፥በበሩም፡አደባባይ፡ፍርድን፡አጽኑ፤ምናልባት፡የሰራዊት፡አምላክ፡ እግዚአብሔር፡ለዮሴፍ፡ቅሬታ፡ይራራ፡ይኾናል። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

16ስለዚህ፥ጌታ፡የሰራዊት፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በያደባባዩ፡ዅሉ፡ላይ፡ዋይታ፡ ይኾናል፤በየመንገዱም፡ዅሉ፡ላይ፡ወዮ፡ወዮ፡ይባላል፤ገበሬዎቹም፡ወደ፡ልቅሶ፥አልቃሾቹም፡ወደ፡ዋይታ፡ ይጠራሉ።

17በመካከልኽ፡ዐልፋለኹና፡በወይኑ፡ቦታ፡ዅሉ፡ልቅሶ፡ይኾናል፥ይላል፡እግዚአብሔር።

18የእግዚአብሔርን፡ቀን፡ለምትፈልጉ፡ወዮላችኹ! የእግዚአብሔርን፡ቀን፡ለምን፡ትፈልጋላችኹ፧ጨለማ፡ ነው፡እንጂ፡ብርሃን፡አይደለም።

19ከአንበሳ፡ፊት፡እንደ፡ሸሸ፡ድብም፡እንዳገኘው፡ሰው፥ወይም፡ወደ፡ቤት፡ገብቶ፡እጁን፡በግድግዳ፡ላይ፡ እንዳስደገፈና፡እባብ፡እንደ፡ነደፈው፡ሰው፡ነው።

20የእግዚአብሔር፡ቀን፡ብርሃን፡ሳይኾን፡ጨለማ፡አይደለምን፧ጸዳል፡የሌለውም፡ድቅድቅ፡ጨለማ፡ አይደለምን፧

21ዓመት፡በዓላችኹን፡ጠልቼዋለኹ፡ተጸይፌውማለኹ፤የተቀደሰውም፡ጉባኤያችኹ፡ደስ፡አያሠኘኝም።

22የሚቃጠለውን፡መሥዋዕታችኹና፡የእኽሉን፡ቍርባናችኹን፡ብታቀርቡልኝም፡እንኳ፡ አልቀበለውም፤ለምስጋና፡መሥዋዕት፡የምታቀርቡልኝን፡የሰቡትን፡እንስሳዎች፡አልመለከትም።

23የዝማሬኽንም፡ጩኸት፡ከእኔ፡ዘንድ፡አርቅ፤የመሰንቆኽንም፡ዜማ፡አላደምጥም።

24ነገር፡ግን፥ፍርድ፡እንደ፡ውሃ፥ጽድቅም፡እንደማይደርቅ፡ፈሳሽ፡ይፍሰስ።

25የእስራኤል፡ቤት፡ሆይ፥በእውኑ፡በምድረ፡በዳ፡አርባ፡ዓመት፡ሙሉ፡መሥዋዕትንና፡ቍርባንን፡ አቅርባችኹልኛልን፧

26ለራሳችኹም፡የሠራችዃቸውን፡ምስሎች፥የሞሎክን፡ድንኳንና፡የአምላካችኹን፡የሬፋን፡ኮከብ፡አነሣችኹ።

27ስለዚህ፥ከደማስቆ፡ወደዚያ፡አስማርካችዃለኹ፥ይላል፡ስሙ፡የሰራዊት፡አምላክ፡የተባለ፡እግዚአብሔር።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source