Skip to content
← Amos

Chapter 6 · Amharic

Amos

1በጽዮን፡ላሉ፡ዓለመኛዎች፥በሰማርያም፡ተራራ፡ላይ፡ተዘልለው፡ለተቀመጡ፥የእስራኤልም፡ቤት፡ወደ፡ እነርሱ፡ለመጡባቸው፡ለአሕዛብ፡አለቃዎች፡ወዮላቸው!

2ወደ፡ካልኔ፡ዐልፋችኹ፡ተመልከቱ፤ከዚያም፡ወደ፡ታላቂቱ፡ሐማት፡ኺዱ፤ከዚያም፡ወደ፡ፍልስጥኤም፡ ጌት፡ውረዱ፤እነርሱ፡ከነዚህ፡መንግሥታት፡ይሻላሉን፧ወይስ፡ድንበራቸው፡ከድንበራችኹ፡ይሰፋልን፧

3ክፉውን፡ቀን፡ከእናንተ፡ለምታርቁ፥የግፍንም፡ወንበር፡ለምታቀርቡ፥

4ከዝኆን፡ጥርስ፡በተሠራ፡ዐልጋ፡ላይ፡ለምትተኙ፥በምንጣፋችኹም፡ላይ፡ተደላድላችኹ፡ ለምትቀመጡ፥ከበጎችም፡መንጋ፡ጠቦትን፡ከጋጥም፡ውስጥ፡ጥጃን፡ለምትበሉ፥

5በመሰንቆም፡ድምፅ፡ለምትንጫጩ፥እንደ፡ዳዊትም፡የዜማን፡ዕቃ፡ለምታዘጋጁ፥

6በፋጋ፡የወይን፡ጠጅ፡ለምትጠጡ፥እጅግ፡ባማረ፡ሽቱም፡ለምትቀቡ፥ስለዮሴፍ፡መከራ፡ግን፡ለማታዝኑ፡ ለእናንተ፡ወዮላችኹ!

7ስለዚህ፥በምርኮ፡መዠመሪያ፡ይማረካሉ፥ተደላድለው፡ከተቀመጡትም፡ዘንድ፡ዘፈን፡ይርቃል።

8ጌታ፡እግዚአብሔር፦የያዕቆብን፡ትዕቢት፡ተጸይፌያለኹ፥አዳራሾቹንም፡ጠልቻለኹ፤ስለዚህ፥ከተማዪቱንና፡ የሚኖሩባትን፡ዅሉ፡አሳልፌ፡እሰጣለኹ፡ብሎ፡በራሱ፡ምሏል፥ይላል፡የሰራዊት፡አምላክ፡እግዚአብሔር።

9እንዲህም፡ይኾናል፤ዐሥር፡ሰዎች፡ባንድ፡ቤት፡ውስጥ፡ቢቀሩ፡እነርሱ፡ይሞታሉ።

10ዐጥንቱንም፡ከቤቱ፡ያወጡ፡ዘንድ፡የሰው፡ዘመድና፡አቃጣዩ፡ባነሡት፡ጊዜ፥በቤቱም፡ውስጥ፡ ያለውን፦እስከ፡አኹን፡ድረስ፡ገና፡ሰው፡ባንተ፡ዘንድ፡አለን፧ባለው፡ጊዜ፥ርሱም፦ማንም፡የለም፡ባለ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ጊዜ፤ያን፡ጊዜ፦የእግዚአብሔርን፡ስም፡እንጠራ፡ዘንድ፡አይገ፟ባ፟ንምና፥ዝም፡በል፡ይለዋል።

11እንሆም፥እግዚአብሔር፡ያዛ፟ል፤ታላቁንም፡ቤት፡በማፍረስ፥ታናሹንም፡ቤት፡በመሰባበር፡ይመታል።

13ፍርድን፡ወደ፡ሐሞት፥የጽድቅንም፡ፍሬ፡ወደ፡ሬት፡የለወጣችኹ፥በከንቱም፡ነገር፡ደስ፡ የሚላችኹ፦በኀይላችን፡ቀንድ፡የወሰድን፡አይደለምን፧የምትሉ፥እናንተ፡ሆይ፥በእውኑ፡ፈረሶች፡በጭንጫ፡ ላይ፡ይጋልባሉን፧ወይስ፡በሬዎች፡በዚያ፡ላይ፡ያርሳሉን፧

14የእስራኤል፡ቤት፡ሆይ፥እንሆ፥እኔ፡ሕዝብን፡አስነሣባችዃለኹ፥ይላል፡የሰራዊት፡አምላክ፡ እግዚአብሔር፤እነርሱም፡ከሐማት፡መግቢያ፡ዠምረው፡እስከዐረባ፡ወንዝ፡ድረስ፡ያስጨንቋችዃል።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source