1ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡አሳየኝ፤እንሆም፥የዃለኛው፡ሣር፡በሚበቅልበት፡መዠመሪያ፡ላይ፡አንበጣን፡ ፈጠረ፤እንሆም፥ከንጉሡ፡ዐጨዳ፡በዃላ፡የበቀለ፡የገቦ፡ነበረ።
2የምድሩንም፡ሣር፡በልተው፡ከጨረሱ፡በዃላ፥እኔ፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡ሆይ፥ይቅር፡እንድትል፡ እለምንኻለኹ፤ያዕቆብ፡ታናሽ፡ነውና፥እንዴት፡ይቆማል፧አልኹ።
3እግዚአብሔርም፡ስለዚህ፡ነገር፡ተጸጸተ፤ይህ፡አይኾንም፥ይላል፡እግዚአብሔር።
4ጌታ፡እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡አሳየኝ፤እንሆም፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡በእሳት፡ለመፍረድ፡ጠራ፤ርሷም፡ ታላቁን፡ቀላይና፡ምድርን፡በላች።
5እኔም፦ጌታ፡እግዚአብሔር፡ሆይ፥እንድትተው፡እለምንኻለኹ፤ያዕቆብ፡ታናሽ፡ነውና፥እንዴት፡ ይቆማል፧አልኹ።
6እግዚአብሔርም፡ስለዚህ፡ነገር፡ተጸጸተ፤ይህ፡ደግሞ፡አይኾንም፥ይላል፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
7እንዲህም፡አሳየኝ፤እንሆም፥ጌታ፡ቱንቢውን፡ይዞ፡በቱንቢ፡በተሠራ፡ቅጥር፡ላይ፡ቆሞ፡ነበር።
8እግዚአብሔርም፦ዓሞጽ፡ሆይ፥የምታየው፡ምንድር፡ነው፧አለኝ።እኔም፦ቱንቢ፡ነው፡ አልኹ።ጌታም፦እንሆ፥በሕዝቤ፡በእስራኤል፡መካከል፡ቱንቢ፡አደርጋለኹ፤ከእንግዲህም፡ወዲህ፡ደግሞ፡ አላልፋቸውም፤
9የይሥሐቅም፡የኰረብታው፡መስገጃዎች፡ይፈርሳሉ፥የእስራኤልም፡መቅደሶች፡ባድማ፡ ይኾናሉ፤በኢዮርብዓምም፡ቤት፡ላይ፡በሰይፍ፡እነሣለኹ፡አለ።
11የቤቴልም፡ካህን፡አሜስያስ፡ወደእስራኤል፡ንጉሥ፡ወደ፡ኢዮርብዓም፡ልኮ፦ዓሞጽ፦ኢዮርብዓም፡ በሰይፍ፡ይሞታል፥እስራኤልም፡ከአገሩ፡ተማርኮ፡ይኼዳል፡ብሏልና፥ዓሞጽ፡በእስራኤል፡ቤት፡መካከል፡ ዐምፆብኻል፤ምድሪቱም፡ቃሉን፡ዅሉ፡ልትሸከም፡አትችልም፡አለ።
12አሜስያስም፡ዓሞጽን፦ባለራእዩ፡ሆይ፥ኺድ፡ወደይሁዳም፡ምድር፡ሽሽ፥በዚያም፡እንጀራን፡ብላ፥
13በዚያም፡ትንቢትን፡ተናገር፤ነገር፡ግን፥ቤቴል፡የንጉሥ፡መቅደስና፡የመንግሥት፡ቤት፡ናትና፥ከእንግዲህ፡ ወዲህ፡በዚህ፡ደግሞ፡ትንቢት፡አትናገር፡አለው።
14ዓሞጽም፡መልሶ፡አሜስያስን፡አለው፦እኔ፡ላም፡ጠባቂና፡ወርካ፡ለቃሚ፡ነኝ፡እንጂ፡ነቢይ፡ወይም፡ የነቢይ፡ልጅ፡አይደለኹም፤
15እግዚአብሔርም፡በጎቹን፡ከመከተል፡ወሰደኝ፥እግዚአብሔርም፦ኺድ፥ለሕዝቤም፡ለእስራኤል፡ትንቢት፡ ተናገር፡አለኝ።
16አኹንም፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስማ፤አንተ፦በእስራኤል፡ላይ፡ትንቢት፡አትናገር፥በይሥሐቅም፡ቤት፡ ላይ፡አትስበክ፡ብለኻል፤ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
17ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ሚስትኽ፡በከተማዪቱ፡ውስጥ፡ጋለሞታ፡ትኾናለች፥ወንዶችና፡ ሴቶች፡ልጆችኽም፡በሰይፍ፡ይወድቃሉ፥ምድርኽም፡በገመድ፡ትከፈላለች፤አንተም፡በረከሰች፡ምድር፡ ትሞታለኽ፥እስራኤልም፡ከምድሩ፡ተማርኮ፡ይኼዳል።